Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
"የተሰበሰበው ገንዘብ ለአርቲስቱ አልተሰጠም" አዘጋጅ ኮሚቴው
"ስሜን ለማጥፋት ነው" ዲጄ ቤቢ

የአርቲስት ዓለማየሁ ደመቀን የ25 ዓመታት የኪነጥበብ ቆይታና አገልግሎት ለማክበርና አርቲስቱን ለማመስገን ዮቶር በሚል ርዕስ ሰኔ 15/2016 ዓ.ም የሙዚቃ ኮንሰርት በማርዮት ሆቴል አዳራሽ መከናወኑ ይታወቃል፡፡

በዝግጅቱ የተገኙ ገቢዎች የስፖንሰርሺፕ ገቢ፣ የቲኬት ገቢና ሌሎችም ገቢዎች ሂሳብ ተሰርቶ ርክክብ ባለመደረጉ በተደጋጋሚ ሂሳብ ተሰርቶ የአርቲስቱ ድርሻ ገቢ እንዲደረግለት ጥያቄ ቢቀርብም በተለያዩ ምክንያቶች ዲጄ ቤቢ መገኘት ባለመቻሉ ጉዳዩ እልባት ማግኘት አልቻለም ሲሉ ኮሚቴዎቹ ቅሬታውን በደብዳቤ ለሚዲያዎች ገልፀው ነበር።

ጉዳዩን አስመልክቶ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ለማጣራት እንደሞከረው ዲጄ ቤቢን አነጋግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል ደብዳቤው ቀድሞ ተልኮልኝ አይቼዋለሁ ያለው ዲጄ ቤቢ እንደአጋጣሚ ሆኖ አሜሪካን ሀገር በላስ ቬጋስ ከተማ በተዘጋጀው የአለም የሬዲዮና ቴሌቪዥን ብሮድካስተሮች ማህበር ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ አሜሪካ ሀገር ሄጃለሁ እሱን አጋጣሚ በመጠቀም "ሸሸ" በማለት ስም ለማጥፋት የተደረገ ስም የማጥፋት ዘመቻ ነው፣ ሙሉ በሙሉ ውሸት ነው! ጉዳዩን ወደ ህግ ወስጄዋለሁ ብሏል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #djbaby #alemayehudemeke