General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ፡- ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የ2017 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡ 

ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት የሦስተኛውን ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት  የኮሌጁ የተቋም ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ሰባሁዲን ሁሴን ለታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት መረጃ መሰረት በ9 ወሩ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር፣ የተቋሙን መሰረተ ልማት ከማስተካከል አኳያ፣ ተቋማዊ ሪፎርም ከመተግበር ረገድ እና ሁሉም አካል በየዘርፉ ተነሳሽነት እና ቅንጅት ፈጥሮ ስራዎችን ከመከወን አንፃር እምርታዊ ለውጥ ያሳዬ እና ስኬታማ እንደነበር ተገልጿል፡፡
     
በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በቀሪው ጊዜና በቀጣይ ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ መሟላት ያለባቸው ግብዓቶችና መተግበር የሚኖርባቸው አሰራሮች እንዲሁም ከአካባቢ የመልማት ፀጋና ተከታታይ የሪፎርም ትግበራ ጋር ተያይዞ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው በኮሌጁ ዋና ዲን በአቶ መለሰ ይግዛው አማካኝነት ማጠቃለያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ሰኞ፡- ሚያዚያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም

4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ዛሬ ተጀመረ።

ለአሸናፊዎች የሜዳሊያ፣ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

ዘንድሮ የሚካሄደው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር " ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች " በሚል ሀሰብ እንደሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።

መርሃ ግብሩ ከዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን እስከ ግንቦታ 2 ቀን 2017 ዓ/ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት እየተካሄደ ይቆያል።

ውድድሩ በክህሎት፣ በቴክኖሎጂና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዘርፎች ነው የሚካሄደው።

በውድድሩም፣ " በሁሉም ክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች በተካሄዱ ተመሳሳይ ውድድሮች አንደኛ ሆነው ያጠናቀቁ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች፣ የኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች ይሳተፋሉ " ተብሏል።

ለውድድሩ አሸናፊዎች የሜዳሊያ፣ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል።

የውድድሩ ዓላማ የዘርፉን አዲስ እሳቤ መሠረት ያደረገ የአሰልጣኞች፣ የሠልጣኞችና ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሙያቸውን እንዲያዳብሩ፣ አቅማቸውን እንዳያሳዩ፣ ቴክኖሎጂችን ባለሃብቶችና ኢንተርፕራይዞች ወደ ምርት አገልግሎት እንዲያሸጋግሩ ጭምር ነው።

በ2015 ዓ/ም በ3ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂ የፈጠሩ ተወዳዳሪዎች በ2016 ዓ/ም ከ80 በላይ ቴክኖሎጂዎችን እንዳመረቱ ተነግሯል።

ፕሮግራሙ በ2017 በጀት ዓመት “ስኪል ኢትዮጵያ” በሚል ስያሜ ቀጥሎ፣ በአሁኑ ጊዜም 180 የሚሆኑ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አምርተው በማውጣት ሂደት እንደሚገኙ ተመልክቷል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

ምንጭ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርብ:- ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮሌጁ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በሀገር አቀፍ ደረጃ አሸነፈ!!

በኮሌጁ አሰልጣኞች የተሰራው የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሰነድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳድሮ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

ይህ የጥናት ሰነድ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር ላይ መነሳቱ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተጓዘው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ አመርቂ ውጤቶች፣ የይዘትና የአቀራረብ ብቃት ወዘተ በሚሉ መስፈርቶች ተመዝኖ በስልጠና መስክ የሀገርን ችግሮች ከሚፈቱ ቀዳሚ ጥናቶች አንዱ ሆኗል፡፡

"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ ከሚያዚያ 27   እስከ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ የኮሌጁ አሰልጣኞች ''የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ሰልጣኞች በስልጠና መጨረሻ ዓመት ላይ በሚሰሯቸው ፕ‹ሮጀክቶች እና ድህረ ልምምዶች ላይ የሰልጣኞችን ልል ክህሎት  እንዲት ማሳደግ ይቻላል?›› በሚል ርዕስ የተሰራው ከኮሌጁ ባሻገር የከተማ አስተዳደሩን የሚዲሊያ ባለቤት አድርጎታል፡፡

በዚህ የውድድር ዘርፍ ከ12 ክልሎችና ከ2 ከተማ አስተዳደሮች 14 ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሰነዶች ቀርበው በጀኔራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተሰራውና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የወከለው ጥናት 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ የአማራ ክልል 1ኛ ደረጃ የኦሮሚያ ክልል ደግሞ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

4ኛው ሀገር አቀፍ የብቃት ውድድር በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የተካሄደ ሲሆን ውድድሩም በክህሎት፣ በቴክኖሎጂ እና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዘርፎች የተደረገ እንደነበር መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
እሁድ:- ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የክህሎት ውድድር ኮሌጁ 3 ሜዲያሊያዎችን አገኘ!!

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር በአሰልጣኞችና ሰልጣኞች ውድድር ውጤት ኮሌጁ 3 ሜዲያሊያዎችን አግኝቷል።

ዘንድሮ "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 27 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ሰልጣኞች በተለያየ ክህሎት አሰልጣኞች ደግሞ በጥናትና ምርምር ኮሌጁ ሜዲያሊያዎችን እንዲያገኝ አድርገዋል።

የኮሌጁ አሰልጣኞች ''የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ሰልጣኞች በስልጠና መጨረሻ ዓመት ላይ በሚሰሯቸው ፕሮጀክቶች እና ድህረ ልምምዶች ላይ የሰልጣኞችን ልል ክህሎት  እንዴት ማሳደግ ይቻላል?›› በሚል ርዕስ የተሰራው ጥናት 2ኛ ደረጃን ይዞ የብር ሜዲያሊያ እና የ400ሺ ብር ሽልማት አስገኝቷል።

በሰልጣኝ የክህሎት ፉክክር ደግሞ በጋርመንት ፕሮዳክሽን የወርቅ ሜዲያሊያ ና የ500ሺ ብር ሽልማት እንዲሁም ከኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት በስትራክቸራል ኮንስትራክሽን ሙያ የነሐስ ሜዲያሊያና የ300ሺ ብር ሽልማት ተበርክቷል።

በተያያዘ ዜና በ12 ክልሎችና በ2 ከተማ አስተዳደሮች በተካሄደው የክህሎት ውድድር ድምር ውጤት የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር አንደኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ረቡዕ:- ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ∙ም

ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የቴክኖሎጂ ሽግግር ተደረገ!!

በተለያየ ዘርፍ ለተሰማሩ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የቴክኖሎጂ ሽግግር ተደረገ፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና የኮሌጁ ዲኖች በተገኙበት 15 ከሚሆኑ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ባለቤቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

የመድረኩ መሰረታዊ ዓላማ በኮሌጁ የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን ለማሸጋገር እና በተቋሙ የሚገኙ የተለያዩ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን ተጠቅሞ አዳዲስ ምርቶችን በጋራ ለማምረት በሚቻልበት ሂደት ላይ ምክክር ለማድረግ ነው፡፡

የኢንዱስትሪዎቹ ባለቤቶችም የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን እና በኮሌጁ ያሉ ማሽኖችን ጎብኝተው ቴክኖሎጆዎችን አሸጋግረው ለማብዛት እንዲሁም ማሽነሪዎችን በመጠቀም በጋራ የማልማት ስራ ለማከናወን መግባባት ተችሏል፡፡

የተቋሙ ስልጠናዎች የገበያውን ቅበላ መሰረት ያደረገ እንዲሆኑ ለማስቻል በአጫጭርም ሆነ በመደበኛ መርሃ ግብሮች የሚሰጡ ስልጠናዎች በጋራ እየተገመገሙ መሰጠት እንዳለባቸው ውይይት ተደርጓል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"