ሰኞ፡- ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም
በኮሌጁ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ!!
ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ምክኒያት በማድረግ እንደ ተቋም ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ፡፡
በዓለም ለ21ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የፀረ ሙስና ቀን በኮሌጁ የስነምግባር እና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት "ወጣቶችን ያማከለ የፀረሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል" በሚል መሪ ሀሳብ የኮሌጁ ሰራተኞችና ሰልጣኞች በተገኙበት ተከብሯል።
በዓሉ በፀረ ሙስና ትግሉ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን ለማስቀጠል፣ የትውልድ ስነ ምግባር ግንባታን ለማጠናከር፣ የፀረ ሙስና ትግሉን ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ታቅዶ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሙስና በስነ ምግባር ውድቀት፣ በቢሮክራሲ መብዛት፣ በተጠያቂነት መጓደል፣ በዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማነስ፣ ባልተማከለ የአሰራር ስርዓት እና መሰል መንስኤዎች የሚከሰት ሲሆን አፈፃፀሙ በጊዜ ሂደት እየሰፋ እና እየረቀቀ በመምጣቱ የሀገርን ሀብት ከዚህ አስከፊ ጥፋት ለመታደግ ሁሉም አካላት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ተብሏል፡፡
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Pastry &Bakery school@Wingate
አርብ:- ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም
በድጋሜ የተለጠፈ ማስታወቂያ
ለ2017 ዓ.ም አዲስ ተመዝጋቢዎች
በኮሌጁ የ2017 አዲስ application form እስከ 22/02/2017 ዓ.ም ሞልታችሁ ያመለከታችሁ ሰልጣኞች አሁን ላይ የማጣራት (screening) ተሰርቶ ከ1 እስከ 3 ከመረጣቸኋቸው ሙያዎች ውስጥ የመጀመሪያ ምርጫችሁ message ደርሷችኋዋል።
በቅድምያ Registration ከመጀመራችሁ በፊት ይህንን ያዘጋጁ;-
1.ከ8ኛ -12ኛ ክፍል ያለውን ዶክሜንት scan (photo) አርጋችሁ መያዝ
2.ክፍያ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ scan (photo) አርጋችሁ መያዝ
ከዚያም በኮሌጁ Registration website; https://gwptc.aatvetb.edu.et/ በመግባት registration form የሚለውን በመጫን Registration እንድታከናውኑ እያሳወቅን ፎርሙ ላይ Year of commencement የሚልበት 1ኛ ክፍል የገባችሁበትን ዓመተ ምህረት Payement method በሚልበት ደግሞ offline በማለት ምዝገባቹን እንታጠናቅቁ እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረዳት ዌብሳይቱ ላይ Registration guide የሚለውን ይመልከቱ
ከ22/2/2017 ዓ.ም በኋላ የተመዘገባችሁ screening እስኪሰራ ድረስ በትዕግስት ጠብቁ

ሐሙስ፡- ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም
#የብሔር_ብሔረሰቦች_ቀን_በኮሌጁ_ተከበረ!!
19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል በኮሌጁ ተከበረ።
የኮሌጁ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች በተገኙበት 19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዛሬው ዕለት በኮሌጁ በድምቀት የተከበረ ሲሆን በመድረኩ ላይ ልዩ ልዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ስለሕብረ ብሔራዊ ሥርዓታችንና እያጋጠሙት ስላሉት ተግዳሮቶች እንዲሁም የመፍትሔ ሀሳቦች የተካተቱበት ሰነድ የቀረበ ሲሆን ዓላማውም አገራዊ መግባባትን በመፍጠር ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር ታቅዶ መሆኑን ሰምተናል።
ከዚህ ባሻገር ስነ ጽሑፍና ሙዚቃ በሰልጣኞች እንዲሁም የሰርከስ ትርኢት በሰርከስ ዊንጌት አባላት ቀርቧል።
የበዓሉ ዝግጅት በድምቀት እንዲከበር በማድረግ ረገድ የኮሌጁ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እና የሰልጣኞች መማክርት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

አርብ፡- ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም
#ኮሌጁ_በ13ኛው_ዓለም_አቀፍ_የጥራት_ቀን_ኤግዚቢሽን_ላይ_ተሳተፈ!!
ኮሌጁ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የጥራት ቀን ምክንያት በማድረግ መገናኛ አምቼ አካባቢ በሚገኘው የጥራት መንደር ግቢ ውስጥ ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርት ጥራት እና የሥራ አመራር ሥርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰጣቸው የግልና የመንግስት ድርጅቶች በተሳተፉበት ዓለም አቀፉ የጥራት ቀን ላይ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም የሚሰጠውን አገልግሎት በኤግዚቢሽኑ ላይ እያስተዋወቀ ይገኛል።
ኮሌጁ በጥራት መንደር ኢግዚቢሽን ላይ መገኘቱ ኢግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች እና ጎብኝዎች አብረውት እንዲሰሩ የመተዋወቅ ዕድል ይፈጥርለታል ተብሏል።
ኤግዚቢሽኑ “ጥራት፡ መስፈርቶችን ከማሟላት ወደ ላቀ የአፈጻጸም ብቃት” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።
በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርት ጥራት እና የሥራ አመራር ሥርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያገኙ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ይህ ኤግዚቢሽን ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን ከህዳር 26-28/2017 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚከበር ታውቋል።

በፋይናንስ፣ በጀት እና ንብረት አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!!
በፋይናንስ፣ በጀት እና ንብረት አጠቃቀም ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች ለኮሌጁ ሰራተኞች ተሰጠ፡፡
በዚህም የንብረትና ጠቅላላ አገልገሎት፣ የመንግስት ግዢ አስተዳደር፣ የፋይናንስ፣ የውስጥ ኦዲት፣ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ፣ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች ባለሙያዎች እና የወርክ ሾፕ ቴክኒሻኖች እንዲሁም ለእነዚህ ዘርፎች አጋዥ እንዲሆኑ የተዋቀሩ ልዩ ልዩ የኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ያሳተፈ የ10 ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን ያዘጋጀውና በኃላፊነት ያስተባበረው የኮሌጁ የውስጥ የኦዲት ዳይሬክቶሬት ሲሆን ዳይሬክቶሬቱ በሚያደርገው የውስጥ ኦዲት ክትትልና ድጋፍ አማካኝነት የታዩ አንዳንድ ግድፈቶችን ለማረምና የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ታቅዶ መሆኑ ተገልጿል።
ስልጠናው በፋይናንስ መመሪያዎች አፈጻጸምና በመዋቅራዊ አሰራር ሂደት ዙሪያ ንድፈ ሃሳባዊ እና ተግባራዊ ልምምድ በማድረግ የተሰጠ ሲሆን ተቋማዊ የሃብት ብክነትና የአሰራር ጥሰት እንዳይፈጠር ያግዛል መባሉንም ሰምተናል።
ስልጠናው በመሰረታዊነት ያተኮረባቸው በሂሳብ አያያዝ፣ በግዢ ስርዓት አፈጻጸም፣ በንብረት አያያዝና አጠቃቀም እና በኦዲት አሰራር ስርዓት እንዲሁም በበጀት ክትትልና አጠቃቀም ዙሪያ ነው።
የስልጠና አቀራረብም ሆነ ይዘት በጣም ጥሩ እንደነበር ተሳታፊዎች ገልጸው የዚህ አይነት ስልጠና ቀጣይነት ባለው ጊዜ ከተሰጠ በአሰራር ላይ የሚገጥሙ ችግሮችን በማስቀረት እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ረገድ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነውም ተብሏል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››