General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ማክሰኞ፡- ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት የግማሽ ዓመቱን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የኮሌጁ ዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ለታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት መረጃ መሰረት በግማሽ ዓመቱ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር፣ የተቋሙን መሰረተ ልማት ከማስተካከል አኳያ እና ሁሉም አካል በየዘርፉ ተነሳሽነት እና ቅንጅት ፈጥሮ ስራዎችን ከመከወን ረገድ እምርታዊ ለውጥ ያሳዬ እና ስኬታማ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በቀሪው ግማሽ ዓመት ከስልጠና ሂደት፣ ከግብዓት አቅርቦት፣ ከውስጥ አሰራር፣ ከተቋማዊ ልማት እና ከማህበራዊ አግልግሎት አንፃር ቢስተካከሉ ያሏቸውን ገንቢ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ቅዳሜ፡- ጥር 17 ቀን 2017 ዓ.ም

     የአይደያ ባንክ /የሀሳብ ማቆር/ ማሰባሰብ ውይይት ተደረገ!!

በኮሌጁ የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት አሰልጣኞች ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም የአይደያ ባንክ ማሰባሰብ ውይይት ተካሄደ፡፡

በስልጠና ዘርፉ ቀጣይ ላይ የሚተገበሩ አዳዲስ ሀሳቦችን በማሰባሰብና ወደ ተግባር በመቀየር ተቋሙ የሚጠበቅበትን ተከታታይ ለውጥ የማምጣት ኃላፊነት እንዲወጡ ለማድረግ የተካሄደ ሲሆን መድረኩን የመሩት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው፡፡

ከዚህ በፊት በኮሌጁ ላሉና በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ አንዳንድ ቢሮች የዕድሳትና የማዘን ስራዎችን በመስራት ረገድ የዲፓርትመንቱ አሰልጣኞች ሚና የላቀ መሆኑ ተገልፆ ቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲሰራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ በርካታ ተቋማት በኮሌጁ ያለውን እምርታዊ ለውጥ ልምድ ለመውሰድ የሚመጡት ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አሻራ ያረፈበት ስኬት ሲሆን ወደ ፊትም የተሰበሰቡ ሀሳቦች በጥራት እንደሚተገበሩ እንተጋለን ተብሏል፡፡

የውይይት መድረኩ የተካሄደው በአስደማሚ ሁኔታ በታደሰው የኮንፈረስ ክፍል ሲሆን የዲን ቢሮ ጽ/ቤትን ጨምሮ የኮንፈረስ ሩሙ ውበትን እንዲጎናፀፍ ያደረጉት የኮንስትራክሽን፣ የውድ ወርክ፣ የኤሌክትሪክሲቲ፣ የጋርመንት እና ሌሎች ዘርፍ አሰልጣኞች የየድርሻቸውን በየሙያቸው ማበርከታቸው ታውቋል፡፡   

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ቅዳሜ፡- የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

ኮሌጁ የሰራተኞች የአንድነት ቀን በዓል አከበረ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰራተኞች የአንድነት ቀን /Get together/ በዓልን ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም በእንጦጦ ፓርክ ፍሬሽ ኮርነር ኪችን አከበረ።

በዕለቱ የኮሌጅ ሰራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የጋራ ማዕድ መካፈል መርሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን በኮሌጁ ዲን በአቶ መለሰ ይግዛው አማካኝነት ዝግጅቱን በማስመልከት መልዕክት ተላልፏል። የኮሌጁ ዲን በመልዕክታቸው <<የዛሬው ዝግጅት ተቋማችን ሁሉን አቀፍ ስኬት እንዲጎናጸፍ የሁሉም ሰራተኛ አበርክቶ የጎላ በመሆኑ ስላደረጋቸሁት ሁሉ ለማመስገን የተዘጋጀ ሲሆን ቀጣይም ዊንጌትን በጋራ ስኬቱን ለማሰቀጠል ቃል የምንገባበት ነው>> ብለዋል።

በዝግጅቱ የተለያየ ዓይነት የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን በኮሌጁ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና አሁን ላይ በጡረታ ለተሰናበቱ ባለውለታዎች፣ በኮሌጁ አመራር ለነበሩና በመሪነት ወደ ሌላ ተቋም ለተዛወሩ፣ በ2016 ዓ.ም ምርጥ ቴክኖሎጂ ለሰሩ አሰልጣኞች፣ በክህሎት ውድድር አሸናፊ ለነበሩ አሰልጣኞች እንዲሁም ችግር ፈቺ ጥናት እና ምርምር ላደረጉ አሰልጣኞች የሰርተፊኬት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዕለቱ በዝግጅቱ ላይ የታደሙት የኮሌጁ ሰራተኞች በፕሮግራሙ መደሰታቸውን ገልጸው የዚህ ዓይነት መርሃ ግብር ከተዝናኖት ባሻገር የስራና የእርስ በእርስ ማህበራዊ ትስስርን ያጠናክራል ብለዋል።

በመጨረሻም የጋራ ማዕድ መርሃ ግብሩ ዝግጅት መስተንግዶ ተከናውኖ ልዩ ልዩ ሽልማት እና አዝናኝ ጨዋታ መርሃ ግብር ተደርጎ የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆናል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት»
ማክሰኞ:- የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ∙ም

    #የሰልጣኞች #ምዝገባ #ማስታወቂያ

የ2017 በጀት ዓመት የሁለተኛው መንፈቀ ዓመት ስልጠና ምዝገባ ከየካቲት 17 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን ስልጠና የሚጀምረው የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ነው።

ምዝገባው የ3ቱም መርሃግብር /የቀን፣ የማታ የቅዳሜ እና እሁድ ነባርና አዲስ መደበኛ ሁሉንም ሰልጣኞች ይመለከታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን አያይዘናል።
Forwarded from FDRE TVT Institute
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የአመራሮች ካውንስል የመጀመሪያውን መደበኛ ጉባዔ ማካሄድ ጀመረ፡፡
የካቲት 07/2017 ዓ.ም**

የኢትዮጵያን የክህሎት ልማትን በማሳደግ ለአገር እድገት ጠቃሚ ሚና እንዲጫወት የተቋቋመው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የአመራሮች ካውንስል የመጀመሪያውን መደበኛ ጉባዔ በቢሾፍቱ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመክፈቻው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በበጀት ዓመቱ እያሳካ ባላቸው ስራዎች የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡


በአገራችን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከተለመደ አሠራር የተሻለ ለውጥ ያመጡበት እንደነበር የገለጹት ክብርት ሚኒስትሯ እነዚህ እየታዩ ያሉ ውጤታማ ስራዎች ባህል እንዲሆኑ በማድረግ ወደ ላቀ የስኬት ምእራፍ ለመሸጋገር የመሪዎች ካውንስል ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር አያይዘውም ዓመተ-ማጽናት ተብሎ በተሠየመው ዓመት የሚካሄድ የመጀመሪያ ጉባኤ በመሆኑ ድርብ ትርጉም እንዳለው ተናግረዋል።


የሚኒስቴሩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) በበኩላቸው ይህ ካውንስል ተቋማት በራሳቸው የሚመካከሩበት ለውጥ የሚያመጣ ሐሳብ የሚያፈልቁበት መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል።

የካውንስሉ ውይይቶች ተቋማት ልምድ በመለዋወጥ በተቋማት መካከል የአፈጻጸም መቀራረብን የሚያመጡበት ፤ የዘርፉን ገጽታ ግንባታ የሚያጠናክሩበት እና ተደማጭነታቸውን የሚያስዱጉ ሃሳቦችን የሚያፈልቁበት ጉባኤ ይሆናልም ብለዋል።


የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አመራሮች ምክርቤት ከተቋቋመ ጀምሮ ሰነድ በማዘጋጀት፣ በቀጠናዊ ትስስር የቴክኒክና ሙያ ደንብ እንዲካተት በማድረግ፣ በኮሌጆች መካከል የልምድና ሀብት ልውውጥ በማድረግ፣ ለምክር ቤቱ ምቹ መደላድል የመፍጠር ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን የየገለጹት ደግሞ የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አቶ መለስ ይግዛው ናቸው፡፡


የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩቱ ካውንስሉን ከመመስረት ጀምሮ ጉባኤውን ከማካሄድ አኳያ ቁልፍ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በጉባኤው ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድርና ም/ዋና ዳይሬክተሮችን ጨምሮ የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡

ዌብሳይት http://www.ftveti.edu.et/
ፌስቡክ https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
ቴሌግራም https://t.me/fdretvtinstitute
ቲክቶክ www.tiktok.com/@fdretvtistitute