General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ:- ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

ኮሌጁ በመደበኛ ኢንስፔክሽን ምዘና እንደ ከተማ አንደኛ ወጣ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተደረገው መደበኛ የኢንስፔክሽን ምዘና ውጤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ አንደኛ ደረጃ ወጣ፡፡

ምዘናውን ያካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ባደረገው የተቋማት ብቃት ልኬት መሰረት ነው፡፡

በዚህም ኮሌጁ ባለው የስልጠና ወርክ ሾፕ እና የሰው ኃይል ግብዓት መጠንና ጥራት፣ በስልጠና ሂደቱ ያለው አተገባበር እና በተቋማዊ አፈፃፀም ብቃት፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ ለመሆን እያደረገው ያለው ትጋት እንዲሁም በተቋማዊ አመራር እና አደረጃጀት ስርዓት ተመዝኖ የስታንዳርዱን ከፍተኛ ውጤት በማምጣቱ ከባለ ስልጣን መስሪያ ቤቱ የዋንጫ እና የሰርተፊኬት ሸልማት ተበርክቶለታል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ለመሆን ራዕይን ሰንቆ በስኬት እየተጓዘ የሚገኘው ኮሌጃችን አሁን ላይ በሀገሪቱ ለሚገኙ አቻ ተቋማት በብዙ አዳዲስ ተግባራቱ አርአያ ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ለዚህ ዘርፈ ብዙ ውጤት መገኘት የእያንዳንዱ የኮሌጁ ማህበረሰብ ትጋት ድምር ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ታሪካዊና ቀዳማዊ በሆነው የብቁ ዜጎች ማፍሪያ ተቋም ቀጣይም አሻራችሁን በማይደበዝዝ ቀለም በማስቀመጥ አበርክቷችሁን አብልጣችሁ እንዲትቀጥሉበት እንገልጻለን፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ማክሰኞ:- ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ∙ም

በኮሌጁ የተሰሩ ልዩ ልዩ መሰረተ ልማቶች ተመረቁ!!

በኮሌጁ የተሰሩ ልዩ ልዩ መሰረተ ልማቶች በክቡር አቶ ጥራቱ በየነ አማካኝነት ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ∙ም ተመረቁ፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ በሆኑት ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የተመራ ልዑካን ቡድን በኮሌጁ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በተቋሙ ተሰርተው የተጠናቀቁ የማሰልጠኛ እና የውስጥ ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።

በዕለቱ የቢሮው የስራ ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተሞችና የወረዳዎች ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች እና በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዋና ዲኖች ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡

የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሪፎርም ስራዎችን በመጀመር እንዲሁም የISO 9001፡2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ስራ አመራር ባለቤት በመሆን ፈር ቀዳጅ ነው ያሉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ናቸው፡፡ ኃላፊው አክለውም ይህ እንዲሳካ ላደረጉ ለኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት እና አጠቃላይ ለኮሌጁ ማህበረሰብ ምስጋና ይገባቸዋል፤ ሌሎች ተቋማትም ይህንን አርአያነት ወስደው ተቋማቸውን ምቹና ማራኪ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት በተካሄደው መድረክ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች የርክክብ ስነ- ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በዚህም ለተቋማዊ ሪፎርም ይረዳ ዘንድ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የተገዙ እና 47 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ላፕቶፓች፣ ደስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች እና ፕሮጀክተሮች ለተወሰኑ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ለሚገኙ የስራና ክህሎት ጽ/ቤቶች እና ኮሌጆች ተበርክቷል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
የስልጠና ማስታወቂያ
          
  ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የቀረበ የስልጠና ገጸ በረከት 

አጠቃላይ ለኮሌጁ ማህበረሰብ እና ለማህበራዊ ሚዲያችን ተከታታዮች በሙሉ ይህን የኮደርስ ስልጠና መሳተፍ እንደምትችሉ እያሳወቅን የኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠናን ሲያጠናቅቁ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት ባለቤት እንደሚሆኑም ስንነግሮት በሙሉ እምነት ነው::

ስልጠናው የሚሰጠው በኦን ላይን /online/ ሲሆን ስልጠናውን ለመከታተል ኢተርኔት ባለበት ቦታ በላፕቶብ ወይም በእጅ ስልክ /ሞባይል/ በመጠቀም መውሰድ እንደምትችሉ ስናበስር ለእናንተ ቅርብ ሆነን ነው፡፡

የሚሰጡ የስልጠና ዓይነቶች:-
1.ዌብ ፕሮግራሚንግ /web programming/
2.ሞባይል ፕሮግራሚንግ /Mobile programming/
3.ዳታ ሳይንስ /Data science/
4. ሰው ሰራሽ አስተውሎት / Artificial Intelligence/ or AI

ማሳሰቢያ:-  ኦንላይን ስትሞሉ #Institution የሚለው ላይ #General_Wingate_Polytechnic_College ብላችሁ መሙላት ይጠበቅባችኋል።
ለስልጠናው የተመዘገባችሁ ሙሉ ስማችሁንና የተመዘገባችሁበትን ሙያ ለአይሲቲ ዲፓርትመንት ኃላፊ ቢሮ እንድታሳውቁ
ትምህርቱ እድሜ፣ ፆታ እና ቦታ አይገድበውም:: 

    📍 በዚህ ሊንክ   https://ethiocoders.et/

መረጃው የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሲሆን ለተጨማሪ ማብራሪያ የኮሌጁን አይሲቲ /ICT/ ዲፓርትመንት ኃላፊ ቢሮ መጠየቅ ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡
አርብ:- ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ∙ም

#የሺያጭ #ማስታወቂያ

ሀ-ብዬ የቆዳ ምርት ውጤቶች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት ለኮሌጁ ማህበረሰብ በሙሉ ከወዲሁ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ድርጅቱ በዓሉን ምክኒያት በማድረግ በጥራትና በውበት የሚያመርታቸውን ፋሽን ጫማዎችና ሌዘር ጃኬቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና በ3 ወር የክፍያ ጊዜ ወስዳችሁ ሽር ብትን በሉ ብሏችኋል፡፡

የሺያጭ ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆ ሲሆን ቦታውም በሰራተኞች ካፍተሪያ አገልግሎት መግቢያ በር አካባቢ ታገኙናለችሁ ኑና መርጣችሁ ሸምቱ ተብላችኋል፡፡

ሀ-ብዬ የቆዳ ምርት ውጤቶች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት