ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
494 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ በተለያየ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የመኪና ስፖኪዮ በመስረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች (ልጆች) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ሚያዚያ 23 እና 24 ቀን 2016 ዓ.ም ወረዳ 2 ጋዜቦ አደባባይ እና ወረዳ 9 አካባቢ ነው የተያዙት ተብሏል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ የትራፊክ መብራቶች እና ተሽከርካሪ በሚቆምባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ ስፖኪዮ ሲሰርቁ እንደነበር አመልክቷል።

በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፈው የተገኙ ህፃናቶች መሆናቸውም ተመላክቷል።

ይህ መነሻ በማድረግ በተደረገ ምርመራ ለህፃናቱ ስምሪት የሚሰጡ የተደራጁ ወንጀለኞች መኖራቸውን ፖሊስ ማረጋገጡን ገልጿል።

አንዳንድ ህፃናት መኪና የሚጠብቁ  እንዲሁም እርዳታ የሚፈልጉ መስለው በመቅረብ ወንጀል እንደሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው   በትራፊክ  መብራቶችም ሆነ የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ ሲቆሙና በዝግታ ሲያሽከረክሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ🚨

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ?

➡️ ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦ ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

➡️ በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦ በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

➡️ በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

➡️ መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።


#Ethiopia
#የአአእሳትናአደጋስራአመራርኮሚሽን

@ትክቫሄትህኦፕአ


ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth