Waliya Entertainment
291 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የኝህ ታላቅ ሙያተኛ ፒያሳ አካባቢ የሚገኘው ቤታቸው ለልማት ተብሎ በፈረሰ ወቅት ይህ አጋጣሚ እንደተፈጠረ እና በጊዜውም ከሌሎች እርባና ከሌላቸው ቁሶች ጋር ተቀላቅሎ እንደተሰጠውም ገልጿል።

እኝህ ተዋቂ ጥበበኛ አሁን በህይወት የሉም ስማቸው እና ስራቸው ለምድር የከበደ፣ ለሰማይ የራቀ ነው። ለልጆቻቸው ለቤተሰቦቻቸውም ስንል ስማቸውን ከመጥቀስ እንቆጠባለን። ግን ደግሞ ለዘመናት የሙያ ስኬቶቻቸው የተስተዋሉባቸው ምስሎችን የያዘው አልበማቸውን ጨምሮ በጉማ አዋርድ አዘጋጆች የተሸለሙትን የህይወት ዘመን ሽልማት ከቻልን ለሽልማቱ አዘጋጆች ካልሆነም ለቤተሰቦቻቸው በዳግም ክብር መልሰን እንሰጣለን።

ይሄ እንዲሆን ያስቻለውን ሰለሞን አክሊሉን ግን ከልብ እናመሰግናለን ብዥታውንም ስላጠራልን።
ለዛ ።   - ብርሀኑ ድጋፌ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ መልዕክት ....🙏🙏

“በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።”

እስኪ የምትወዷት በላይክ ግለፁለት!!!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
Today's Best photo🥰🥰🥰

Youtube -  https://www.youtube.com/@waliyaent?sub_confirmation=1

#photo #photographychallenge
#photooftheday #photochallengesmilechallengetoday
#waliya_entertainment #Zeritu_kebede
👍21
ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ በጋራ የተሰሩት ገሚስ አልበም ዛሬ ይመረቃል

ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ በጋራ የተሰሩት "አዲስ ቀለም" የተሰኘ ገሚስ አልበም ዛሬ ሐምሌ 18 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ቦሌ ዓለም ሲኒማ አካባቢ በሚገኘው "The Jungle" ውስጥ እንደሚመረቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።የዚህ ገሚስ አልበም ምርቃት መግቢያ በነፃ ተብሏል።

"አዲስ ቀለም" ገሚስ አልበም በውስጡ ምንድነው ፣ ኤሌክትሪክ፣ ማዕዘን፣ተው ተው፣አንድ ሰሞን የተሰኙ አምስት ሙዚቃዎችን የያዘ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

የገሚስ አልበሙ ግጥም ፣ ዜማ፣ እንዲሁም ከሙዚቃው ቅንብር እስከ ማስተሪንጉ ድረስ በያምሉ ሞላ ተሰርቷል።

በተጨማሪም በከበሮ አገረሰላም ሻፊ ፣ በመሰንቆ ሀዲንቆ፣በክራራ ፋሲካ ኃይሉ ተሳትፈዋል።

"አዲስ ቀለም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና የሙዚቃ አቀናባሪው ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ የተጣምሩበት ገሚስ(EP) የሙዚቃ አልበም በዩቲዩብ እና ስፖቲፋይ መተግበሪያዎች በኩል ባሳለፍነው አርብ እንደተለቀቀ ይታወሳል

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ከሰሞኑን በደቡቡ የሀገራችን ክፍል (ጎፋ) በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ እና ጉዳት በደረሰባቸው ኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ በደረሰውም አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች በሙሉ ከልብ መፅናናትን እመኛለሁ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፍቅር ያሸንፋል !
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ቬሮኒካ : -አሁን ደህና ነኝ

ዱባይ የምትገኘው ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ እንዴት ቦርሳዋ ውስጥ እንደተገኘ የማታስታውሰውን የጥፍር ማጠበቂያ ግሉ የታዘዘላት የአይን ጠብታ መስሏት ሳታስተውል አይኗ ላይ ሙሉ በሙሉ ጨምራው ወድያው በፍጥነት ወደ ሆስፒታል በመሄዷ አይኗ ከመጥፋት የዳነ ሲሆን ቬሮኒካ እኔን በዋዜማው አባቴን ከሞት አደጋ ያተረፈው ቅዱስ ገብርኤል ብርሀኔን ከማጣት አድኖኛል ሴቶች ጥንቃቄ አድርጉ የምትጠቀሙዋቸውን ነገሮች በተረጋጋ ስሜት እና በማስተዋል አድርጉ ብላለች::

አሁን በጣም ደህና ነኝም ብላለች::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
😁2
ቴዲ ማክ የሙዚቃ አቀናባሪ ፣ ዜማ ደራሲ ፣ ኪቦርድ ተጫዋች ሁለገብ ሙዚቀኛ።

ቴዲ ማክ በሙዚቃ ባለሙያነቱ የተዋጣለት አርቲስት ሆኖ ከሃያ ስምንት አመታት በላይ ቆይቷል። በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊ ሙዚቃ እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ካደረጉ የሙዚቃ ባለሞያዎች ውሰጥ አንዱ እንደሆነም ይነገርለታል። ቴዲ ማክ ለሙዚቃ ፍቅር የነበረው ገና በ8 አመቱ በጀርመን ትምህርት ቤት (በአዲስ አበባ) ተማሪ እያለ ነው። ቴዲ ማክ በመጀመሪያ ሙዚቃን የተማረው በአዲስ አበባ በሚገኘው ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሲሆን በመቀጠልም በሰሜን ቨርጂኒያ ኮሚኒቲ ኮሌጅ አሜሪካን ጃዝ ሙዚቃን ተማረ።

የቴዲ ማክ የሙዚቃ ስራዎች ከ573 በላይ ዝግጅቶችን እና ሙዚቃዊ ድርሰቶችን፣ለ25 ዘጋቢ ፊልሞች የድምጽ ትራኮችን፣ከ 45 በላይ የሙዚቃ አልበሞችን አዘጋጅቷል። "ገመና" የተሰኘውን ተከታታይ ድራማን ጨምሮ ለተለያዩ ፊልሞች የድምፅ ትራኮችንም ሰርቷል።

ከሰራቸው ተወዳጅ ስራዎች ውስጥ በጥቂቱ
1, ጥላሁን ገሰሰ - ኢትዮጵያ
2, ሚኒሊክ ወስናቸው - ፍቅር አያረጅም
3, አስቴር አወቀ - ኤቦ
4, ኤፍሬም ታምሩ - ቢልልኝ
5, በዛወርቅ አስፋው - ለመኖር

እርሶ የቱን ስራ ይወዱታል?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Teddy_mak
🔥2
❣️ 1 ሚሊዮን ብር ለገሠ

#Ethiopia | ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በጎፋ በመሬት ናዳ ሳቢያ ለተጎዱ ወገኖች መርጃ የሚውል 1 ሚሊየን ብር ለግሷል።

❣️ ቴዲ አፍሮ
ትናንት በማህበራዊ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት “ከሰሞኑን በደቡቡ የሀገራችን ክፍል (ጎፋ) በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ እና ጉዳት በደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ በደረሰውም አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች በሙሉ ከልብ መፅናናትን እመኛለሁ።” ማለቱም ይታወሳል።

❣️ Artist #Tewodros_Kassahun (ቴዲ አፍሮ)

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት ተመልካች ያገኙ 10 የሳምንቱ ሙዚቃዎች

በዚህ ሳምንትም የሙሉአለም ታከለ "የት ነሽ" አዲስ ሙዚቃ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲገባ የአብዱ ኪያር እና ሰላማዊት ዮሐንስ በዚህ ሳምንትም በርካታ ተመልካች በማግኘት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን አለቀቁም።

1ኛ🔸አብዱ ኪያር (ገለመሌ) 🎶 788,380 እይታ
2ኛ🔸ሰላማዊት ዮሐንስ (ሰንቢደ) 🎶 671,352 እይታ
3ኛ ሙሉአለም ታከለ (የት ነሽ) 🎶 486,302 እይታ
4ኛ🔸 አብዱ ኪያር (አይዞ) 🎶 407,959 እይታ
5ኛ🔸 አንዱዓለም ጎሳ (ቢሊሌ) 🎶 338,132 እይታ
6ኛ አብዱ ኪያር (ቡቡዬ) 🎶 337,481 እይታ
7ኛ🔻አብዱ ኪያር (ፓ! ፓ! ፓ!) 🎶 329,395 እይታ
8ኛ🔻ሮፍናን (ሸግዬ) 🎶 315,744 እይታ
9ኛ🔸 ናሆም መኩሪያ (ባዳ ባዳ) 🎶 301,013 እይታ
10ኛ🔸 ቬሮኒካ አዳነ (እናነይ) 🎶 299,179 እይታ

ደረጃ ያሻሻሉ
🔻 ደረጃ የቀነሱ
🔸ባሉበት ደረጃ የቆዩ

🎶 በሳምንቱ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት የታዩ ሙዚቃዎችን በትክክለኛ ዳታ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ምርጥ አስር ሙዚቃ ሰንጠረዥ ነው።

🎶 ቁጥሮች በሳምንት ውስጥ የጨመሩትን እይታ ብቻ ነው የሚያሳየው።

አርብ ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም

👏1