Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሚስት ቀነኒ አዱኛ በድገንት ሂወቷ አለፈ።

የተወዳጁ ኦሮሚኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ አንዱአለም ጎሳ ሚስት የሆነችው ቀነኒ እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት ህይወቷን እንዳጣች መረጃ ቢገኝም ስለአሟሟቷ ፖሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Andualem_gossa
አርቲስት አንዷለም ጎሳ ከዕጮኛው ሞት ጋር በተያያዘ ለጥያቄ በፖሊስ መጠራቱ ተነገረ

በኦሮምኛ ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው አርቲስት አንዷለም ጎሳ ከዕጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ጋር በተያያዝ በፖሊስ ጥያቄ እንደተደረገለት ተሰምቷል።

በማኅበራዊ ሚደያ በርካታ ተከታዮቿ ያሏት ቀነኒ አዱኛ ማክሰኞ ጥዋት መሞቷን ተከትሎ በርካቶች ሐዘናቸውን ከመግለፅ ባሻገር የሞቷ ምክንያት እንዲጣራ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ፖሊስ በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።

የአርቲስት አንዷለም ማኔጀር ሌሊሳ ኢንድሪስ የአስከሬን ምርመራው በሚኒሊክ ሆስፒታል እንደሚደረግ እና የሟች የቀብር ሥነ-ሥርዓት ረቡዕ እንደሚከናወን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግሯል።

ቀነኒ ከሚኖሩበት ሕንጻ መውደቋን እና "ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ መሞቷን" ሌሊሳ ተናግሮ አንዷለም እና ቤተሰቦቹ ወድቃ እንዳገኟት አስታውቀዋል።

ሌሊሳ ንጋት 11 ሰዓት ሰዓት ስልክ ተደውሎ "ቀነኒ ጉዳት ደርሶባት ሆስፒታል እንደገባች" እንደተናገረው ገልጾ፣ "እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከአምስተኛ ፎቅ ወድቃ ነው የሞተችው። ሁኔታውን ለማጣራት ምርመራ ተጀምሯል" ብለዋል።

ሌሊሳ እንደሚለው አርቲስት አንዱአለም በአሁኑ ወቅት ለምርመራ በፖሊስ ጣቢያ ነው የሚገኘው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #andualem_gossa
ምንድነው የተፈጠረው?

የድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ማናጀር የሆነው ለሊሳ እንድሪስ የተፈጠረውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ከሰጠው ምላሽ በፋስት መረጃ እንደሚከተለው እናቀርበዋለን።
ንጋት 11:00 ሰዓት ስልክ ተደውሎ «ቀነኒ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች ቶሎ ድረስ» እንደተባለ የሚናገረው ለሊሳ እሱ ሩቅ በመሆኑ በሰዓቱ መድረስ እንዳልቻለ ይናገራል።

ቦሌ አራብሳ ከአመት በላይ በጋራ ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው ከአምስተኛ ፎቅ እንደወደቀች እና ምን እንደተፈጠረ ፖሊስ እያጣራ መሆኑ ተነግሯል።

ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ በቅርብ በሚገኘው ያኔት ሆስፒታል ከገባች በኋላ ጠዋት ፖሊስ መጥቶ ሬሳዋን ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ከወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት እስኪወጣ አስክሬኗ ወደ ቤተሰቦቿ ሱሉልታ መሄዱ ነው የተገለፀው።

ድምፃዊ አንዱዓለም ጎሳ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከሆስፒታል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እዛ የሚገኝ ሲሆን እኛ የምናውቀው እስካሁን አለመታሰሩን ነው ምርመራ እናድርግ ብሎ ነው ፖሊስ የወሰደው ሲል ማናጀሩ ይናገራል።

ለሁለት አመታት በፍቅር ከቆዩ በኋላ በቅርቡ ጋብቻቸውን ለመፈፀም እየተዘጋጁ እንደሆነ አውቃለሁ ሲል ለሊሳ ይናገራል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #andualem_gossa
በአንዱአለም ጎሳ ክስ ላይ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ፖሊስ ተጋጩ!

ተጠርጣሪው ድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ከተያዘ በኋላ በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በኦሮሚያ ፖሊስና ሚሊሻ መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ። ዛሬ ሦስት የኦሮሚያ ፖሊስ መኪኖች ከሚሊሻዎች ጋር አንዱአለምን ወደሚገኝበት ማቆያ ጣቢያ በመሄድ ጉዳዩን ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ እንዲተላለፍላቸው ጠየቁ። የፌደራል ፖሊስና ከንቲባ ጽ/ቤት ያረጋገጡዋቸውን ደብዳቤዎች ይዘው መጡ።

ነገር ግን የአዲስ አበባ ፖሊስ ተጠርጣሪውንም ሆነ የጉዳዩን ፋይል ለማስተላለፍ ፈቃደኛ አልሆነም። ይህም ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኖ የተኩስ ድምፅም ተሰምቷል።