Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የአይቤክስ ባንድ ስቴሪዮ በመሳሪያ የቀነባበረ ሙዚቃ ከ49 አመት በኋል በድጋሚ ለአድማጮች ሊቀርብ ነው ⵑⵑ

#Ethiopia | ከ1968 ዓ.ምቱ የአይቤክስ ባንድ አልበም የሆነውን ስቴሪዮ በመሳሪያ የቀነባበረ ሙዚቃ በሚል የተሰየመውን አልበም በድጋሚ ከ49 አመት በኋላ በድጋሚ ለአድማጮች እንደሚደርስ ሙዚቃዊ አስታውቋል ፡፡

የጆቫኒ ሪኮ እና ሰላም ወልደማርያም ልዩ ስራዎች የሚደመጡበት ይህ አልበም ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያዎች አማካኝነት ለህዝብ ተደራሽ እንደሚሆን ቅዳሜ ገበያ ያገኘችው መረጃ ያሳያል ።

የሙዚቃ አልበሙ ከምድላዬይ፤ መለያየት ሞት ነው ፤ ዘራፌዋ ፤ ሸሞንሟናዬ፤ የዘመድ የባዳ፤ ሀኪም ዘሞሴ፤ የኔ ፍቅር ፤ ስቃይሲ ይካአልዩ ፤ ቱሩምቡሌ ፤ አይ ውበት ፤ አሳ አበላሻለሁ ፤ የኑሮ መጠንሽን የሚሉ ሙዚቃዎች የያዘ እንደሆነ ቅዳሜ ገበያ ካገኘችው መረጃ ተረድታለች ፡፡

Follow us
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #ibex
#ስለቀነኒ ዲያሪ(Diary)

መምህር ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ አበባየሁ ጌታ እናሮ ለጉርሻዎች በውስጥ የተላከው መልእክት እንዲህ ይላል

የወንጀል ምርመራ በተለይም የነፍስ ግድያ ወንጀል ምርመራ እጅግ ውስብስብ እና ቀጥተኛ ማስረጃ በግልጽ ከሌለ እጅግ አዳጋች እና አስቸጋሪ የወንጀል ዓይነት መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች የሚያውቁት ሀቅ ነው ።

በተለይም ሟች በሰው እጅ ወይስ በራስ እጅ ነው ሕይወቱ ያለፈው የሚለው ጥያቄ በብዙ ውስብስብ ምርመራ እንዲሁም ቴክኒክ እና ታክቲክ ማስረጃዎች ታግዞ እና በአግባቡ ተተንትኖ ወደ አንዳች ድምዳሜ የሚያደርሱ መሆኑ እሙን ነው ።

በተያያዘው ጉዳይ #የቀነኒ_ማስታወሻ_ደብተር ነው #የተባለው ወደ ተጠርጣሪው ጠበቃ እጅ እንዴት እጁ ላይ ሊገባ ቻለ?

መቼ እና ለምን?

የብርበራ ትዕዛዝ ሲወጣ በተለይም በእንዲህ ዓይነት የነፍስ ግድያ ወ ራስን ማጥፋት ጉዳይ ላይ ፍንጭ ሊሰጡ የሚችሉ እንደ እነ ስልክ ንግግሮች ፣ የማስታወሻ ደብተር ፣ እንደ እነ የተቀዱ ካሴቶች እና ሌሎች ማስረጃዎች በመርማሪ ፖሊስ እጅ መግባት አልነበረባቸውምን? ወይስ በሰዓቱ ተደብቀዋል?

ጠበቃው በእጄ አለ ያለውንስ ማስታወሻ ደብተር ከየት አገኘው?

እንዳገኘውስ ለምን የምርመራው አካል አላደረገውም? ወይስ ወደ በኋላ ለመከላከያ መልስ ለመጠቀም በማሰብ አቆየው?

እውን የእሷ ማስታወሻ ደብተር ስለመሆኑስ ምን ማረጋገጫ አለ?

ለምንስ በዚህ ምርመራ ወቅት ተነሳ?

በአሁን ሰዓት ወንጀል ፈጽመዋል አልፈጸመም ወይስ ክርክሩ የዋስትና መብት ይጠበቅ ነው?

ፍርድ ቤቱስ በዚህ ማስታወሻ በተባለው ደብተር ጉዳይ ምን ይበይን ይሁን?

* እልፍ ጥያቄዎች
* አንድ እውነት
* ንጹህም አይቀጣ!
* ወንጀለኛም አይለቀቅ

Via Abebayehu Geta Enaro

@waliyaentmt
@waliyaentmt
ኢትዮጵያ የባህል ዕሴቿን እና ኪናዊ ፀጋዎቿን ለብሪክስ አባል ሀገራት ልታስተዋውቅ ነው

#Ethiopia | “የኢትዮጵያ የባህል ድልድይ ህዝብ ለህዝብ ትስስር” በሚል መሪ ቃል ኢትዩጵያ ላይ ያሉ ቱባ ባህላዊ ዕሴቶችን፣ ኪናዊ ፀጋዎችን እንዲሁም የፈጠራ ምርቶችን በመጠቀም ከኢትዩጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች በተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለብሪክስ አባል ሀገራት ለማቅረብ ዝግጅት ጀምራለች፡፡

ኢትዩጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በዲፕሎማሲው መስክ ከምትሰራቸው ስራዎች አንዱ የባህልና የኪነ ጥበብ ዲፕሎማሲ እንደመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ ልክ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይህንን ዝግጂት ለማቅረብም የሚያስችል የውል ስምምነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር ተፈራርሟል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #kamuzukassa
"የተሰበሰበው ገንዘብ ለአርቲስቱ አልተሰጠም" አዘጋጅ ኮሚቴው
"ስሜን ለማጥፋት ነው" ዲጄ ቤቢ

የአርቲስት ዓለማየሁ ደመቀን የ25 ዓመታት የኪነጥበብ ቆይታና አገልግሎት ለማክበርና አርቲስቱን ለማመስገን ዮቶር በሚል ርዕስ ሰኔ 15/2016 ዓ.ም የሙዚቃ ኮንሰርት በማርዮት ሆቴል አዳራሽ መከናወኑ ይታወቃል፡፡

በዝግጅቱ የተገኙ ገቢዎች የስፖንሰርሺፕ ገቢ፣ የቲኬት ገቢና ሌሎችም ገቢዎች ሂሳብ ተሰርቶ ርክክብ ባለመደረጉ በተደጋጋሚ ሂሳብ ተሰርቶ የአርቲስቱ ድርሻ ገቢ እንዲደረግለት ጥያቄ ቢቀርብም በተለያዩ ምክንያቶች ዲጄ ቤቢ መገኘት ባለመቻሉ ጉዳዩ እልባት ማግኘት አልቻለም ሲሉ ኮሚቴዎቹ ቅሬታውን በደብዳቤ ለሚዲያዎች ገልፀው ነበር።

ጉዳዩን አስመልክቶ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ለማጣራት እንደሞከረው ዲጄ ቤቢን አነጋግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል ደብዳቤው ቀድሞ ተልኮልኝ አይቼዋለሁ ያለው ዲጄ ቤቢ እንደአጋጣሚ ሆኖ አሜሪካን ሀገር በላስ ቬጋስ ከተማ በተዘጋጀው የአለም የሬዲዮና ቴሌቪዥን ብሮድካስተሮች ማህበር ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ አሜሪካ ሀገር ሄጃለሁ እሱን አጋጣሚ በመጠቀም "ሸሸ" በማለት ስም ለማጥፋት የተደረገ ስም የማጥፋት ዘመቻ ነው፣ ሙሉ በሙሉ ውሸት ነው! ጉዳዩን ወደ ህግ ወስጄዋለሁ ብሏል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #djbaby #alemayehudemeke
" ልዑል ኮንሰርት ቱር "በ ሶስት ከተሞች የሙዚቃ ድግስ ሊያዘጋጅ ነው!

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በዘመናዊ ሙዚቃ በመጀመሪያ አልበም ከፍተኛ ተወዳጅነት እና ተቀባይነት ያገኘው ልዑል ሲሳይ በፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ እና ሸጋ ኢቬንትስ እና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት ሀገር አቀፍ የሙዚቃ ቱር "የልኡል ሙዚቃ"ቱር በሚል ስያሜ ይከናወናል ተባለ።

ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ "ልዑል'' ሲል በሰየመው የመጀመሪያ አልበሙ ውሰጥ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ስልተ-ምቶችን ጨምሮ ሬጌና ፖፕ ስልቶችን አካቶ መምጣቱ ይታወሳል።

ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ በሚሊኒም አደራሽ የመጀመርያ ኮንሰርቱን ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የፊታችን ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም ቅዳሜ ምሽት በጊዮን ሆቴል ስራዎቹን ከአዲስ ሙዚቃዎች ጋር በማካተት ለየት ባለ አቀራረብ ከአደናቂዎቹ ጋር ለመገናኘት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

በዕለቱ በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙት ስካት ናቲ፣ሃና ግርማ እና ዊሃ በዝግጅቱ ላይ ስራዎቻቸውን በቶራ ባንድ ታጅበዉ ያቀርባሉ፡፡

በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የተዘጋጀው ኮንሰርት እንደተጠናቀቀ በሀዋሳ ግንቦት 2/ 2017 ዓ.ም እንዲሁም በድሬዳዋ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም ሌሎች ድምፃዊያንን በማካተት የኮንሰርት ቱር ይካሄዳል፡፡

አዘጋጆቹ እንደገለጹት ሦስቱም የኮንሰርቶች ላይ በአጠቃላይ ከ 22 ሺህ በላይ ተመልካች ይጠበቃል፡፡

በሶስቱ ኮንሰርቶች ቀድሞ ለሚገዙ ውስን የሚሆኑ ትኬቶችን በ400 ብር መደበኛ 600 በዕለቱ በር ላይ 800 ቪአይፒ 2500 ብር ሲሆን ትኬቱን መግዛት የሚቻለው በቴሌ ብር ብቻ መሆኑ ተነግሯል ::

Follow us on
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ተወዳጇ የ90ዎቹ ድምፃዊ ሃይማኖት ግርማ ''እንዴት ነህ ጅንኑ ?'' የተሰኘ አልበሟን ልታወጣ ነው።

በብዙሃን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑትን የ90ዎች የሙዚቃ ስብስብ ውስጥ ኦማሂሬ፣ባለጋሪው እና የተለያዩ ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ያደረሰችን ሃይማኖት ግርማ አሁን ደሞ ከረጅም ጊዜ በኋላ ግንቦት 15 "እንዴት ነህ ጅንኑ" የተሰኘ 3ኛ አልበሟን እንደምትለቅ አሳውቃለች !

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #haymanot_girma
ድምፃዊ ዘሪቱ ከበደ "ማፅናናትህ" የተሰኘ የመዝሙር አልበም ልታወጣ ነው።

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ እጅግ ተወዳጅነትን ካገኙ እና በድምፅ ብቃቷ ብዙዎች የሚመሰክሩላት ከኤልያስ መልካ ጋር በሰራችው አንድ አልበም ብቻ ዘመን አይሽሬ ድምፃውያን ተርታ ውስጥ የተመደበችው ድምፃዊ ዘሪቱ ከበደ ከዘፈኑ አለም ወጥታ መንፈሳዊ አለም ውስጥ በመቀላቀል ዘማሪ እንደሆነች ይታወቃል። በቅርቡም "ማፅናናትህ" የተሰኘ አዲስ የመዝሙር አልበም እንደምትለቅ አሳውቃለች !

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Zeritu_kebede
ሙዚቀኛው ሞቶ ተገኘ!

#Ethiopia | የቀድሞ ሮሀ ባንድ ሳክስፎኒስቱ በመኖሪያ ቤቱ ሞቶ ተገኘ

ከቀደምት ሮሀ ባንድ አባላት መካከል ተጠቃሹ አርቲስት ስምኦን ሊባኖስ በመኖሪያ ቤቱ ሕይወቱ አልፎ እንደተገኘ ጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ የአርቲስቱን የቀድሞ ስራ ባልደረባና ጓደኛ ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

" ከደቂቃዎች በፊት ጋሽ ዳዊት ይፍሩ እንዲህ አለኝ.. "እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነን። የዛን ዘመን የሮሃ ባንድ ሳክስፎኒስት የቀድሞ የስራ ባልደረባዬና ጓደኛዬ የነበረው አርቲስት ስሞኦን ሊባኖስ ( ዮናስ ደገፉ) ዛሬ ህንድ ኢንባሲ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።
ለምርመራው የአዲስ አበባ ፖሊስ አስክሬኑን ወስዷል"አለኝ።

ግን ሌላው የሚያሳዝነው ቤተሰቦቹን ማግኘት አልተቻለም ። እና ቤተሰቡ ወይም ወዳጆቹ አዲስ አበባ ፖሊስ መጠየቅ ትችላላችሁ። " ሲል መረጃውን አጋርቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
እውቋ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ኬቲ ፔሪ የጠፈር ጉብኝቷን አጠናቃ ተመለሰች

የፖፕ ኮከቧ ኬቲ ፔሪን ያካተተው የብሉ ኦርጂን ኩባንያ የጠፈር ቡድን ሰኞ ማለዳ ወደ ጠፈር ለጉብኝት ተጉዟል።

በረራው በሙሉ የሴቶች ቡድን የተደረገ ሲሆን እንደ ኩባንያው ገለጻ ይህ በረራ ከአውሮፓውያኑ 1963 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች የተደረገ የጠፈር በረራ ሆኗል::

ከታዋቂዋ አቀንቃኝ ኬቲ ፔሪ ጋር፣ የብሉ ኦርጂን ባለቤት የሆነው የጄፍ ቤዞስ እጮኛ ላውረን ሳንቼዝም በጉብኝቱ ውስጥ ተካታለች።

ኬቲ ፔሪ ከብሉ ኦርጂን የጠፈር በረራ አጠናቃ ወደ ምድር እንደተመለሰች ደስታዋን እና ምስጋናዋን ገልጻለች።

ሙዚቀኛዋ ልምዷን "ሕይወትን የሚቀይር" በማለት ስትሰይም በረራው ስለሚሰጠው ጥልቅ የአመለካከት ለውጥ አፅንዖት ሰጥታ ተናግራለች::

"ይሄ ከሁሉ የላቀ መንፈሳዊ ተሞክሮ ነው" በማለት ነው የገለፀችው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #kettyperry