Waliya Entertainment
285 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
March 2
March 2
March 4
ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ አዲስ ነገር ይዛ እየመጣች ትገኛለች…

ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ የበኩር አልበምዋን "መጠርያዬ" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ይዛ መምጣትዋን አይዘነጋም፡፡

ሁል -ጊዜ አዳዲስ ጉዳዮችን ይዛ ብቅ የምትለው ወጣቷ ድምፃዊት ከሰሞኑ የሚለቀቁ ቪድዮች እንደ ሚኖሩም ገልፃለች፡፡ በራስዋ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ እንዲህ ስትል ለአድናቂዎቿ የሙዚቃ አድማጮች በሙሉ አድርሳለች፡፡

…"አንድ አንዴ ፈጣሪን ማመስገኛ ቃል አጣለሁ ተመስገን…በጣም የማከብረው ድርጅት ጋር የBrand Ambassader የመሆን ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን ነገ የምለቀውን ቪድዮ ሙሉ በሙሉ ገዝተውታል፡፡ የኔ ደስታ የሚያስደስታችሁ ቤተሰቦቼ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
ለማንኛውም የነገው አዲስ ነገር በMarch 8 በveronica Adane Youtube Channel የሚለቀው በውስጡ ያለው 12 ቪድዮ ነው ብዙ ደክመውበታል እንደ ምትወዱት አልጠራጠርም" ስትል ገልፃለች፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #veronica_adane
March 7
March 7
"ኪነ ጥበብን በኃላፊነት ተጠቅመን የተሻለ አብሮነት፣ ፍቅርና መከባበር እንዲኖር እንሰራን "- የሙዚቃ ባለሙያዎች

የሙዚቃ ባለሙያው ካሙዙ ካሳ እንደተናገረው፣ ኢትዮጵያ እዚህ የደረሰችው በአብሮነት በመሆኑ ነገንም ለመቀጠል አብሮነት እንደሚያስፈልግ ገልጻል፡፡ ስለአብሮነት ሁሌም መነገር፣መነሳት ማስታወስ አስፈላጊ ነው ያለው የሙዚቃ ባለሞያ ካሙዙ፣ለኢትዮጵያዊያን አብሮነት አዲስ አይደለም በአብሮነት የኖረ ህዝብ ነው ብሏል፡፡

በአብሮነት ችግርን መቅረፍ ጠላትን፣ ኑሮን ማሸነፍ፣ ድል መንሳት እንደሚቻል ገልጾ፣ በኪነ ጥበብ ፍቅር፣አንድነትና ጀግንነትን መግለጽ እንደሚቻል ተናግሯል።

ቀደም ሲል በነበሩ አባቶች፣ወጣት ድምጻዊያን ብዙ ተሰርቷል፣ወደፊትም ይሰራል። ኪነ ጥበብ በኃላፊነት ሰዎች ያላዩበትን መንገድ ማሳየት ፍቅርን ፣አብሮነትን መስበክ፣ሰዎችን ለመልካም ነገር ማነሳሳት መሆኑን አስረድቷል፡፡

ወጣቱ ትውልድ አብሮነት ከሌለ ምንም ነገር መሆን እንደማይችል ማወቅ እንዳለበትና መከፋፈሉ፣ መለያየቱ የማይጠቅም ነገር መሆኑን ሊረዳ ይገባል። መከፋፈልን ትተን በአንድነት፣ በመተሳሰብና ይቅር በመባባል የተሻለች ሀገር ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ አለብን ብሏል፡፡

ድምጻዊት ሃይማኖት ግርማ በበኩሏ፣ህዝባችን ከንግግር በላይ በተግባር አብሮ ይኖር ነበር፣ ወደፊትም ይኖራል፡፡ በሥራም በማንኛውም ጉዳይ የሆነ አካባቢ ሲኬድ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ጋር ጥሩ ነገር አለ። በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያለው አብሮነት የሚያስደስት ነው ብላለች፡፡

ሙዚቃ ትልቁ ሥራው ፍቅር፣አብሮነትን፣መልካም ነገርን፣የሰዎች መቀራረብን መስበክ መሆኑን በመግለጽ፣ወደፊትም በሰዎች መካከል አብሮነትን የሚያጸኑ ሥራዎችን እንደሚያስቀጥሉ ተናግራለች፡፡

@waliyaentmt
@waliyaentmt
@waliyaentmt
March 8
March 10
March 11
አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ድምፃዊ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ መሰንቆና ዋሽንት ተጫዋች፣ ክራርና በገና ደርዳሪ፣ የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መምህር የሆኑት አለማየሁ ፋንታ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ ከማስተማርም በዘለለ ትምህርት ቤቱ ሲከፈት የባህል ሙዚቃ ትምህርትን ለተማሪዎች እንዲሆን አድርገው ካሪኩለም በማዘጋጀት ከፍተኛ ሚናን ተጫውተዋል።

ውልደትና እድገታቸው በአሁኑ የዋግምራ ዞን ሰቆጣ አካባቢ ሲሆን፣ በልጅነታቸው በድቁና ማዕረግ ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል፡፡

ሙዚቃን የጀመሩት በሀገር ፍቅር ቴአትር ሲሆን ከ1950 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ዓመታት ያህል በክፍሉ ሰርተዋል፡፡ የኢትዮጵያን የባህል ሙዚቃ በመወከል በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእስያ በርካታ ሀገራትንም ተዟዙረዋል።

በእንግሊዝ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ጀርመን፣ ኦስትሪያና ሌሎችም በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የባህል ሙዚቃ አምባሳደርነት ማዕረግን ያገኙ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ በ1968 ዓ.ም ከዳካር የኔግሮ አርትስ ፌስቲቫል ሽልማት ከዩኔስኮ ለሙዚቃ ስራዎቻቸው እውቅና ፣ ከኮርያ ስፕሪንግ ፍሬንድ ሺፕ አርት ፌስቲቫል ዲፕሎማና የክብር ሜዳሊያና መሰል በርካታ ሽልማቶችንም አግኝተዋል::

አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ስርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈፀምም ታውቋል።

Follow us on
Telegram - https://t.me/waliyaent
March 11
March 11