General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ፡- ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

ኮሌጁ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወር /AMN/ ጋር በትብብር ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ!!


የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ /AMN/ በትብብር ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

የሚዲያው የስራ ኃላፊዎች ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ ተገኝተው ተቋማዊ ጉብኝት እና የስራ ውይይት ካደረጉ በኋላ በቀጣይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ችለዋል፡፡
ኮሌጁ ከተለያዩ ሚዲዎች ጋር አብሮ ሲሰራ ቢቆይም ከሚዲያ አንፃር የስምምነት ሰነድ ተፈራርሞ በጋራ ለመስራት በዚህ መልኩ ስምምነት ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያ ነው ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ #መለስ ይግዛው ናቸው። ዲን አክለውም ከበርካታ አገር አቀፍና ዓለም ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ ያለ ሲሆን አገልግሎቶቻችን ተደራሽ ለማድረግ ከእናንተና መሰል መገናኛ ብዙሃን ጋር ተባብረን መስራት ግድ ይለናል ብለዋል።

በሌላ በኩል የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የገበያ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ #መሀመድ ናስር በበኩላቸው ስምምነቱ የብዙሃን ድምጽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በስሩ ለሚገኙ ባለሙያዎች የቴክኒክ እና ሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችለዋል ብለዋል።

ሚዲያ አንጋፋ በሆነው በዚህ ኮሌጅ የሚከናወኑ የልማትና የፈጠራ ስራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በዜናና በዶክመንተሪ ሽፋን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
አርብ፡- ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮሌጁ የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!


የኮሌጁ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

በዕለቱ በዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች በኮሌጁ የተከናወኑ የዝግጅት ምዕራፍ ሪፖርቶች ቀርበው ሀሳብ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት መረጃ መሰረት በሩብ ዓመቱ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር፣ የተቋሙን መሰረተ ልማት ከማስተካከል አኳያ፣ ነባርና አዳዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ በአግባቡ ከማሰልጠን አንፃር እና ተጓዳኝ ስራዎችን ከመከወን ረገድ ያሉ እምርታዊ ለውጦች እና የነበሩ ክፍተቶች ለውይይት ቀርበው አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በእቅድ አፈፃፀም ግምገማው ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በኮሌጁ ያሉ ጥንካሬ እና ክፍተቶችን ›አንስተው መድረኩ በቀጣይ የስራ አቅም እና ተነሳሽነት እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ለኮሌጁ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች

በኮሌጁ ግቢ ውስጥ ከ14/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ የብሔራዊ መታወቅያ ምዝገባ እየተከናወነ ስለሆነ በፍጥነት በመመዝገብ የእድሉ  ተጠቃሚ እንድትሆኑ።

ቦታ በኮሌጁ ግቢ ፔፕሲ ሱቅ አጠገብ።