አርብ፡- ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም
#ኮሌጁ_በ13ኛው_ዓለም_አቀፍ_የጥራት_ቀን_ኤግዚቢሽን_ላይ_ተሳተፈ!!
ኮሌጁ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የጥራት ቀን ምክንያት በማድረግ መገናኛ አምቼ አካባቢ በሚገኘው የጥራት መንደር ግቢ ውስጥ ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርት ጥራት እና የሥራ አመራር ሥርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰጣቸው የግልና የመንግስት ድርጅቶች በተሳተፉበት ዓለም አቀፉ የጥራት ቀን ላይ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም የሚሰጠውን አገልግሎት በኤግዚቢሽኑ ላይ እያስተዋወቀ ይገኛል።
ኮሌጁ በጥራት መንደር ኢግዚቢሽን ላይ መገኘቱ ኢግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች እና ጎብኝዎች አብረውት እንዲሰሩ የመተዋወቅ ዕድል ይፈጥርለታል ተብሏል።
ኤግዚቢሽኑ “ጥራት፡ መስፈርቶችን ከማሟላት ወደ ላቀ የአፈጻጸም ብቃት” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።
በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርት ጥራት እና የሥራ አመራር ሥርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያገኙ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ይህ ኤግዚቢሽን ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን ከህዳር 26-28/2017 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚከበር ታውቋል።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"