ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
494 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba

ጓደኛቸውን #በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ተያዙ።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ ነው።

ጓደኛማቻቾቹ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ  ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ  ቴዎድሮስ ታከለ እና  ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን  አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል  ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል።

ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡

አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡

ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ካበናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ " ወለቴ " ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት አረጋግጧል።

መኪናውም ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማወል ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ነገ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች ይኖራሉ።

ስለሆነም ነገ ለስራ፣ ለቤተሰብ ለጓደኛ ጥየቃ ለሌላም ጉዳዮች ፕሮግራም የያዛችሁ ፕሮግራማችሁን ከልሱ።

መንገድ የሚዘጋው " ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም " በሚል የጎዳና ላይ ሩጫ ስለሚካሄድ ነው።

ሩጫው መነሻውን መስቀል አደባባይ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ከዛም በባምቢስ፣ ዑራኤል አደባባይ ወደ ቀኝ፣ ፒኮክ መናፈሻ ፣

በዚህም ፦
- ከ22 ወደ ዘሪሁን ህንፃ
- ከዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ
- ከአትላስ መብራት ወደ ዑራኤል አደባባይ
- ከቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ወደ ወሎ ሠፈር
- ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ
- ከኤግዚብሽን ወደ ፊላሚንጎ
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቴሌ ማቋረጫ (ክቡ) ባንክ ወደ ስታድየም
- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከካዛንቺስ ሼል (ኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል) ወደ ባምቢስ
- ከዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:30 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ከዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በተጠቀሱ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia

ቴዘርን የመኪና መቆጣጠሪያ GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
ለተሽከርካሪ የማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመ አሽከርካሪ ተቀጣ

AMN- ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም

በትናትናው ዕለት ከረፋዱ 5:45 አካባቢ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለተሽከርካሪ በማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመው ግለሰብ በደንብ ማስከበር ተቀጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከመንግሥት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በልማቱ ላይ በባለቤትነት እንደሚሳተፍ ሁሉ በመሰረተ ልማት ጥበቃ ዙሪያም በንቃት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህዝቡ ጋር በመተባበር መሰረተ ልማቶች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ የማድረግ ስራውን በሁሉም አማራጮች ትምህርት መስጠትን ጨምሮ ህጉን የሚተላለፉትን አሽከርካሪዎች እና እግረኞችን በህጉ መሰረት አስፈላጊውን መቀጮ እየሰጠ መሄዱን እንደሚቀጥል ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#Addisababa
#Ethiopia
ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን የተመለከተ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ ሊውል ነው

AMN-ነሐሴ 25/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከብልሹ አሰራር እና ከደህንነት ስጋት የጸዱ እንዲሆኑ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ ሊያውል መሆኑን አስታወቀ፡፡

የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች የአሰራር፣ አደረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የዲሲፕሊን አፈጻጸም መመሪያ ማስፈጸሚያ ማኑዋል ላይ የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሂደዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ፣ የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች ከነዋሪው ዘንድ በተለያዩ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲነሳባቸው እንደቆየ ገልጸው፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በዘርፉ የሚስተዋለውን የህግ ጥሰት እና ወንጀል ለመከላከል መመሪያው ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ታርጋ ሳይለጥፉ አልያም ህገወጥ ታርጋ በመለጠፍ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ተሳታፊዎች መመሪያው ጠንካራ ህጋዊ ክትትል እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ከማድረግ አኳያም የላቀ ሚና አለው ብለዋ


በሃብታሙ ሙለታ

#Addisababa
#Ethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#AddisAbaba

" ከአዲስ መንጃ ፈቃድ ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይታደሳሉ " - የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን

ከአዲስ መንጃ ፈቃድና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ እንደሚታደሱ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ፤ " ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል " ብሏል።

በዚህም ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአራት ዓመት እንደሚታደሱ አስታውቋል፡፡

አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት የሙከራ በኋላ፣ ባለው አሰራር መሠረት በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ ተመላክቷል።

ነገር ግን ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) እንደሚሆን ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ገልጿል።

@tikvahethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth