Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
#ስለቀነኒ ዲያሪ(Diary)

መምህር ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ አበባየሁ ጌታ እናሮ ለጉርሻዎች በውስጥ የተላከው መልእክት እንዲህ ይላል

የወንጀል ምርመራ በተለይም የነፍስ ግድያ ወንጀል ምርመራ እጅግ ውስብስብ እና ቀጥተኛ ማስረጃ በግልጽ ከሌለ እጅግ አዳጋች እና አስቸጋሪ የወንጀል ዓይነት መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች የሚያውቁት ሀቅ ነው ።

በተለይም ሟች በሰው እጅ ወይስ በራስ እጅ ነው ሕይወቱ ያለፈው የሚለው ጥያቄ በብዙ ውስብስብ ምርመራ እንዲሁም ቴክኒክ እና ታክቲክ ማስረጃዎች ታግዞ እና በአግባቡ ተተንትኖ ወደ አንዳች ድምዳሜ የሚያደርሱ መሆኑ እሙን ነው ።

በተያያዘው ጉዳይ #የቀነኒ_ማስታወሻ_ደብተር ነው #የተባለው ወደ ተጠርጣሪው ጠበቃ እጅ እንዴት እጁ ላይ ሊገባ ቻለ?

መቼ እና ለምን?

የብርበራ ትዕዛዝ ሲወጣ በተለይም በእንዲህ ዓይነት የነፍስ ግድያ ወ ራስን ማጥፋት ጉዳይ ላይ ፍንጭ ሊሰጡ የሚችሉ እንደ እነ ስልክ ንግግሮች ፣ የማስታወሻ ደብተር ፣ እንደ እነ የተቀዱ ካሴቶች እና ሌሎች ማስረጃዎች በመርማሪ ፖሊስ እጅ መግባት አልነበረባቸውምን? ወይስ በሰዓቱ ተደብቀዋል?

ጠበቃው በእጄ አለ ያለውንስ ማስታወሻ ደብተር ከየት አገኘው?

እንዳገኘውስ ለምን የምርመራው አካል አላደረገውም? ወይስ ወደ በኋላ ለመከላከያ መልስ ለመጠቀም በማሰብ አቆየው?

እውን የእሷ ማስታወሻ ደብተር ስለመሆኑስ ምን ማረጋገጫ አለ?

ለምንስ በዚህ ምርመራ ወቅት ተነሳ?

በአሁን ሰዓት ወንጀል ፈጽመዋል አልፈጸመም ወይስ ክርክሩ የዋስትና መብት ይጠበቅ ነው?

ፍርድ ቤቱስ በዚህ ማስታወሻ በተባለው ደብተር ጉዳይ ምን ይበይን ይሁን?

* እልፍ ጥያቄዎች
* አንድ እውነት
* ንጹህም አይቀጣ!
* ወንጀለኛም አይለቀቅ

Via Abebayehu Geta Enaro

@waliyaentmt
@waliyaentmt