ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
494 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
አመሰገኑ

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ስራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሰገኑ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት የኮሪደር ልማት ስራዎቻችን የእያንዳንዱ ቀን እና ምሽት ስራ እየተገመገመ የሚስራ ስራ መሆኑን ገልጸው ፤ ልማቱ ለመረጠን እና ቃል ለገባንለት የከተማችን ነዋሪ የኢኰኖሚ ፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ፤ከዘመናዊነት ጋር የተቃኘ አሰራርን በመዘርጋት እና በማሳለጥ ለከተማችን የኢኮኖሚ እድገት ወሳኙን ሚና እንድንወጣ ያስቻለን ነዉ ብለዋል፡፡

በሂደቱም በምታደርጉት ተሳትፎ በአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ታሪካዊ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ መሆናችሁን ተረድታችሁ ስራውን በፍጥነት ብቻ ሳይሆን በጥራት እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ ብለዋል።

በታሪክ ሂደት የከተማዋን የሥራ ባህል በቀየርንበት ፤ ቀንና ለሊት በስራችሁበት ጎን ለሥራ ጥራት የምትሰጡት ትኩረት እንዲሁ ባህል ሆኖ መቀጠል እንዲችል መስራት አለብን ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ ሳይት በየምሽቱ በሥራ ላይ ለነበሩ ሰራተኞችን የእራት ግብዣ እያደረጉ ያሉትን የአካባቢውን ነዋሪዎች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#Ethiopia

በነዳጅ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መከልከሉ ይታወቃል።

ይኸው ክልከላ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችን እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።

ምንም ዓይነት የሕግ ድንጋጌ ሳይኖር ወይም ግልጽ የሆነ ሕግ ሳይወጣ እና ሕግን የተከተለ ክልከላ ሳይኖር ' ከላይ በወረደ ወይም ተሰጠ ' በተባለ አቅጣጫ ላይ ብቻ በመመሥረት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ መከልከሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችን እያተጓጎለ እንደሆነ ጠቁሟል ኮሚሽኑ።

ኮሚሽኑ ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ እንድሂህ ብሏል ፦

- በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል፣ በሕግ አግባብ ወይም ድንጋጌ የታገዘ አይደለም፡፡

- ለማንኛውም አይነት አገልግሎት የሚውሉ ከባድ የጭነት ተሽከርኮሪዎች፣ የእርሻ ትራክተሮችና ለቱሪስት ማስጎብኛ የሚያገለግሉ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን መከልከል ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ነው፡፡

- በግብርና ፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ፣ በሆልቲካልቸር ፣በቱሪዝም ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ በግንባታ እና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው።

- በተለይ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ልዩ ባህሪ የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት እንዲቻል ሚኒስቴሩ ፈቃድ ሊሰጥ ይገባል።

#ReporterNewspaper

@tikvahethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
ትኩረት- ለወባ- በሽታ!!!

#Ethiopia | የወባ ወረርሽኝ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል !

የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል መወሰድ ያለባቸው ተግባራት እንደሚከተለው ቀርቧል

👉አጎበርን በአግባቡ መወጠርና ሁሌም
በአግባቡ መጠቀም

👉በፀረ-ወባ ኬሚካል በተነከረ አጎበር
ውስጥ መተኛት

👉የአጎበር አጠቃቀም ላይ ለነፍሰጡር.
እናቶችና ለህጻናት ቅድሚያ መስጠት

👉አጎበርን ለታለመለት አላማ በማዋልና
መጠቀም

👉የቤት ውስጥ የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል
ቤትዎን ማስረጨት
👉በጸረ-ወባ ኬሚካል የተረጨ ግድግዳ ላይ
እስከ 6 ወር ቀለም አለመቀባት፣ እበት
ባለመለቅለቅ፣ በወረቀት አለመሸፈን

👉በግቢዎና በአካባቢዎ ያሉ ዉሃ የሚያቆሩ
ቦታዎችንና ቁሳቁሶችን እንደ መኪና ጎማ፣
የሸክላ ስባሪዎች፣ የወዳደቁ ጣሳዎች
ማስወገድ፣ ማፋሰስ፣ መደልደል

👉ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ማላብ፣ ራስ
ምታት፣ የሰውነት መጓጎል፣ ማቅለሽለሽና
ማስመለስ የወባ በሽታ ምልክቶች ሊሆኑ
ስለሚችሉ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና
ተቋም በመሄድ ምርመራ ያድርጉ።

👉በምርመራ የወባ በሽታ መሆኑ ከተረጋግጠ
በጤና ባላሙያ በታዘዘሎት መሰረት
መድኃኒቱን ጨርሶ መውሰድ

👉በወባማ አካባቢዎች ከአንድ ወር በላይ
ቆይተው ሲመለሱ የወባ በሽታ ምርመራ
በማድረግ ራስዎን ቤተሰቦን እና
ማህበረሰቡን ከወባ በሽታ ይከላከሉ:


Via ጌጡ ተመስገን

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
በአዲስ አበባ ከተማ ኮድ 2 በፈረቃ ሊሆን ነው

#Ethiopia | በአዲስ አበባ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት፤ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው፡፡

በከተማዋ ጠዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡

ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል ያሉት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ሁነት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያሌው እቴሳ ናቸው፡፡

እቅዱ በ2 እና በ3 ወር ጊዜ ውስጥ፤ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካራች በፈረቃ አንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የኦሮሚያንና የፌዴራልን ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755 ሺ በላይ ናቸው ያሉት አቶ አያሌው ከእነዚህ ውስጥ የበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጠዋትና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ሲሉም ለሸገር ተናግረዋል፡፡

Via ሸገር ኤፍኤም

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
አይ ቴክኖሎጂ😱😱

የሚስቱን ውስልትና በድሮን ታግዞ ያወቀው ባል

#Ethiopia | ሚስቴ የተለየ ባህሪ አሳይታለች በሚል መከታተል የጀመረው ባል በመጨረሻም ከአለቃዋ ጋር እንደምትወሰልት ደርሶበታል

አል-ዐይን

ባልየው በድሮን ታግዞ ባደረገው ክትትል በቅርቡ የደመወዝ ጭማሪ ካደረገላት ሌላ ባለትዳር ጋር ስትወሰልት የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል ለቋል

የሚስቱን ውስልትና በድሮን ታግዞ ያወቀው ባል

ጂንግ በመባል የሚጠራው ቻይናዊ ሰው ስሟ ካልተጠቀሰችው ባለቤቱ ጋር በትዳር ተሳስረው እየኖሩ ነበር፡፡

በአንድ ህንጻ ላይ ነገር ግን በተለያዩ ተቋማት ተቀጥረው ሲሰሩ የተዋወቁት እነዚህ ጥንዶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ፍቅራቸው ንፋስ ገብቶበታል፡፡

ባልተለመደ መልኩ ቤተሰቦቼን ልጠይቅ እየሄድኩ ነው በሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ለባሏ የምታቀርበው ይህች ሚስት ለመዝናት በባሏ ስትጠየቅም ይቅርታ እየጠየቀች እንደማይመቻት ስትናገር ነበርም ተብሏል፡፡

የሚስቱን ባህሪ መቀያየር ያስተዋለው ባልም በተለያዩ መንገዶች መከታተል ይጀምራል፡፡ ለዚህ ውጥኑም በድብቅ በድሮን የታገዘ ክትትል ሲያደርግየቆየው ባል በመጨረሻም ከአንድ ሰው ጋር ወደ ተሽከርካሪ ስትገባ ያያል፡፡

እስከ መጨረሻው ባደረገው ክትትልም ሚስቱ ከሌላ ሰው ጋር እየወሰለተች መሆኑን ያወቀ ሲሆን በሰውየው ላይ ባደረገው ክትትልም

ሚስትየው ከአለቃዋ ጋር ሆና ወደ ተለያዩ መዝናኛ ቦታዎች ሲገቡ እና ሲወጡ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መለቀቃቸውን ተከትሎ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

via ጌጡ ተመስገን

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
ለተሽከርካሪ የማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመ አሽከርካሪ ተቀጣ

AMN- ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም

በትናትናው ዕለት ከረፋዱ 5:45 አካባቢ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለተሽከርካሪ በማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመው ግለሰብ በደንብ ማስከበር ተቀጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከመንግሥት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በልማቱ ላይ በባለቤትነት እንደሚሳተፍ ሁሉ በመሰረተ ልማት ጥበቃ ዙሪያም በንቃት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህዝቡ ጋር በመተባበር መሰረተ ልማቶች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ የማድረግ ስራውን በሁሉም አማራጮች ትምህርት መስጠትን ጨምሮ ህጉን የሚተላለፉትን አሽከርካሪዎች እና እግረኞችን በህጉ መሰረት አስፈላጊውን መቀጮ እየሰጠ መሄዱን እንደሚቀጥል ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#Addisababa
#Ethiopia
ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
የአፋልጉኝ ተማጽኖ

#Ethiopia | ባለቤቱ ፦ ሲሳይ እንዳለዉ ይባላል

ታርጋ፦66348
የጠፋበት ቦታ፦ ገርጅ ታክሲ ተራ ወረዳ 13
የተመለከተበት ፖሊስ ጣቢያ፦ገርጅ ፖሊስ ጣቢያ ወረዳ 13

ስልክ፦0930111154
0912005445

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
👍1
በባንክ የምዛሬ ዋጋ በስንት ጨመረ ?

የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ከመደረጉ ከ3 ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ4895 ሳንቲም ነበር ፤ መሸጫው 58 ብር ከ6393 ሳንቲም ነበር።

አሁን ማሻሻያውን ተከትሎ በዛሬው የምናዛሬው ተመን አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ 74 ብር ከ7364 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 76 ብር ከ2311 ሳንቲም ሆኗል።

የአንድ ፓውንድ መግዣ ዋጋ 70 ብር ከ6759 ሳንቲም ፤ መሸጫው 72 ብር ከ0894 ሳንቲም የነበረ ሲሆን በዛሬው የባንክ ምንዛሬ መግዣው 91 ብር 8787 ሳንቲም ፤ መሸጫው 93 ብር ከ7162 ሳንቲም ሆኗል።

አንድ ዩሮ በ62 ከ3359 ሳንቲም ይገዛ ፤ በ63 ብር ከ5856 ሳንቲም ይሸጥ የነበረ ሲሆን በዛሬው የባንክ ምንዛሬ መግዣው 81 ብር ከ0367 ሳንቲም ፤ መሸጫው 82 ብር ከ6574 ሳንቲም ሆኗል።

#ETHIOPIA

@tikvahethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
👍1
የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣን በሽታ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆኑን አወጀ

#Ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋ ያለውን የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ሲል አውጇል፡፡

ቫይረሱ በኮንጎ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋና ህጻናትና ጎልማሶች በበሽታው እየተያዙ መሆኑም ተሰምቷል፡፡

በአህጉሪቱ ያለው የክትባት መጠን ጥቂት እንደሆነ የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው።

በዚህ ሣምንት የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት (ሲዲሲ አፍሪካ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ የህዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋ መሆኑንና ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች ሲያዙ፤ 524 ሰዎች በዚሁ ምክንያት መሞታቸውን በመግለጽ ዓለም አቀፍ ድጋፍ መጠየቁ ይታወሳል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፥ በሽታው ሁሉንም ሊያሳስብ እንደሚገባ ጠቅሰው፤ ከአፍሪካ አልፎም የበለጠ የመስፋፋት እድሉ በጣም

ሲዲሲ አፍሪካ በፈረንጆቹ 2024 በ13 ሀገራት ውስጥ በሽታው መከሰቱን ገልጾ፥ ቀደም ካለው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በበሽታው የተያዙ ሰዎች 160 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል።

በበሽታው ምክንያት የሚከሰተው ሞት ደግሞ በ19 በመቶ ከፍ ማለቱም ነው የተገለጸው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ የአደጋ ጊዜ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲሚ ኦርጋና እንዳሉት፥ ቀደም ሲል በሽታው ባልነበረባቸው ሀገራት እንደ ዩጋንዳ፣ ርዋንዳ፣ ብሩንዲ እና ኬንያ ባሉ ሀገራት

በፈረንጆቹ 2022 በሽታው ሲከሰት ከ70 በላይ ሀገራትን ሲያጠቃ ከ1 በመቶ ያነሱ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ዘገባው አስታውሷል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
የሞት አደጋ
5 ሺህ ብር የነበረዉ አሁን ወደ 250 ሺህ ብር ከፍ ብሏል

#Ethiopia | በሰው ላይ ለሚደርስ የሞትና የአካል ጉዳት የሚከፈለው ካሳ መጠን ወደ 250 ሺህ ብር ከፍ ብሏል።

አዲሱ የሦስተኛ ወገን የተሸከርካሪ መድን ፖሊሲ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን መጀመሩን ተገለፀ።

5 እጥፍ ጭማሪ የተደረገበት የአርቦን ክፍያ በአንድ ሰው ላይ ለሚደርስ የሞት አደጋ 5 ሺህ ብር የነበረዉ አሁን ወደ 250 ሺህ ብር ከፍ እንዲል ሆኗል።

በአዲሱ ደንብ መሰረት በአንድ ሰው ላይ ለሚደርስ ለአካል ጉዳት እስከ ብር 40 ሺህ ያልበለጠ የገንዘብ ካሳ ይከፈል የነበረ ቢሆን አሁን ግን 250 ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጓል።

እንዲሁም በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ወይም ኪሳራ ከብር 100 ሺ ያልበለጠ የገንዘብ ካሳ የሚከፈል የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 200 ሺህ ብር ከፍ ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል።

በስራ ላይ የነበረዉና የሚኒስትሮች ምክርቤት በአዋጅ ቁጥር 799/2002 የተሸከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ዋስትና የአርቦን መጠንና የመድን ፈንድ ታሪፍን በተመለከተ ያስተላለፈው ዉሳኔ በአዲሱ ደንብ መሻሩ ታዉቋል።

ስናሽከረክር ጠንቀቅ ማለቱ ይበጃል!

via getu temsgen

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
የዘመን መለወጫን የበዓል ገቢያ ለማረጋጋት 50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይቱ ወደ ኢትዮጵያ መግባት ጀመረ

#Ethiopia | የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግስት ግዢ የተፈጸመው 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ የተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ዛሬ ጀምሯል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ እንዳስታወቀው፤ ከዚህ ቀደም መንግስት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻል እና ገበያን ለማረጋጋት ተከታታይነት ያለው እርምጃ እንደሚወስድ ቃል በገባው መሠረት 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ የተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ዛሬ ጀምሯል።

የምግብ ዘይቱ በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር እና በመኪና ተጭኖ ወደ አገራችን መግባት የጀመረ ሲሆን፣ ይህ የፍጆታ ዕቃ በዋናኝነት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግስት ግዢ የተደረገ ነው ተብሏል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ጋር በመቀናጀት በሚቀጥሉት ጊዜያት በተቀላጠፈ መልኩ 50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የሚሰራጭ እንደሚሆን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድረ ገጹ ላይ ጠቁሟል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
👍1
በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በትራንስፖርት አቅርቦት ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተደረገ

#Ethiopia | በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሰረት በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በትራንስፖርት አቅርቦት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክሱ የሚመለከተው ከአንድ ቤተሰብ ወርሃዊ አማካይ ፍጆታ በላይ ኤሌክትሪክ እና ውሃን በብዛት የሚጠቀመው የመክፈል አቅም ያለው የህብረተሰብ ክፍል ነው ተብሏል፡፡

መንግስት አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል በመኖሪያ ቤቱ የሚጠቀመውን አማካይ ወርሃዊ የውሃና ኤሌክትሪክ ፍጆታ ከታክሱ ነፃ የሚያደርግ ሲሆን ከታክሱ ነፃ ከተደረገው በላይ የውሃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ የትራንስፖርት አገልግሎትም ተጨማሪ እሴት

ሚኒስቴሩም የትራንስፖርት አገልግሎትም ላለፉት 22 ዓመታት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆን የተደረገው አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለትራንስፖርት የሚያወጣው ወጪ እንዳይንር እንዲሁም በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚከፈለው ታክስ የዕቃዎችን ዋጋ መናር እንዳያስከትል በማሰብ ነበር ብሏል፡፡

በመሆኑም ከህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ውጪ ለሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች የዚህ አይነቱን ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ባለመሆኑ፣ መንግስት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የመሆን መብት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር ከስምንት መቀመጫ በላይ ያላቸው ተሸከርካሪዎች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Via getu temsgen

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
🤔1
የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን የተመለከተ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ ሊውል ነው

AMN-ነሐሴ 25/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከብልሹ አሰራር እና ከደህንነት ስጋት የጸዱ እንዲሆኑ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ ሊያውል መሆኑን አስታወቀ፡፡

የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች የአሰራር፣ አደረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የዲሲፕሊን አፈጻጸም መመሪያ ማስፈጸሚያ ማኑዋል ላይ የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሂደዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ፣ የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች ከነዋሪው ዘንድ በተለያዩ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲነሳባቸው እንደቆየ ገልጸው፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በዘርፉ የሚስተዋለውን የህግ ጥሰት እና ወንጀል ለመከላከል መመሪያው ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ታርጋ ሳይለጥፉ አልያም ህገወጥ ታርጋ በመለጠፍ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ተሳታፊዎች መመሪያው ጠንካራ ህጋዊ ክትትል እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ከማድረግ አኳያም የላቀ ሚና አለው ብለዋ


በሃብታሙ ሙለታ

#Addisababa
#Ethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
የአፍሪካ ህብረት የተያዙበት መኪኖች እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ መንግስትን ጠየቀ

#Ethiopia | የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በፃፉት ደብዳቤ በጅቡቲ ወደብ እና በአዲስ አበባ ጉምሩክ የተያዙት የአፍሪካ ህብረት መኪናዎች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

ኤሌክትሪክ ያልሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ ኢትዮጵያ ያወጣችው እገዳ ይፋ ከመሆኑ በፊት የታዘዙ ቢሆንም አሁን ላይ ተግባራዊ በሆነው ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፖሊሲ ምክንያት ለወራት ተይዘዋል ብለዋል።

ሙሳ ፋኪ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ተሽከርካሪዎችን ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተደነገገበትን ስምምነት እየጣሰች ነው ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፖሊሲው ቀድመው በታዘዙ ተከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መደረግ እንደሌለበት አፅንኦት ሰጥተው በአፍሪካ ህብረት ስራ ላይ ተጨማሪ መስተጓጎልን ለመከላከል ፈጣን እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የነዳጅ ተሸከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ አወዛጋቢ በሆነ መልኩ እገዳ ማውጣቱ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ለማስገባት የያዘችው አቋም ላይ ዲፕሎማቶችን እና አስመጪዎችን ግራ ያጋባ መሆኑ ይታወቃል።

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበሩ ጉዳዩን ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እና የኢትዮጵያን የአፍሪካ ህብረት ዋና ፅህፈት ቤት አስተናጋጅ ለመሆን የገባችውን ቃል እንዲያስከብሩ ጠይቀዋል።
#ቅዳሜገበያ


ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር አዋሽ አካባቢ ጉዳት አጋጥሞታል

#Ethiopia | የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር አዋሽ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ፡፡

15 ሜትር ርዝመት ያለው የባቡር ሃዲዱ ብረት ወደ መሬት መስጠሙን እና አንዳንድ የሃዲዱ ማሰሪያዎች መቆራረጣቸውም ተገልጿል፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) የጉዳት መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተፈጠረውን መጠነኛ ጉዳት በፍጥነት በማስተካከል መስመሩን ወደ ሙሉ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር አዋሽ አካባቢ ጉዳት አጋጥሞታል

#Ethiopia | የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር አዋሽ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ፡፡

15 ሜትር ርዝመት ያለው የባቡር ሃዲዱ ብረት ወደ መሬት መስጠሙን እና አንዳንድ የሃዲዱ ማሰሪያዎች መቆራረጣቸውም ተገልጿል፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) የጉዳት መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተፈጠረውን መጠነኛ ጉዳት በፍጥነት በማስተካከል መስመሩን ወደ ሙሉ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡


ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን አውሮፕላን ሊረከብ ነው

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውና ''Ethiopia land of origins'' በሚል መጠሪያ የተሰየመውን ኤ350-1000 የመንገደኞች አውሮፕላን በተያዘው ጥቅምት ወር ከኤርባስ ኩባንያ እንደሚረከብ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት፣ አየር መንገዱ በአፍሪካ የአቪዬሽን መስክ ያለውን የቀዳሚነት ድርሻውን ለማስቀጠል በየጊዜው አዳዲስ አውሮፕላኖችን በማስመጣት እንዲሁም ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን በማስፋት ላይ ይገኛል።

በዚህም አየር መንገዱ በቅርቡ ከኤር ባስ ኩባንያ የሚረከበው የኤ350-1000 አውሮፕላንም በአይነቱ ልዩና በአፍሪካ የመጀመሪያው ስለመሆኑ አንስተዋል።

አየር መንገዱ ኤ350-900 አውሮፕላኖችን መጠቀም ከጀመረ ሰባት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ አሁን ላይ ሃያ የኤ350- 900 አውሮፕላኖች በስራ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኤ350-1000 አውሮፕላን ደግሞ 400 መቀመጫዎች ያሉት እና ለደንበኞች የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አየር መንገዱ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2035 በዓመት 67 ሚሊዮን መንገደኞችን በማጓጓዝ 25 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት እየሰራ ነው።

በአሁኑ ወቅትም ባሉት 147 አውሮፕላኖች 139 ዓለም አቀፍና 22 የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
የ "ፋይዳ" መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ መሆኑን አስታወቀ

#Ethiopia | የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ደንበኞች "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተቋሙ ባወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡

በመሆኑም ከህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ደንበኞች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ማሳሰቡን ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ እና ከቦሌ ወደ መገናኛ አደባባይ በሁለቱም አቅጣጫዎች ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኗል-ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

#Ethiopia | ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ እና ከቦሌ ወደ መገናኛ አደባባይ በሁለቱም አቅጣጫዎች ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።

በመገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት የሚያግዝ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታ ተጀመሯል ተብሏል።

እግረኞች በሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ በኩል ማለፍ ስለማይቻል በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ባለው የእግረኛ መንገድ እንዲጓዙ ባለስልጣኑ አሳስቧል።

አሽከርካሪዎችም ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ማሳሰቡን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ለጥንቃቄ🚨

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ?

➡️ ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦ ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

➡️ በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦ በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

➡️ በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

➡️ መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።


#Ethiopia
#የአአእሳትናአደጋስራአመራርኮሚሽን

@ትክቫሄትህኦፕአ


ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
መንግሥት የሕዝብ ትራንስፖርትን አገልግሎቱን ለውጪ ባለሀብቶች ክፍት ሊያደርግ መሆኑ ተጠቆመ

#Ethiopia | የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የሕዝብ ትራንስፖርትን አገልግሎትን ለውጪ ባለሀብቶች ክፍት ሊያደርግ መሆኑን ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚሰማሩ ባለሀብቶች እየቀነሱ መምጣታቸውን ተከትሎ፤ ይህንን ችግር ለመቀነስ ሌሎች አማራጮችን መመልከት ተገቢ በመሆኑ የትራንስፖርት ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረግ ማስፈለጉን ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በዘርፉ የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች እጥረት መኖሩን ያነሱት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የትራንስፖርት አገልግሎትና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪ አሰፋ ሀዲስ፤ የተለያዩ ማበረታቻዎችን በማቅረብ ባለሀብቱን ወደዘርፉ ለመቀላቀል እየተሰራበት እንደሚገኝ ለአሐዱ ገልጸዋል።

ኅብረተሰቡን በሚመጥን መልኩ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ለማድረግ ሰፊ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝና መንግሥት ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግም ለአዳዲስ አሰራሮች ሰነድ ተዘጋጅቶ መቅረቡን ተናግረዋል።

በዚህም መሰረትም የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን ከማበረታታት በተጨማሪ የውጪ ባለሀብቶችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት በዘርፉ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ከዚህ በፊት ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ብቻ የሚፈቀዱና ለውጪ ኢንቨስተሮች ዝግ የነበሩ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመጠቀም ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆንም ሆነ ለብቻቸው ገብተው ኢንቨስት ማድረግ እንዲችሉ፤ ዘርፉን ክፍት የማድረግ ሥራ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በጋራ እየተሰራበት እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የውጪ ባለሀብቶችን ወደሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚደረገው አሰራር ገና እንዳልፀደቀ የጠቀሱት የትራንስፖርት አገልግሎትና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪው፤ በተለይም ከ45 ወንበር በላይ የሚይዙ ተሽከርካሪዎችን ክፍት ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በመሆኑም አዋጁ ፀድቆ ወደሥራ ሲገባ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የሆነ አማራጭን ሊሰጥ የሚችል እንደሚሆን በመጠቆም፤ በዚህ ዙሪያ የውጪ ባለሀብቶችም ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚታሰብ አማካሪው ለአሐዱ አስታውቀዋል።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

"""""""""""***""""""""""
ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth