የአፍሪካ ህብረት የተያዙበት መኪኖች እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ መንግስትን ጠየቀ
#Ethiopia | የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በፃፉት ደብዳቤ በጅቡቲ ወደብ እና በአዲስ አበባ ጉምሩክ የተያዙት የአፍሪካ ህብረት መኪናዎች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።
ኤሌክትሪክ ያልሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ ኢትዮጵያ ያወጣችው እገዳ ይፋ ከመሆኑ በፊት የታዘዙ ቢሆንም አሁን ላይ ተግባራዊ በሆነው ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፖሊሲ ምክንያት ለወራት ተይዘዋል ብለዋል።
ሙሳ ፋኪ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ተሽከርካሪዎችን ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተደነገገበትን ስምምነት እየጣሰች ነው ብለዋል።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፖሊሲው ቀድመው በታዘዙ ተከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መደረግ እንደሌለበት አፅንኦት ሰጥተው በአፍሪካ ህብረት ስራ ላይ ተጨማሪ መስተጓጎልን ለመከላከል ፈጣን እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል።
የትራንስፖርት ሚኒስቴር የነዳጅ ተሸከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ አወዛጋቢ በሆነ መልኩ እገዳ ማውጣቱ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ለማስገባት የያዘችው አቋም ላይ ዲፕሎማቶችን እና አስመጪዎችን ግራ ያጋባ መሆኑ ይታወቃል።
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበሩ ጉዳዩን ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እና የኢትዮጵያን የአፍሪካ ህብረት ዋና ፅህፈት ቤት አስተናጋጅ ለመሆን የገባችውን ቃል እንዲያስከብሩ ጠይቀዋል።
#ቅዳሜገበያ

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth