ረቡዕ፡- ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም
የጥንቃቄ መልዕክት ማስታወቂያ!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመዲናይቱ ነዋሪዎች፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ለሚገኙ ወጣቶችና ተማሪዎች ስለ አዋኪ ጉዳዮች ምንነት፣ አጋላጭ ምክኒያቶች፣ የሚያደርሱት ጉዳቶች እና የተጠያቂነት ሂደቶች ዙሪያ ትኩረት ያደረጉ ይዘቶችን ያካተተ የድምጽ መልዕክት ስለላከ ለጥንቃቄ ይረዳችሁ ዘንድ እንደሚከተለው አድርሰንላችኋል።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

አርብ:- ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ∙ም
ፋዊ ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ሰልጣኞችና ቤተሰቦቻቸው ስለ ፕሮግራሙ በኮሌጁ ገለፃ ሰጠ!!
የአፍሪካ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች ፎረም /FAWE/ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ሰልጣኞችና ቤተሰቦቻቸው ስለፕሮግራሙ ይዘት ግንዛቤ ሰጠ።
በዕለቱ የፋዊ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ እና የቦርድ ሰብሳቢ፣ የድርጅቱ ሰራተኞች፣ የኮሌጁ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ፋዌ ኢትዮጵያ ቻፕተር እና ፋዌ አፍሪካ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር የሃርድ ስኪል ስልጠና ለሚከታተሉ ሰልጣኞች የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲትሆኑ አድርጓል፡፡
እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው ጀነራል ዊንጌት እና አዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ሲሆኑ በሁለቱ ተቋማት እየሰለጠኑ ለሚገኙ ሰልጣኞች ስለ ድርጅቱ ምንነት፣ የሚሰጣቸው ድጋፍ ዓይነቶች እና ከሰልጣኞችና ቤተሰቦቻቸው የሚጠበቅ ትጋት ምን እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።
ፋዊ በምዕራፍ ሁለት ፕሮግራሙ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና /TVET/ ላይ ትኩረት አድርጎ ከ15 - 25 የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው።
ፕሮግራሙ 80 ከመቶ ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ5 እስከ 10 ፐርሰንት ለአካል ጉዳተኛ ከ10 እስከ 15 ፐርሰንቱ ደግሞ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ዜጎች ዕድል መስጠቱ ታውቋል፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

አርብ፡- ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ለሚሰጡ አሰልጣኛኞች ስልጠና ተሰጠ!!
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት ለሚሰጡ የኮሌጁ አሰልጣኛኞች የ5 ቀናት ስልጠና ተሰጠ::
በኮሌጁ የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ በኩል 40 ለሚሆኑ አሰልጣኞች ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ትግበራ ጋር በተያያዘ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናው ከህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን ይዘቱም ድጋፍ ከሚሰጥባቸው ማዕቀፎች መካከል በኢንተርፕርነርና በካይዘን ትግበራ ዙሪያ መሆኑን ሰምተናል።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

ማክሰኞ:- ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም
በስነ ምግባርና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!!
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በመጡ ባለሙያዎች በስነ ምግባርና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ለኮሌጁ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናው ትናንት ጀምሮ ሁለት ቀናት የፈጀ ሲሆን በስነ ምግባርና በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በሙስና መከላከል ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ነው።
የስልጠናው ዓላማ ከሙስናና ከብልሹ ተግባር ነጻ የሆነ ዜጋ መፍጠር እንዲሁም መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ከብልሹ አሰራር የፀዳ ፍትሀዊ አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች በእኩል ደረጃ ለመስጠት ነው ተብሏል።

ሁለተኛው የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳው ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት ጀመረ!!
በኮሌጁ ዋና በር መግቢያ ላይ የሚገኘውና በተለምዶ ትንሹ የእግር ኳስ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ደረጃውን የጠበቀ አራት ዘመናዊ የእግር ኳስ ማዘውተሪያ ሜዳ ለማሰራት ታቅዶ ወደ ስራ ከተገባ በኋላ የሁለተኛዋው ሜዳ ስራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
የማህበረሰብ የግል አጋርነት ተሳትፎ /Public Private Partnership participation/ በሚለው መርህ መሰረት ፉት ፒች ኃላ/የተ/የግ ድርጅት በተሰኘ የግል ኩባንያ ግንባታው እየተሰራ የሚገኘው የእግር ኳስ መለማመጃ ሜዳ አሁን ላይ ከ4ቱ ውስጥ 2ቱ ተጠናቀው ወደ አገልግሎት ሲገቡ ሁለቱ ደግሞ እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
በትንሹ ወደ 20 ሚሊዮን ብር ወጪ ይጠይቃል የተባለለትን ይህን ፕሮጀክት ኮሌጁ የግል አልሚዎችን በመጋበዝ መተግበሩ በማህበረስብ አገልገሎት ዘርፍ የአካባቢው ወጣቶች በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ፣ የኮሌጁ ተቋማዊ ገጽታ ማራኪ እንዲሆን፣ የኮሌጁ የውስጥ ገቢ እንዲያድግ፣ ለተለያዩ የጤና ስፖርት ቡድኖችና ለኮሌጁ ማህበረሰብ ስፖርታዊ እንቀስቃሴ እንዲያደርጉ ያገለግላል ተብሏል፡፡