Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
"በጊዜ ሂደት የገባኝ ነገር ምንድነው ሰው ማፋቀር ፤ ማግባት ፤ መውለድ የተፈጥሮን ህግ መከተሉ ፤ ማህበራዊ ህይወት ከአጓጉል ድባቴ እና ego ነፃ ያወጣዋል። የሰው ልጅ እድሜው ከፍ እያለ ሲጫጫን ፤ ብቸኝነት ሲበዛ ፤ ቅርቡ ያሉትን ከራሱ ጋር ማነፃፀር ሲጀምር ሲያይ ከባድ የሆነ ግድ የለሽነት ውስጥ ይገባል። የሚኖርለት ሃሳብ ሲኖር ግን ካለበት ጉዳይ ጋር የሚያዛምደው ብቻውን ሳይሆን በሱ እቅፍ ስር ያሉትን ያገናዘበ ውሳኔዎቹን ያደርጋል። ሰው ለራሱ የሚሆነው እስከ ትንሽ ጊዜ ነው። ከዛ መሰላቸት ቸል ማለት ተስፋ ማጣት ይጠናወተናል ለሰው ለመኖር ነው የተፈጠርነው ። በ አቅራቢያችን የተረፉትን ስመለከት ተፈጥሮን የተከተሉ ናቸው። ተፈጥሮን መከተል ልክ ነው።" - እሱባለው ይታየው

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Esubalewu
8ኛው የኦዳ አዋርድ በፊንፊኔ ሸራተን ሆቴል ትናንት ተካሄደ።

የጉቱ አበራ 'Gaaffii Koo'' የተሰኘው አልበም የ2016 የአመቱ ምርጥ አልበም በመባል ተመርጧል።

አንዱአለም ጎሳ በምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ እና በምርጥ ነጠላ ዘርፍ “Bilillee” በተሰኘው ዘፈኑ ሁለት ሽልማቶችን አግኝቷል።

የ2016 የአመቱ ምርጥ የቡድንና ጥንድ ዘፈን አደም መሀመድ መሃመድ እና ጫልቱ ቡቶ “Gadaa Malee” በተሰኘው ዘፈን ተሸልመዋል።

በየአመቱ ተወዳጅ ዘፈን ዘርፍ ዮሳን ጌታሁን “ባላ ጊዜ” በተሰኘ ዘፈን አሸናፊ ሆኗል።

ምርጥ የሴት ዘፋኝ በመባል ለምለም ሃይለሚካኤል፣ ምርጥ አዲስ ዘፋኝ በመባል ደግሞ አሳንቲ አስቹ አሸናፊ ሆነዋል።

በምርጥ ዘመናዊ ዘፈን ደግሞ C Boy “አጀብ” በተሰኘ ዘፈን አሸንፏል።

ምርጥ ልበወለድ በመባል የጂኔኑስ ደጀኔ “Gungummii Eelaa” የሰኘ ልበወለድ አሸንፊ ሲሆን፤ በምርጥ የግጥም ስብስብ መፅሐፍ ደግሞ የገመቹ ተሊላ “Miilas Miilaanis” መፅሐፍ አሸናፊ ሆኗል።

አርቲስት እልፍነሽ ቀኖን ጨምሮ ሶስት አርቲስቶች የኤድሜ ልክ ሽልማት ተሸልመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በኦዳ አዋርድ ለ8 የምስራቅ አፍሪካ አርቲስቶች ሽልማት ተበርክቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #odaaward
ምስጋና ከ ልኡል ሲሳይ

"ልዑል የሙዚቃ አልበም ከወጣ ዛሬ አንድ ዓመቱን አስቆጥሯል ተመስገን 🙏🏾

በብዙ ፍቅር እና መዉደድ የምወዳችሁ የማከብራችሁ የሙዚቃዬ ወዳጆች አድናቂዎች ለድጋፋችሁ በጣም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ያክብርልኝ!"

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Leulsisay
ለተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ 5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል በፍርድ ቤት የተወሰነበት ድርጅት መክፈል እንደማይችል አሳወቀ።

ለረጅም ጊዜ የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ላየን ፕሮሞሽን የተሰኘው ድርጅትእና የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጌታነህ አንዳርጌ ከቴዲ አፍሮ ጋር በነበራቸው የፍትሐብሔርክስ ክርክር ላይ ፍርድ ቤቱ ለድምፃዊው 5 ሚሊዮን ብር ሊከፈለው ይገባል ሲል ጥቅምት 6 ቀን 2016 አ.ም ወስኖባቸው ነበር።

በዚህ ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኙት አቶ ጌታነህ አንዳርጌ ይግባኝ ጠይቀን ለጥር 27 ቀጠሮ ተሰጥቶናል በተጨማሪም ድርጅቱ አሁን ላይ ምንም አይነት ስራ እየሰራ ባለመሆኑ ገንዘብ የለውም ስለዚህም ገንዘቡን መክፈል አይችልምሲሉ አስታውቀዋል።

ክሱ የተጀመረው ኢትዬጲያ ወደ ፍቅር ጉዞ የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የካቲት 14 ቀን 20012 አ.ም በመስቀል አደባባይ የተደረገውን ኮንሰርት በማስመልከት በፅሁም ስምምነቱ መሰረት ለቴዲ አፍሮ 10 ሚሊዮን ብር እንደሚከፈለው የተገለፀ ቢሆንም ነገር ግን ገንዘቡ ሳይከፈለው መቅረቱን በማስመልከት ክስ ተመስርቶ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_afro
ኢትዮጲያዊውያን የሙዚቃ ባለሙያዎች ከክሮሺያውኑ ሙዚቀኞች ያጣመረው አልበም ለሙዚቃ አፍቃሪያን ሊደርስ ነው

ዝነኛው የባህል ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቹ እና በተለየ የማሲንቆ አጨዋወት ስልቱ የሚታወቀው ሀዲስ አለማየሁ (ሀዲንቆ) በሙሉ የበኩር አልበም ስራውን እንዳጠናቀቀ አስታወቀ፡፡

አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የአልበም ስራው እንደተጠናቀቀ ያስታወቀው ሙዚቀኛው ከኢትዮጲያውን በተጨማሪ የተለያየ ሀገር የሙዚቃ ባለሙያዎች ተሳትፎ እንዳደረጉበት አስታውቋል፡፡

የክሮሺያ ሁለት ባንዶችን ጨምሮ የዴንማርክ፤ የጃፓን፤ የአሜሪካ እና ጃማይካ የሙዚቃ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የተናገረው ሀዲስ አለማየሁ በአልበም ስራው ውስጥ የተለያየ ስልተ ምት ያላቸው ሙዚቃዎች እንደተካተቱበት በተጨማሪነት አንስቷል፡፡

በርካታ የሙዚቃ መሳሪያዎች ቢካተቱበትም የማሲንቆ ድምፅ ጎልቶ እንዲወጣ እንዲሰማ መደረጉን ያስታወቀ ሲሆን ክዚህ ቀደም በማሲንቆ ብቻ ከተሰሩ ስራዎች አንፃር ምስስሎሽ እንዳይኖረው ለማድረግ መሞከሩን ሙዚቀኛው አስታውቋል፡፡

ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ክሮሺያዊው የሙዚቃ ባለሙያው በአልበም ስራው ውስጥ በፕሮዲውሰርነት እንደተሳተፉበት የተናገረ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለሙዚቃ ወዳጆች እንደሚቀርብ በተጨማሪነት ገልጿል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #masinqo #haddis_alemayehu
ዝነኛው ፈንድቃ በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ስራ መጀመሩን አስታወቀ

በካዛንቺስ ለበርካታ አመታት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ፈንድቃ ባህል ማዕከል በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል አገልግሎት መስጠቱን ዛሬ ሕዳር 29/2017 ዓም በተሰጠ መግለጫ አስታውቋል።

የባህል ማዕከሉ መስራች መላኩ በላይ እንደገለፀው ሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ፈንድቃን በሃያት ሪጀንሲ እንድንገነባ የፈቀዱ የሆቴሉን ስራ አስኪያጅ ከሪምን አመስግነው በካዛንቺስ ሲሰጥ የነበረው ሁሉም ፕሮግራም በሃያት ሪጀንሲ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ከሰኞ እስከ እሁድ ምሽት ፕሮግራሞች የሚኖሩ ሲሆን መግቢያ ዋጋ በካዛንቺስ እንደነበረው 200 ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን መግቢያ በር በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በኩል እንደሆነም እውቁልኝ ብሏል።

ካዛንቺስ የነበረው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ቦታው እኛ እንድናለማ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቦታውን ከእኛ ሰጥቶኛል ለዚህ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እናመሰግናለን ሲል መላኩ በላይ ምስጋና አቅርቧል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #fendika
ዛሬ የሙዚቃ ልደቷ ነው !
ታህሳስ 1/1970- ♾️

ስለ ሙዚቃ እና ሙዚቀኝነት ሲነሳ ተስጥኦ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል በእውነተኛ ሙዚቃ ውስጥ ሀሳብ ስሜት እውነት ፍቅር ይስተጋባል በሙዚቃ ሀገር ይገነባል ትውልድ ይቀረፃል ለትውልድ ደግሞ ታሪክ ይሰነድበታል እንዲህ ባለው ጠቃሚ ኢንዱስትሪ ላይ ከተከሰቱ እና በአጭር ጊዜ ብዙ እርምጃዎችን ከተራመዱ ሙዚቀኞች መሀል ኤልያስ መልካ ግንባር ቀደሙ ነው ። በዚህ ኢንዱስተሪ ላይ እንደ ኤልያስ መልካ ያለ ተስእጦን ከረቀቀ የሙያ ጥግ እና ከተሟላ ስብእና ጋር የተላበሰ ሙያተኛን ማግኘት መቻል ደግሞ እንደ ሙዚቃ አድማጭ በእጅጉ እድለኝነት ነው።

ኤልያስ መልካ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ላይ ምን ማለት እንደነበር እሱን ከማጣት በላይ ማሳያ አለ ብዬ አላምንም(ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሰማኝ ያለው ይህ ነው)

ጊታሪስት፣ኪቦርዲስት፣ቤዚስት፣ፒያኒስት፣ቼሎ ተጫዋች የሙዚቃ አቀናባሪ የዜማ እና ግጥም ደራሲ የላቀ ሀሳብ አመንጪ የባለሙያው መብት ተሟጋች ሙዚቃን በዲጂታል መንገድ የማገበያየት ሀሳብ ፈጣሪ (እንተርፕርነር) ወዘተ በመሆን ሀገሩን በትጋት በማገልገል በሙዚቃችን ላይ የማይተካ አይነተኛ ሚናን ተጫውቷል ።

ውድ ኤልያስ መልካ እንኳንም ተወለድክልን መልካም የ47ኛ አመት ሰማያዊ ልደት !!!💜💜💜

የኤልያስ መልካ አድናቂዎች ህብረት !!

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Elias_melka
"የደጋ ሰው"
የየማ የመጀመሪያ አልበም በፈረንሳይ 🇫🇷 ሀገር በሲዲ ታተመ

#Ethiopia | "የደጋ ሰው" የተሰኘው የየማ የመጀመሪያ አልበም በተለያዩ መተግበሪያዎች ከተለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንሳይ ሀገር በሲዲ ታተመ።

“በዲጂታል ዘመን ሙዚቃዎቼ ታትመው በእጄ ሳገኛቸው ስሜቱ የተለየ ነው። “ ስትል በማህበራዊ ገፇ የማ አስፍራለች።

በቅርቡ በዩኤስቢ እና በሽክላ የሚታተም ይሆናል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yema #eyuel_mengistu #yedegasew