ሐሙስ፡- ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም
#የብሔር_ብሔረሰቦች_ቀን_በኮሌጁ_ተከበረ!!
19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል በኮሌጁ ተከበረ።
የኮሌጁ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች በተገኙበት 19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዛሬው ዕለት በኮሌጁ በድምቀት የተከበረ ሲሆን በመድረኩ ላይ ልዩ ልዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ስለሕብረ ብሔራዊ ሥርዓታችንና እያጋጠሙት ስላሉት ተግዳሮቶች እንዲሁም የመፍትሔ ሀሳቦች የተካተቱበት ሰነድ የቀረበ ሲሆን ዓላማውም አገራዊ መግባባትን በመፍጠር ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር ታቅዶ መሆኑን ሰምተናል።
ከዚህ ባሻገር ስነ ጽሑፍና ሙዚቃ በሰልጣኞች እንዲሁም የሰርከስ ትርኢት በሰርከስ ዊንጌት አባላት ቀርቧል።
የበዓሉ ዝግጅት በድምቀት እንዲከበር በማድረግ ረገድ የኮሌጁ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እና የሰልጣኞች መማክርት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"