ሐሙስ፡- ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም
#የብሔር_ብሔረሰቦች_ቀን_በኮሌጁ_ተከበረ!!
19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል በኮሌጁ ተከበረ።
የኮሌጁ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች በተገኙበት 19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዛሬው ዕለት በኮሌጁ በድምቀት የተከበረ ሲሆን በመድረኩ ላይ ልዩ ልዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ስለሕብረ ብሔራዊ ሥርዓታችንና እያጋጠሙት ስላሉት ተግዳሮቶች እንዲሁም የመፍትሔ ሀሳቦች የተካተቱበት ሰነድ የቀረበ ሲሆን ዓላማውም አገራዊ መግባባትን በመፍጠር ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር ታቅዶ መሆኑን ሰምተናል።
ከዚህ ባሻገር ስነ ጽሑፍና ሙዚቃ በሰልጣኞች እንዲሁም የሰርከስ ትርኢት በሰርከስ ዊንጌት አባላት ቀርቧል።
የበዓሉ ዝግጅት በድምቀት እንዲከበር በማድረግ ረገድ የኮሌጁ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እና የሰልጣኞች መማክርት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

አርብ፡- ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም
#ኮሌጁ_በ13ኛው_ዓለም_አቀፍ_የጥራት_ቀን_ኤግዚቢሽን_ላይ_ተሳተፈ!!
ኮሌጁ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የጥራት ቀን ምክንያት በማድረግ መገናኛ አምቼ አካባቢ በሚገኘው የጥራት መንደር ግቢ ውስጥ ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርት ጥራት እና የሥራ አመራር ሥርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰጣቸው የግልና የመንግስት ድርጅቶች በተሳተፉበት ዓለም አቀፉ የጥራት ቀን ላይ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም የሚሰጠውን አገልግሎት በኤግዚቢሽኑ ላይ እያስተዋወቀ ይገኛል።
ኮሌጁ በጥራት መንደር ኢግዚቢሽን ላይ መገኘቱ ኢግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች እና ጎብኝዎች አብረውት እንዲሰሩ የመተዋወቅ ዕድል ይፈጥርለታል ተብሏል።
ኤግዚቢሽኑ “ጥራት፡ መስፈርቶችን ከማሟላት ወደ ላቀ የአፈጻጸም ብቃት” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።
በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርት ጥራት እና የሥራ አመራር ሥርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያገኙ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ይህ ኤግዚቢሽን ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን ከህዳር 26-28/2017 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚከበር ታውቋል።

በፋይናንስ፣ በጀት እና ንብረት አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!!
በፋይናንስ፣ በጀት እና ንብረት አጠቃቀም ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች ለኮሌጁ ሰራተኞች ተሰጠ፡፡
በዚህም የንብረትና ጠቅላላ አገልገሎት፣ የመንግስት ግዢ አስተዳደር፣ የፋይናንስ፣ የውስጥ ኦዲት፣ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ፣ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች ባለሙያዎች እና የወርክ ሾፕ ቴክኒሻኖች እንዲሁም ለእነዚህ ዘርፎች አጋዥ እንዲሆኑ የተዋቀሩ ልዩ ልዩ የኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ያሳተፈ የ10 ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን ያዘጋጀውና በኃላፊነት ያስተባበረው የኮሌጁ የውስጥ የኦዲት ዳይሬክቶሬት ሲሆን ዳይሬክቶሬቱ በሚያደርገው የውስጥ ኦዲት ክትትልና ድጋፍ አማካኝነት የታዩ አንዳንድ ግድፈቶችን ለማረምና የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ታቅዶ መሆኑ ተገልጿል።
ስልጠናው በፋይናንስ መመሪያዎች አፈጻጸምና በመዋቅራዊ አሰራር ሂደት ዙሪያ ንድፈ ሃሳባዊ እና ተግባራዊ ልምምድ በማድረግ የተሰጠ ሲሆን ተቋማዊ የሃብት ብክነትና የአሰራር ጥሰት እንዳይፈጠር ያግዛል መባሉንም ሰምተናል።
ስልጠናው በመሰረታዊነት ያተኮረባቸው በሂሳብ አያያዝ፣ በግዢ ስርዓት አፈጻጸም፣ በንብረት አያያዝና አጠቃቀም እና በኦዲት አሰራር ስርዓት እንዲሁም በበጀት ክትትልና አጠቃቀም ዙሪያ ነው።
የስልጠና አቀራረብም ሆነ ይዘት በጣም ጥሩ እንደነበር ተሳታፊዎች ገልጸው የዚህ አይነት ስልጠና ቀጣይነት ባለው ጊዜ ከተሰጠ በአሰራር ላይ የሚገጥሙ ችግሮችን በማስቀረት እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ረገድ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነውም ተብሏል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

https://t.me/gwstudent
ማስታወቂያ
ለኮሌጁ ሰልጣኞች
ከኮሌጁ ይህ ዋናው የቴሌግራም ገጽ በተጨማሪ በሰልጣኝ ካውንስል የሚተላለፉ ሰልጣኝ ነክ መረጃዎችን በዚህ ተጨማሪ ገጽ መከታተል ትችላላችሁ።

Telegram
General Wingate Students Channel
ይህ የጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተማሪ ቻናል ነው። @Gw2016bot
This is the Student Channel of General Wingate Polytechnic College.