ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
494 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
የዘመን መለወጫን የበዓል ገቢያ ለማረጋጋት 50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይቱ ወደ ኢትዮጵያ መግባት ጀመረ

#Ethiopia | የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግስት ግዢ የተፈጸመው 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ የተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ዛሬ ጀምሯል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ እንዳስታወቀው፤ ከዚህ ቀደም መንግስት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻል እና ገበያን ለማረጋጋት ተከታታይነት ያለው እርምጃ እንደሚወስድ ቃል በገባው መሠረት 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ የተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ዛሬ ጀምሯል።

የምግብ ዘይቱ በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር እና በመኪና ተጭኖ ወደ አገራችን መግባት የጀመረ ሲሆን፣ ይህ የፍጆታ ዕቃ በዋናኝነት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግስት ግዢ የተደረገ ነው ተብሏል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ጋር በመቀናጀት በሚቀጥሉት ጊዜያት በተቀላጠፈ መልኩ 50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የሚሰራጭ እንደሚሆን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድረ ገጹ ላይ ጠቁሟል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
👍1
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66cd87871ab8285b9d2f2742

Purchase of Forested Sticker (2)
- Published by Documents Authentication and Registration service

💵 ፕሮፎርማ Tue Aug 27th, 2024 - Tue Aug 27th, 2024

ምንጭ
በማገዶ ጭስና ተቀጣጣይ ነገሮች የሚመጣ
- የሳንባ ካንሰር መስፋፋቱ ተጠቆመ

በማገዶ እንጨትና ተቀጣጣይ ነገሮች አማካይነት የሚመጣ የሳንባ ካንሰር መጨመሩን የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ ባወጣው ጥናት አመልክቷል፡፡ “የሳንባ ካንሰር የተጋላጭነት መጠን በሴቶችና በወንዶች መካከል ተመጣጣኝ ነው" ብሏል - ጥናቱ፡፡

ብዙዎቹ የሳንባ ካንሰር ታማሚዎች ወደ ሕክምና ተቋማት የሚመጡት ዘግይተው መሆኑ ያመለከተው ጥናቱ፤ የሳንባ ካንሰር አራት ደረጃዎች እንዳሉትም ይጠቁማል፡፡ በመጀመሪያው የሳንባ ካንሰር ደረጃ ላይ የሚገኝ ታማሚ ወደ ሕክምና ተቋም ከመጣ፣ የመዳን ዕድሉ ሰፊ መሆኑን የሚጠቅሰው ጥናቱ፤ በሦስተኛና አራተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ ከመጣ ግን የመፈወስ ዕድሉ ጠባብ ነው ይላል።

በአገራችን ከ90 በመቶ በላይ የሳንባ ካንሰር ታማሚዎች ወደ ሕክምና ቦታ የሚመጡት የመጨረሻዎቹ ሁለት ደረጃዎች ላይ ከደረሱ በኋላ መሆኑን የገለጸ ጥናቱ፤ በኢትዮጵያ የሳንባ ካንሰር ሕሙማን አማካይ ዕድሜ፣ ከሌሎች አገራት አማካይ የሳንባ ካንሰር ታማሚዎች አንጻር ወጣት መሆናቸው ተጠቁሟል። በዚህም 55 ወይም 56 ዓመት ዕድሜያቸው ላይ ታማሚ እንደሚሆኑ ነው ጥናቱ ያረጋገጠው፡፡

ጥናቱ በማገዶ እንጨቶች፣ በከሰል፣ በኩበት ጭስና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች የሚመጣው የሳንባ

“የሳንባ ካንሰር በሲጋራ ጭስ አማካኝነት የሚመጣ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሲጋራ የሚያጨሱ ሴቶች ቁጥር ከ1 በመቶ በታች ሆኖ ለሳንባ ካንሰር ያላቸው ተጋላጭነት ግን ከወንዶች እኩል ነው" ሲል የኢትዮጵያ ቶራሲክ ማሕበር በጥናቱ አመልክቷል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66cee7641ab8285b9d2f2d45

Purchase Requisition Transit service
- Published by Armauer Hansen Research Institute

💵 ፕሮፎርማ Thu Aug 29th, 2024 - Wed Aug 28th, 2024

ምንጭ
👍1
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66d062cf1ab8285b9d2f34c9

Lot 1 Laboratory Apparatus & Equipment

- Published by Ethiopian Environmental Protection Authority

💵 50,000 ETB Wed Sep 4th, 2024 - Tue Aug 20th, 2024

ምንጭ
በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በትራንስፖርት አቅርቦት ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተደረገ

#Ethiopia | በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሰረት በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በትራንስፖርት አቅርቦት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክሱ የሚመለከተው ከአንድ ቤተሰብ ወርሃዊ አማካይ ፍጆታ በላይ ኤሌክትሪክ እና ውሃን በብዛት የሚጠቀመው የመክፈል አቅም ያለው የህብረተሰብ ክፍል ነው ተብሏል፡፡

መንግስት አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል በመኖሪያ ቤቱ የሚጠቀመውን አማካይ ወርሃዊ የውሃና ኤሌክትሪክ ፍጆታ ከታክሱ ነፃ የሚያደርግ ሲሆን ከታክሱ ነፃ ከተደረገው በላይ የውሃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ የትራንስፖርት አገልግሎትም ተጨማሪ እሴት

ሚኒስቴሩም የትራንስፖርት አገልግሎትም ላለፉት 22 ዓመታት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆን የተደረገው አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለትራንስፖርት የሚያወጣው ወጪ እንዳይንር እንዲሁም በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚከፈለው ታክስ የዕቃዎችን ዋጋ መናር እንዳያስከትል በማሰብ ነበር ብሏል፡፡

በመሆኑም ከህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ውጪ ለሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች የዚህ አይነቱን ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ባለመሆኑ፣ መንግስት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የመሆን መብት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር ከስምንት መቀመጫ በላይ ያላቸው ተሸከርካሪዎች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Via getu temsgen

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
🤔1
ፈገግታ ሲያስቀጣ 🙄

ሰሜን ኮርያ አትሌቶቿን ልትቀጣ መሆኑ ተነገረ

በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በድብልቅ ጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ለሀገራቸው ሰሜን ኮርያ የብር ሜዳልያ ያስገኙት አትሌቶች በሀገሪቱ መንግሥት ሊቀጡ መሆኑ ተገልጿል።

የሰሜን ኮርያ መንግሥት አትሌቶቹን ለመቅጣት እየመረመረ የሚገኘው ከደቡብ ኮርያ አትሌቶች ጋር በፈገግታ ተሞልተው ፎቶ መነሳታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

በኪም ጆንግ ኡን የሚመራው የሰሜን ኮሪያ መንግሥት የሀገሪቱ አትሌቶች ወደ ፓሪስ ሲያመሩ የደቡብ ኮሪያን ጨምሮ ከየትኛውም ሀገር አትሌቶች ጋር እንዳይነጋገሩ አስጠቅቆ እንደነበር ተገልጿል።

በሀገሪቱ ከዚህ በፊት በውድድሩ ደካማ አቋም ያሳዩ አትሌቶች ትችት እና ቅጣት እንደተጣለባቸው ሲገለፅ ግዴታቸውን ባለተወጡት ላይ ደግሞ በነፃ የጉልበት ስራ እንዲሰሩ መደረጉ ተጠቁሟል።

tikvaheth sport
ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66d17c0b1ab8285b9d2f3a5e

ኮንስራክሽን 23
paint
- Published by National Intelligence and Security Service

💵 xx,xxx.xx ETB Fri Aug 30th, 2024 - Fri Aug 30th, 2024

ምንጭ
የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን የተመለከተ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ ሊውል ነው

AMN-ነሐሴ 25/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከብልሹ አሰራር እና ከደህንነት ስጋት የጸዱ እንዲሆኑ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ ሊያውል መሆኑን አስታወቀ፡፡

የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች የአሰራር፣ አደረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የዲሲፕሊን አፈጻጸም መመሪያ ማስፈጸሚያ ማኑዋል ላይ የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሂደዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ፣ የባለ ሶስት እና አራት እግር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች ከነዋሪው ዘንድ በተለያዩ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲነሳባቸው እንደቆየ ገልጸው፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በዘርፉ የሚስተዋለውን የህግ ጥሰት እና ወንጀል ለመከላከል መመሪያው ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ታርጋ ሳይለጥፉ አልያም ህገወጥ ታርጋ በመለጠፍ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ተሳታፊዎች መመሪያው ጠንካራ ህጋዊ ክትትል እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ከማድረግ አኳያም የላቀ ሚና አለው ብለዋ


በሃብታሙ ሙለታ

#Addisababa
#Ethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66d2e9aa1ab8285b9d2f416b

procurement of printer
- Published by Kotebe University of Education

💵 ፕሮፎርማ Sat Aug 31st, 2024 - Sat Aug 31st, 2024

ምንጭ
News ‼️

ብሔራዊ ባንክ የዉጪ ምንዛሪ ቢሮ ፍቃድ መስጠት የሚያስችለውን ሂደት መጨረሱን ገለፀ‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የዉጪ ምንዛሪ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ህጋዊ ሆነዉ ፍቃድ አዉጥተዉ መስራት እንዲችሉ መፍቀዱን ተከትሎ ከወዲሁ ብዙ ሰዎችና ኩባንያዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ አስታዉቋል።

የዉጪ ምንዛሪ ገበያ ዉስጥ የሚሳተፉ በፊት ባንኮች ብቻ የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ከባንኮች በተጨማሪ ሌሎች በግላቸው በዘርፉ ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ አካላት እንዲሰሩ ተደርጓል።

ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ክትትልና መጠባበቂያ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባየሁ ዱፈራ እንደተናገሩት " የዉጪ ምንዛሪ ዚሮዉን ለመክፈት ፍላጎት አሳይተዋል ያላቸዉን ሰዎች መቀበሉን " የገለፁ ሲሆን ከንግድ ሚኒስትር ጋር ያለዉ ጉዳይ ከተፈታ ወዲያው ፍቃድ መስጠት እንጀምራለን በእኛ በኩል ሁሉም ነገር አልቋል ሲሉ ተደምጠዋል ።

እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለፃ "ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖሩ የዉጪ ሀገር ዜጎችም አካዉንት ከፍተዉ ሲፈልጉ ብቻ ወደ ብር ቀይረዉ እንዲጠቀሙ ተፈቅዷል " ይህም በድፍረት የተደረገ ነዉ ማለት ይቻላል ሲሉም እርጃዉን አድንቀውታል።

ሀገር ዉስጥ ያሉ ማንኛውም የዉጪ ምንዛሪ የሚያገኙ ግለሰቦች በትንሹ በ 100 ዶላር የዉጪ ምንዛሪ አካዉንት መክፈት እንደሚችሉ የጠቆሙት አበባየሁ ዱፈራ ይህ ጥቅሙ ለግለሰቦች ሳይሆን ሀገርም ጭምር ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
AI generating image on CPU with the prompt 'a lovely cat holding a sign that says flux cpp'

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66d5a8c91ab8285b9d2f483a

ቆርቆሮ 32 ጌጀ 1ኛ ደረጃ
- Published by Ethiopian sport Academy

💵 ፕሮፎርማ Mon Sep 2nd, 2024 - Mon Sep 2nd, 2024

ምንጭ
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66d6de2b1ab8285b9d2f5196

Postcard Printing
- Published by Authority For Civil Society Organizations

💵 ፕሮፎርማ Wed Sep 4th, 2024 - Tue Sep 3rd, 2024

ምንጭ
በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የምግብ ቤት የሮቦት አስተናጋጆች በናይሮቢ ከተማ ስራ ጀመረ

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ የተከፈተው አዲስ ሬስቶራንት ከሚሰጠው አገልግሎት የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት በላይ መነጋገሪያ ሆኗል።

በመኃል ናይሮቢ ኪሌሌሽዋ በሚባለ አካባቢ ሮቦት ካፌ እውን ሆኗል። በምግብ ቤቱ ውስጥ ሶስት የሮቦት አተናጋጆች በኬንያም ሆነ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዘንድ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ጀምረዋል። ከሮቦቶቹ መካከል አንዷ ናዲያ ትባላለሽ። ከኩሽና ወደ ደንበኛው ጠረጴዛ ምግብ ታቀርባለች።

በላቁ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ራስን በሚያሽከረክር ቴክኖሎጂ የታጠቀችው ናዲያ የመመገቢያ ቦታውን በትክክል ትመራለች፣ እንቅፋቶችን በማስወገድ እና እያንዳንዱ ትዕዛዝ በትክክል እና በብቃት መድረሱን ታረጋግጣለች። የካፌው ሥራ አስኪያጅ ጆን ካሪዩኪ ምዋንጊ ለአናዶሉ እንደተናገሩት "ቴክኖሎጂን ከትልቅ አገልግሎት ጋር በማጣመር የማይረሳ ጊዜን ለደንበኞች መፍጠር እንፈልጋለን" ብለዋል።

"የእኛ ሮቦት አስተናጋጆች አሰራራችንን ለማቀላጠፍ ረድተውናል። የሰው ሰራተኞቻችን በሚሰሩት ጉዳይ ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ነፃ በማድረግ የአቅርቦት ስርዓቱን የበለጠ ቀልጣፋ ሆኗል ብለዋል።ኤሚሊ ንጆሮጌ የምትባል ደንበኛ ምግብ እና መጠጦችን ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ሮቦቶች እየጠቆመች “ይህ ለማየት በጣም አስደናቂ ነው” ብላለች ። "ሮቦቶች ከአካባቢያቸው ጋር ምን ያህል እንከን የለሽ መስተጋብር እንደሚፈጥሩ ማየት በጣም አስደናቂ ነው። ፊልም ይመስላል ስትል አክላለች።



ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66d83db81ab8285b9d2f58c6

purchase of car key
spare parts
- Published by Alert Specialized Hospital

💵 ፕሮፎርማ Wed Sep 4th, 2024 - Wed Sep 4th, 2024

ምንጭ
በአዲስ አበባ የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ደንብ በዚህ ሳምንት ወደ ስራ ይገባል

🔗 የተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራው ብቁ ስለመሆኑ የብቃት ማረጋገጫ ያስፈልጋል፣

በአዲስ አበባ ከተማ የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ደንብ መጽደቁን ተከትሎ በዚህ ሳምንት ወደ ስራ እንደሚገባ የመዲናዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በሰጠው መግለጫ÷ ደንቡ በከተማዋ ውስጥ የባከነ የህንጻ ስር የተሸከርካሪ ማቆሚያ ቦታዎችን ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ በማድረግ የተሸከርካሪ ማቆሚያ አቅርቦትን የሚያሳድግ መሆኑን ገልጿል።

ደንቡ የመንገድ ዳር የተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራዎችና የህንፃ ላይ፣ የህንፃ ስር፣ የመሬትስር፣ የመሬት ላይ እና ሌሎች ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ሥፍራዎች ላይ እንደሚተገበር ተጠቁሟል።

ማንኛውም የግል ተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የሚሰጥ አካል አገልግሎት መስጠት የሚችለው የተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራው ብቁ ስለመሆኑ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት ሲችል ብቻ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ማንኛውም ማህበር ወይም ድርጅት ከባለስልጣኑ ጋር የአገልግሎት ውል ሳይፈጽም ወይም የፈጸመው ውል ሳይታደስ፣ ማህበራት ወይም የግል የተሽከርካሪ ማቆሚያ ድርጅት ያለ ደረሰኝ ወይም በህግ እውቅና ያልተሰጠው ደረሰኝ መጠቀም

የተከለከሉ ድጊቶችን የፈጸመ የተሸከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት ሰጪ አካል እንደጥፋቱ መጠን በወንጀል መጠየቁ እንደተጠበቀ ሆኖ በባለስልጣኑ በኩል ከ3 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ድረስ እንደሚቀጣ ተመላክቷል፡፡

(መሳፍንት እያዩ -FBC)

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
ምህረት የለሿ ሰሜን ኮሪያ‼️

ሰሜን ኮሪያ ህዝብን ለጎርፍ አደጋ አጋልጠዋል ያለቻቸውን 30 ካድሬዎች በሞት ቀጣች‼️

ሰሜን ኮሪያ ህዝብን ለጎርፍ አደጋ አጋልጠዋል ያለቻቸውን ካድሬዎች በሞት ቀጣች፡፡

ጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ጨምሮ ከሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ጋር መልካ ግንኙነት የሌላት ሰሜን ኮሪያ ሀላፊነታቸውን አልተወጡም ባለቻቸው ካድሬዎች ላይ እርምጃ ወስዳለች፡፡

ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ ከቻይና ጋር አዋሳኝ በሆነችው ቻጋንግ ክልል ላይ ከባድ የጎርፍ አደጋ የደረሰ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል፡፡

እንዲሁም ሲኒጁ የተሰኘችው ሌላኛዋ ክልልም ተመሳሳይ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ አጋጥሞ ነበር፡፡

የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከሆነ ህዝብ በጎርፍ አደጋዎች እንዲጎዳ አስቀድመው የመከላከል ስራዎችን አልሰሩም በተባሉ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ዘግቧል፡፡

መቀመጫውን ደቡብ ኮሪያ ያደረገው ሳውዝ ቲቪ በበኩሉ የዜጎች መኖሪያ ቤቶች፣ የሕዝብ መገልገያ መሰረተ ልማቶች እና ሌሎች ተቋማት እንዲወድም ምክንያት ሆነዋል የተባሉ ካድሬዎች ተገድለዋል ብሏል፡፡

ዘገባው አክሎም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን በጎርፍ የተጥለቀለቁ አካባቢዎችን ከጎበኙ በኋላ ከ20 -30 የሚደርሱ ካድሬዎች እንዲገደሉ ውሳኔ አሳልፈዋል ተብሏል፡፡

Driving in Ethiopia
ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
👍1
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66d9731a1ab8285b9d2f5e4d

ልዩ ልዩ የደንብ ልብሶች ግዥ
ለ/መቤቱ ልዩ ልዩ የደንብ ልብስ ለሚመለከታቸው ሰራተኞች
- Published by Ministry of Revenue

💵 35,000 ETB Mon Sep 23rd, 2024 - Thu Aug 29th, 2024

ምንጭ