Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
" ፈንድቃን ዳግም እንድገነባ መንግስት ፈቃድ ሰጥቶኛል "

#Ethiopia : ካዛንቺስ በተመሳሳይ ቦታ ፈንድቃን እንድገነባ መንግስት ፍቃድ ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ መላኩ በላይ ። የፈንድቃ ባለቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት ፣ ውድ የፈንድቃ ወዳጆችና ጏደኞቼ፣ ለፈንድቃ ያላችሁን ፍቅር እና ድጋፍ በጣም አከብራለሁ አመሰግናለሁ። መንፈሶቻችሁ ለጥበብ ያላቹ ክብር በልቤ ውስጥ ነው - በጣምም ያበረታኛል ብሏል ።

ካዛንቺስ በተመሳሳይ ቦታ ፈንድቃን እንድገነባ መንግስት ፍቃድ ስለሰጠኝ በጣም አመሰግናለሁ ያለው መላኩ ፣ አንድ ላይ ሆነን ለፈንድቃ የተሻለ የወደፊት ጊዜ እንዳለም አምናለሁ ሲል ገልጿል ።

አዲሱን ፈንድቃ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ሁላችሁም የበኩላችሁን እንድታበረክቱ እጠይቃለሁ። የፈንድቃን ህልም አንድ ላይ በመሆን እንደምናሳካውም አውቃለሁ::

" በቅርቡ GoFundMe ዘመቻ እንጀምራለን ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በ fendika.org/support በዚህ መንገድ የገንዘብ ድጋፍ እንድታደርጉ አማራጮችን ይሰጥዎታል። ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Fendika
ዳዊት ፅጌ ህዳር 7 ቀን በሚሊኒየም አዳራሽ ኮንሰርት ሊያደርግ ዝግጅቱን ጨርሷል።

"የኔ ዜማ" አለም አቀፍ የሙዚቃ ጉዞ የመጀመሪያ ምዕራፍ ማጠናቀቂያ ይሆን ዘንድ ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስአበባ በሚሊኒየም አዳራሽ የሙዚቃ ኮንሰርታችንን ለማቅረብ ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን ሲሆን በዚህ ደማቅ ምሽት ላይ ተገናኝተን የማይረሳ ጊዜ እንድናሳልፍ ስል በአክብሮት እጋብዛለሁ።" - ዳዊት ፅጌ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #dawit_tsige
"ለወደፊቱ ዘማሪ የመሆን እቅድ አለኝ" - ቬሮኒካ አዳነ

#Ethiopia  | ሰላም የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የመዝናኛ መጽሔት አንባቢያን እንደሚታወቀው በአውደ ጥበብ ገፃችን በሀገራችን ኢትዮጵያ በኪነ፡ጥበብ ፣ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በማህበራዊ ግልጋሎት ፣ በበጎ አድራጎት ፣ በስፖርትና በሌሎች የተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለሀገራቸው እና ለማህበረሰባቸው  በርካታ ትሩፋትን ያበረከቱና ቅንነትን መለያቸው ፣ ምክንያታዊነትን የህይወት መርህ አድርገው በሀገር ፍቅር ከተቃኙ መካከል ለእናንተ ለአንባብያን በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች ከህይወታቸው ፣ ከስብዕናቸው ፣ ከስራ ውጣ ውረዳቸውና ከልምዳቸው ትማሩበታላችሁ ያልናቸውን ወደ እናንተ የምናደርስበት አምድ ነው፡፡ ታዲያ በዛሬው አውደ ጥበብ አምዳችን እንግዳችን ወጣቷ ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ናት፣ ቬሮኒካ የህይወት ተሞክሮዋን እና ልምዷን ልታካፍለን ከመዝናኛ መጽሔት ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡ እንድትከታተሉን አስቀድመን በት ህትና እንጋብዛለን።

መዝናኛ:- በቅድሚያ በዚህ በተጣበበ ጊዜሽ የመዝናኛ መፅሔት እንግዳ ለመሆን ፈቃደኛ ስለሆንሽ በመፅሔት  አንባቢያን ስም እጅግ በጣም  እናመስግናለን። ወደ መዚቃው አለም እንዴት እንደገባሽ እና ማን ፈር ቀዳጅ እንደሆነልሽ ብትገልጭልን?
ቬሮኒካ:- በቅድሚያ የመዝናኛ መፅሔት እንግዳ ስላደረጋችሁኝ እጅግ በጣም አመስግናለሁ። ወደ ሙዚቃው ዓለም የገባሁት በልጅነቴ መዝሙር አዳምጥና አንጎራጉር ነበር፣ ቀስ በቀስ ይህ ልምምዴ ወደ ዘፈን ማዜም ይዞኝ ሊጓዝ ችሏል፣ መዝሙር በጣም ይመስጠኝ ነበር እናም እየዘመርኩኝ ነው ድምፄ የተሞረደው፣ አባቴ ዘፋኝ መሆን ተጨምሮበት ፣በመቀጠልም ዘፈኖችን እያዳመጥኩ ወደ ዘፈኑ አደላሁ፣ የማዳመጥ እድሉን አገኘሁና ወደዛ ተሳብኩ፣ የአማርኛ ዘፈኖችን መዝፈን የምችል አይመስለኝም ነበር በጊዜው። ከዚያ የናቲ ማን በቃ አልበም ሲወጣ በጣም መስጦኝ ዘፈኖቹን መዝፈን ጀመርኩ፣ ከዛም ጭልጥ አድርገው ወደ አማርኛ ዘፈኖችይዘውኝ ገቡ፣ እንግዲህ አማርኛ መዝፈን እንደምችል ሳውቅ ከሪሃና ቀጥሎ፣ቴዲ ታደሰ እና ናቲ ማን ለእኔ ወደ ዘፈን አለም መግባት ፈር ቀዳጆቼ ናቸው።

መዝናኛ:- ቬሮኒካ ጥሩ ጋዜጠኛ ትሆናለች ተብሎ ሲጠበቅ ነው በሙዚቃው የተከሰትሽው፣ እንዲያውም  ጋዜጠኝነቱን ከጥግ ለማድረስ እስከ ዩንቨርስቲ ዘልቀሽ ተመርቀሻል፣ ጋዜጠኛኝነቱ የት ቀረ?

ቬሮኒካ:- በጆርናሊዝም እና ኮሙኒኬሽን ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዲግሪ  ተመርቂያለሁ፣ የእውነትም ወድጄው የተማርኩት ትምህርት ነው፣ በጥሩ ውጤትም ነው የጨረስኩት። ግን ሙዚቃው አሸነፈኝና ለጊዜው ሙሉ ትኩረቴን እዚህ ላይ አድርጌአለሁ፣ ለወደፊቱ ግን አንድ ነገር መስራቴ የማይቀር ነው፣ ሙዚቀኛ ባልሆን ኖሮ ጎበዝ ጋዜጠኛ እሆን ነበር፣ምክንያቱ ደግሞ ለሙያው ልዩ ክብርና አድናቆት ስላለኝ።

መዝናኛ:- የትኞቹን ማህበራዊ ሚዲያዎች ትጠቀሚያለሽ፣ እንዴት እና ለምንድን ነው  የምትጠቀሚባቸው፣ ስለ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን ላይ ምን ታዘብሽ?

ቬሮኒካ:- ሁሉንም ማህበራዊ ሚዲያዎችን እጠቀማለሁ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቲክቶክ እና ዩቲዩብ እጠቀማለሁ፣ ራሴን እና ስራዎቼን ለተከታዬቼ ለማስተዋወቅ፣  የምፈልገውን መልዕክት ለማስተላለፍ፣ በተለያዩ ጉዳዬች ላይ ያሉኝን ቅን ሀሳቦች ለሌሎች ለማካፈል  እጠቀማቸዋለሁ። ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ሸጋ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው፣ በአሁኑ ጊዜ፣ ማህበራዊ ሚዲያ በዓለም ላይ ቀዳሚው የመገናኛ ዘዴ ሆኗል። ማህበራዊ ሚዲያ ሀሳቦቻችንን፣ አፍታዎችን፣ መረጃዎችን፣ ሰነዶቻችንን እና የተለያዩ መረጃዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ  እንድንለዋወጥ ያስችለናል፣ በአውንታዊ ሁኔታ እስከተጠቀምንበት ድረስ፣ በዚህ ዘመናዊ ዓለም ውስጥ፣ ማህበራዊ ሚዲያ በሕይወታችን ውስጥ የተለየ ቦታ ይዟል፣ የሕይወታችን አካልና ክፍል ሆኗል። በአጠቃላይ ማህበራዊ ሚዲያ  ለበጎ ነገር ከተጠቀምንበት ኃይል አለው፣ ማህበራዊ ሚዲያን ለአፍራሽ ተልዕኮና ለአሉባልታ የሚጠቀሙበት ጥቂት ሰዎች እንዳሉ ሆነው ማለቴ ነው።

መዝናኛ:- ሰዎች የተሻለ  ስብዕና እንዲኖራቸው  ምን  ትመክሪያቸዋለሽ?

ቬሮኒካ:- እራስን መሆን፣ እራስን ማክበር፣ ሌሎች የሚኖሩትን ኑሮ ለመኖር መሞከር ሳይሆን፣ ራስ ህ ባለህ ነገር ማመስገን፣ ሌሎችን ለመወዳደር መኖር ሳይሆን የራስን ህልም ለመኖር መሞከር፣ ራስን ማክበር፣ ያለህበትን ማንኛውም ሁኔታ መቀበል። ለምሳሌ፣ አባቴ ሊስትሮ ቢሆን፣ እናቴ አስተናጋጅ ብትሆን ይሄንን ማክበር፣ በእነርሱ መኩራት፣ በቃ ለራስ ክብር  መስጠት ያስፈልግይል ። ይሄንን ስል ራስ ወዳድ መሆን ሳይሆን፣  ለራስ ክብር መስጠት ማለቴ ነው፣  አንተ ያላከበርከውን አንተነት ሌሎች አያከብሩትም እና ክብር ለራስ መስጠት ያስፈልገናል።

መዝናኛ:- ለወደፊቱ በሙዚቃው ኢንደስትሪ ውስጥ የራስሽን አሻራ ለማሳረፍ  ምን ሀሳብ አለሽ?

ቬሮኒካ:-ለወደፊቱ  የራሴን ስራዎችም ሆነ የሌሎችን ሙዚቃዎች ለማሳተም እፈልጋለሁ፣ እራሴንም ሆነ ሌሎችን ፕሮዱዮስ አደርጋለው ብዬ አስባለሁ፣ ለወደ ፊቱ ግን እግዚአብሄር ቢፈቅድ ዘፋኝ ሆኜ መኖርን አላስብም፣ እግዚአብሄር በሰጠኝ ድምፅ በመዝሙር እያገለገልኩት መኖር ነው ህልሜ። እርሱንም ወደ ፊት የምናየው ይሆናል።

መዝናኛ:- ማህበረሰብሽን እንዴት ታገለግያለሽ?

ቬሮኒካ:- የኪነ ጥበብ ሰው ለተገኘበት ማህበረሰብ ብዙ ነገር መልሶ መስጠት አለበት እላለሁ፣ ማህበረሰቡን ለማንቃት፣ ለመደገፍና ለማገዝም ትልቅ ኃላፊነት አለበት፣  ምክነያቱም ሞያህንም ሆነ አንተነትን ህዝብ ሲወድልህ እና ሲያከብርህ ነው አንተ ከፍ የምትለው ፣ እናም ላከበረህ፣ ለወደደህ ህዝብ ደግሞ በሚፈልግህ ጊዜ ሁሉ በገንዘብህም ሆነ በሞይህ ቀድመህ መገኘት አለብህ ብዬ አስባለሁ፣ ምክንያቱም የዚሁ ህብረተሰብ አባልና ክፍል ስለሆንክ።

መዝናኛ:- ማህበራዊ ሚዲያው ለሙዚቃው ኢንዱስትሪ እድገት ምን ያህል ጠቀሜታ አለው ብለሽ ታስቢያለሽ?

ቬሮኒካ:- ኦ! በጣም በጣም ትልቅ ጥቅም አለው ፣ እኔ አሁን የመጣሁት ከህዝብ ጋር ያስተዋወቀኝ ማህበራዊ ሚዲያው ነው፣ በእንድ ጊዜ ዓለም ላይ ላሉ የሙዚቃ አፍቃሪዎች መድረስ ትችላለህ፣ ድሮ ቢሆን ይኼ የለም ነበር፣ አንድን አሳታሚ ደጅ ጠንተህ ነበር ህልምህ እንዲሳካ የምትሞክረው፣ እጅግ ጠባብ ነበረ፣ የማይገቡ መሰዋትነቶችን ልትከፍል ትችል ነበር በጊዜው፣ በተለይ ሴት ስትሆን ደግሞ ብዙ ዋጋ ልትከፍል ትችላለህ፣ ያንን ሁሉ ነው ያስቀረልን ማህበራዊ ሚዲያው፣ እና በጣም ጠቃሚ ነው። ማህበራዊ ሚዲያን መጠቀም በአለም ላይ ካለ ማንኛውም ሰው ጋር የመገናኘት እና መረጃን በፍጥነት የመለዋወጥ እድልን ስለሚፈጥር  በሰዎች መካከል ለመግባባት እና ለመታወቅ በጣም ሀይለኛ መንገድ ነው።

መዝናኛ:- ስለ ሀገርሽ ምን ታስቢያለሽ፣ ምንስ ትመኛለሽ?

ቬሮኒካ:- ሀገሬ! ሀገሬ!! ሁሉም ሰው በሰላም ወጥቶ የሚገባበት፣ ሰርቶ የሚያገኝባት፣ በልቶ የሚጠግባት፣ ለብሶ የሚያጌጥባት፣ ፍቅር የሚነግስባት፣
እንደ ሰው በፍቅር ብቻ የምንኖርባት ሀገር እንድትሆን እመኛለው። ሀገሬ
ለሁላችንም የፍቅር፣ የሰላም፣ የአንድነት ሀገር እንድትሆን እመኛለሁ።

መዝናኛ:- የሀገርሽን ባህል በሙዚቃሽ እንዴት ታስተዋውቂያለሽ?
ቬሮኒካ:- ወደፊት በእንግሊዘኛ የመዝፈን ፍላጎት ቢኖረኝም፣ ምንም ቢሆን የመጣሁበት ማንነት የማይለቅ ነው፣ ዘፈኖቼን ብታያቸው በዘመናዊ መልኩ ባህልን የሚያስተዋውቁ ሆነው ነው የተሰሩት፣ አባቴ ሙሉ በሙሉ በሙዚቃ ስራዎቹ ባህሉን ሲያስተዋውቅ የኖረ ሰው ነው፣ እኔም ከእርሱ መፈጠሬ ባህሌን እንድወድ እና እንዳከብር ያደርገኛል፣ እንደ አባቴ እንኳን ባይሆንም ዘመናዊ በሆነ መንገድ ወደፊት በስራዎቼ ላይ በትልቁ ባህሌን መግለጥ አስባለሁ። ባህሌ ከእኔ ጋር አብሮ ያደገ ስለሆነ በልብቤ ውስጥ ሁልጊዜም የሚኖር ነው። በምንም አትለውጠውም በጎደለብኝ ባነሰብኝ ብለህ የምታበላልጠው ነገር አይደለም፣ የሀገራችንን ባህሎች ሁሉንም ስለምወዳቸውና ስለምኮራባቼው፣ የማንነቴ አሻራዎች ስለሆኑ በዘፈኔ ብቻ ሳይሆን በኑሮየም አስተዋውቃቸዋለሁ።

መዝናኛ:- ለሌሎች ልክ እንዳንች ዘፋኝ ለመሆን ለሚፈልጉ ወጣቶች ምን ትመክሪያቸዋለሽ፣ በመዚቃው ዓለም የገጠሙሽ ተግዳሮቶችስ ምንድን ናቸው?

ቬሮኒካ:- እኔ ለወጣት ልጆችን የምመክረው ምክር ለሞያቸው ታማኝ መሆን ያስፈልጋል፣ ጥረት፣ ትጋት፣ ዲሲፒሊን፣ እውነተኛ የሞያ ፍቅር ያስፈልጋል። አንድ ሰው ዘፋኝ መሆን ሰለ ፈለገ ብቻ ዘፋኝ መሆን አይችልም፣ የተሰጠው ክህሎት ያስፈልገዋል፣ ተሰጥዖው እና ድምፁ ካለ በራስ መተማመንም ወሳኝ ጉዳይ ነው። እራስን መጠበቅ፣ አደርገዋለሁ ብሎ መነሳት፣ መፀለይ፣ ጠንክሮ መስራት፣ ለሙያዉ ታማኝ መሆንን እና ፀንቶ መቆምን ሙያው ይጠይቃል። በዚህ ሞያ ውስጥ ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች አሉ፣ በተቻለ መጠን ፀንቶ በመቆም፣ ነገን በተስፋ በማሰብ፣ ጠንክሮ በመስራት ችግሮቾን ማለፍ ይቻላል የሚል የፀና አቋም አለኝ፣ የህይወት ልምዴ ይኼንን ነው ያስተማረኝ፣ ሳይበገሩ አላማ ግቡን እንዲመታ መጣር ያስፈልጋል፣ ምክሬ ለወጣቶች ይህ ነው። እኔ ብዙ ፈተናዎች ገጥመውኛል፣ ፀንቼ በመቆሜ ዛሬ ላይ እዚህ ላይ ደርሻለሁ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #veronica_adane
"እንደድከማችን ...እንደተሰበርነው ...በጭንቀት ውስጥ እንሆነው ...እንደታመምነው...የሚያበረታ አካል እንደፈለግነው ...መጠንከር እና በራስ መቆም እንደፈለግነው አምላክ ያውቃል ! ይህን ሁሉ የሚያውቅ ጌታ አለን ...ስለኛ ሁሉን የሚያውቅ ጌታ አለን ። እኛ ማወቅ ያለብን አምላክ እንዳለን ነው ። አዎ አምላክ አለ!!❤️❤️❤️" - ያሬድ ነጉ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yared_negu
ጋሼ ማሕሙድ አሕመድ ከመደረክ ሊሰናበት ነው

በአገራችን ዘመናዊ ሙዚቃን ከባህላዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ጋር አዋህዶ በመዝፈን በአገራችን ቀደምት የሙዚቃ ንጉስ ከመድረክ ሊሰናበት ነው።

ጋሽ ማሕሙድ በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በሊይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያበረከተው አስተዋጽኦ ለአሁኑ ትውልድ ትልቅ አርአያ የሆነ የሙዚቃ ገጉስ ነው፡፡ በዚህ ረገድ እኢአኢኔ በ2ዐዐ7 ቢቢሲ ሬዱዮ ከአፍሪካ በድንቅ ዘፋኝነቱ ተሸለሚ አድርጎታል፡፡

ይህ በአገራችን የሙዚቃ ዘርፍ ስመጥር ሀብታችን የሆነውን የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም ለመሰናበት ወይም ማይኩን ሊሰቅል ሲዘጋጅ እጃችንን አወዛውዘን መሸኘት አግባብነት የለውም በሚል ሽኝቱን በደመቀ እና በታሪከ ማስታወሻነትም እንዲቀመጥ ጆርካ ኤቨንት ይህን ከባድ ኃሊፊነት ከጋሽ ማሕሙድ ኮሚቴ ጋር በመሆን ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚለኒየም አዳራሽ ደረጃውን የጠበቀ የመጨረሻውን የህይወት ዘመን ስንብት ኮንሰርት ያዘጋጃል፡ እንዱሁም በዚህም ቀን በክብር ዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ
የሙዚቃ ሕይወት የተዘጋጀ መፅሀፍ የሚመረቅ ይሆናል፡፡ይህም የመጨረሻ የመድረክ ስንብት ሁሉም ኢትዮድያዊ ከጎናችን ስለሚቆም ከብር ይሰማናል ።


Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #mehammud_ahmed
የድምፃዊ ዲሽታ ጊና መልእክት

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተሳታፊ ከሆኑ ባህላዊ መሪዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከል ድምጻዊ ታሪኩ ጋንካሲ (ዲሽታጊና) “በመድረኩ ተሳታፊ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ። ለሀገሪቱ ቀጣይ ዕድገት፣ ልማትና ብልፅግና በማስተዋል በመምከር ያጋጠሙ ችግሮችን መፍታት ይገባል” ሲል ተናግሯል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #dishta_gina
ተወዳጁ ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ከአባቱ ሞት በዃላ የአልበም ምርቃቱን ሊያደርግ ነው።

በብዙዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅነትን ያገኘው የሚካኤል በላይነህ አዲሱ ‘አንድ ቃል’ የተሰኘውን አልበም ቅዳሜ ጥቅምት 30 /Nov. 09/ በማርዯት ሆቴል ለማስመርቅ ዝግጅቱን ጨርሷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #micheal_belayneh
ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በዩቲዩብ ከ 1ሚሊዮን በላይ ሰብስክራይበር በማግኘት የዩቲዩብ ጎልድ በተን ተሸላሚ ሆነ።

እንኳን ደስ አለህ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_afro
ወጣቱ ድምፃዊ ከወራት በኋላ የአልበም ስራውን ለአድማጭ እንደሚያደርስ ገለፀ

ከእዚህ ቀደም ሰርቶ ለሙዚቃ አፍቃሪያን ባደረሳቸው አንቀልባ፣ ሀገሬ፣ ንማጀ፣ እንዲ ነው ወይ? እና ሌሎች ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎች የሚታወቀው ወጣቱ ድምፃዊ በፍቃዱ ያደቴ (በፊ ያድ) የመጀመሪያ አልበሙን ሰርቶ እንዳጠናቀቀ ተናግሯል።

በአልበም ስራው ውስጥ የተለያዩ ሀሳቦችን እና በልዩ ልዩ ስልተ ምት የተቃኙ ስራዎች እንደተካተቱበት ድምፃዊው አንስቷል።

እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ የአልበም ስራውን ለአድማጭ ለማድረስ መታቀዱን የገለፀ ሲሆን በርካታ የሙዚቃ ባለሙያዎች ተሳትፎ እንዳደረጉበት ገልጿል።

ከአንድ ሳምንት በፊት ለአልበሙ መዳረሻ ይሆን ዘንድ ታስቦ የተሰራው ነጠላ ዜማው በድምፃዊው ስም በተከፈተው ዩቲዩብ ቻናል መለቀቁንም ተናግሯል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #befiyad
የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ አልባሳትና ቁሳቁስ ለዕይታ ሊቀርብ ነው።

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ አልባሳት እና ቁሳቁስ ትውልድ እንዲያየው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ተቋም ጥቅምት 29 ቀን 2017 በክብር ይቀመጣል ተባለ፡፡
በዕለቱም የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች እና ሌሎች እንግዶች እንደሚገኙ የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የመታሰቢያ ዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል፡፡

ታሪካዊ የሆኑ እና በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ኅያው ሆነው እንዲኖሩ ከአርቲስቱ ቤተሰቦች የተሰበሰቡ አልባሳት እና ቁሳቁሶችንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተረክቦ ለዕይታ ያቀርባሉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #tilahun_gessesse
ተወዳጅዋ ድምፃዊ የማርያም ቸርነት (የማ) እና እዩኤል መንግስቱ የኢትዮጵያን ቱባ ክዋኔ ጥበብ ለማስተዋወቅ በአውሮፓ ሊዞሩ ነው።

"በቅርቡ ለሶስት ወር ከግማሽ ከኢትዮጵያ ውጪ በአውሮፓ (ፈረንሳይ፣ ቤልጂየም፣ ስዊትዘርላንድ፣ ሞናኮ ሞንቴካርሎ፣ አንዶራ) በተለይም በተለያዩ የፈረንሳይ ግዛቶች የኢትዮጵያን ቱባ ክዋኔ ጥበብ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል። ለወራት ልምምድ ያደረግንበት ይህንን የሀገራችንን ክውን ጥበብ (Performing Art) በዓለም አቀፍ መድረክ ለማቅረብ ከሙሉ የሙዚቃ፣ የዳንስ እና የሰርከስ ቡድን ጋር ዝግጅታችንን መጨረሳችንን ዛሬ በቱሊፕ ሆቴል /Tulip Hotel/ በነበረን ጋዜጣዊ መግለጫ አብስረናል።

በሚኖሩን በነዚህ ዓለም አቀፍ መድረኮች በኢዩኤል መንግስቱ ፕሮድዩስ ከተደረገው እና የበኩር ስራዬ ከሆነው "ከደጋ ሰው አልበም" ውስጥ የተወሰኑ ስራዎችን የማቀርብ ሲሆን በተጨማሪም በአንጋፋው የፈረንሳይ የፊልም ሙዚቃ ደራሲ፣ አቀናባሪ፣ የሙዚቃ መሪ/conductor/ ክርስቲያን ክራቬሮ የተፃፉ ሙዚቃዎችን የምናቀርብ ይሆናል።

የአፍሪካን ድሪም አርትስ እና ሰርከስ (African Dream Arts and Circus) መስራች፣ ሀላፊ፣ አሰልጣኝ በሆነው የኔነህ ተስፋዬ ዳይሬክተርነት እና በፈረንሳዩ ሰርክ ፌኒክስ ካምፓኒ ፕሮዲዩሰርነት ለተዘጋጀው ዓለም አቀፍ ክውን ጥበብ /Performing Arts/ በፌኒክስ መድረክ እንድንቀርብ ስለተጋበዝኩ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።" - የማርያም ቸርነት(የማ)

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yema