የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
የዋሓት ምንድን ነው ?

የዋሓት ከብልጣብልጥነትና ከአታላይነት ሕይወት ነጻ መሆን ማለት ነው ። ከገራገርነትና ከአለመከለል ጋር የማይያያዝ ነው ። መድኃኒታችን ለዘሪው ምሳሌ ገራገርነትን ፤ አለመከለል ፤ የዋኀትነትን በተለያየ ምሳሌ አቅርቦታል ።

የሕይወት ልምድ አለመኖር ከጭንጫ መሬት ጋር ተነጻጽሮ ቀርቧል ። ጭንጫ ምድር ለአትክልት ማብቀያ ሥፍራ ሆኖ አያገለግልም ። ዘር ሲወድቅበት ምንም ውጤት ሳይኖረው ወፎች የሚለቅሙት ይሆናል ። የሕይወት ልምድ የሌለው ዝንጉ ሰው ከሰዎች ተሞክሮ የሚማርበት ድርጊቶች ወደ እርሱ ይመጣሉ ።
እርሱ ግን ለመማር ፈቃደኛ አይደለም ። ነገሮችን አጥርቶ መመልከትም አይቻለውም ። የሕይወት ልምድ የሌለው ሰው ነገሮችን አይለይም ። እውነተኛ ፍርድንም አይጠነቀቅም ። ስለዚህ ራሱን ችግር ውስጥ ያገኛል ። የልምድ ማነስ የእውቀት ማነስና ባዶ ኩራት ያጅበዋል ።

#ግልብነት በድጋያማ ቦታን ይመስላል ጥልቀት የለውም ። በዚህ ድጋያማ ሥፍራ የሚወድቅ ዘር ዕጣ ፈንታው ምን ይሆናል ? ይበቅላል ነገር ግን ወደ ታች ሥፍራ ይዞ ይበቅል ዘንድ አይቻለውም ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ይሞታል ። ግልብነት #ነገሮችን_ከላይ_ከላይ_የሚመለከት_ሰው_ምሳሌ_ነው ። የነገሮችን ጥልቀት ትርጉም አይመረምርም አይረዳም ።

#የዋሓት የጥሩ መሬት ምሳሌ ነው ። ሠላሳ ፤ ስድሣ ፤ መቶ ያማረ ፍሬ የሚያፈራ ምድር ምሳሌ ነው ። የዋሓት ሌሎችን ባሕርያት ያሻሽላል ። ሰው የልምድ ማጠር ቢኖርበት ወይም አስቀድመን የጠቀስናቸው የሥጋ ባሕሪያት ቢሰለጥኑበት የዋኅ ከሆነ ይማራል ። ምክንያቱም #የዋኃት_የጥበብ_እጮኛ_ናት ። የዋኅ ሰው ወደ ጥበብ ይቀርባል ። #የዋኃት_የትሕትና_ልጅ_ነው ። ትእቢትና ትዝህርት የሰውን ልብ የሚከለክሉ ናቸው ። ትኅትናና የዋሓት የቅድስና መሣሪያዎች ናቸው ። የዋኀትን ገንዘብ ያደረገ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መፈጸም የሚያስገኝውን ሽልማት እያሰበ ከውለታ ነጻ ነው ። ግልብነት ድርጊትንም ውጤትንም አይመለከትም ። የሕይወት ልምድ ማነስ አንድ ሰው የሚሰራውን ሥራ ውጤት ከግምት ውስጥ የሚያስገባ አይደለም ።

#አቡነ_ሽኖዳ_ሳልሳዊ
እንኳን ለእመቤታችን ፅንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!🙏🙏
ድክመቶቼን ማወቄ ምንድነው የሚጠቅመኝ? ካልን አንድ ሰው ድክመቶቹን ካወቀ እግዚአብሔርን ያውቃል።''ስደክም ያንጊዜ ኃይለኛ ነኝና'' 2ቆሮ 12፡10። ኃጢአቴ ምን ያህል አስነዋሪ እንደሆነ ሳረጋግጥ የእግዚአብሔርን ፀጋ እሻለሁ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ብሏል ''ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ እና ከእኔ ተለይ'' ሉቃ 5፡8። ቅዱስ ጴጥሮስ ምን አይነት ችግር ውስጥ እንዳለ ተሰምቶታል። ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አለው ''አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ'' ሉቃ 5፡10 ቅዱስ ጴጥሮስ ለታላቅ ተልእኮ እና አገልግሎት የበቃው መቼ ነበር? ይህ የሆነው ራሱን ባወቀ ቅጽበትና "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ" ብሎ በተናገረ ጊዜ ነበር። የሰው ልጅ በእንዲህ ዓይነት ስሜት ውስጥ በሆነ ጊዜ እግዜአብሔር እንዲህ ይላል። "አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ"። ስለዚህ ራሳችንን ማወቅ ማለት እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ነው።

የሕይወት መዓዛ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ'

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
እሳት የእግዚአብሔር #የወርቅ_ማዕጠንት የእመቤታችን ወርቅ የንጽሕናዋ ማዕጠንቱ እሳቱን እንደተሸከመ እመቤታችንም ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኗ የመሸከሞ ምሳሌ
JOIN OUR CHANNEL
@ethiopianorthodoxbooks
የምስራች

የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በናይልሳት (Nilesat) የ24 ሰዓት የሙከራ ስርጭት ጀመሯል።

Frequency: 11555
Polarization: V
Symbol Rate: 27500
FEC: 7/8

"ዝክረ ቅዱሳን" የቴሌቪዥን ጣቢያ የ24 ሰዓት የሙከራ ስርጭቱን ጀምሯል።

Frequency: 10727
Polarization: H
Symbol Rate: 27500
ቅዱስ ሩፋኤል
ከከበሩት ከ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ ::
ጦቢት 12 : 13
እንግዲህ ከባህሪው ቅድስና ፍጥረቱን በጸጋ ቅድስና መርጦ የሚለይ እግዚአብሔር አክብሮ እንዲህ ያለ ሰማያዊ ፀጋ ከሰጣቸው ቅዱሳን መላእክት መካከል በስልጣኑ
ሊቀመናብርት (የመናብርት አለቃ) የሆነ በሹመት
ፈታሔ ማኅጸን (ማሕጸን የሚፈታ)
ከሳቴ እውራን (የእውራንን ዓይን የሚያበራ) ሰዳዴ አጋንንት (አጋንንትን የሚያባርር)
ፈዋሴ ዱያን (ድውያንን የሚፈውስ)፣
አቃቤ ኆኅት (የምህረትን ደጁ የሚጠብቅ) ተብሎ የተገለጠ ከሊቃነ መላእክቱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ተከትሎ የሚነሳ መልአክ ራሱን እንዲህ በማለት ገለጠ « የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነት ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ» (ጦቢ.12÷15)
ይህ የከበረ ታላቅ መልአክ ሰሙ የእብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት ውጤት ነው፡፡
" ሩፋ " ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን "ኤል "ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጠል ስመ አምላክ ነው ይህም « መልአኬን በፊትህ እሰዳለሁ….. ስሜ በእርሱ ስለሆነ . አታስመርሩት» (ዘጸ.23÷20-22) እዳለው ነው፡፡
~~~~ታዲያ ሩፋኤል የሚለው በጥምረት ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ የሚለውን ይተካል «በሰው ቁስል የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሩፋኤል ነው፡» (ሄኖ.6÷3)
ይህ መልአክ እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን ይጠብቃቸዋል(ዳን.4÷13 ዘጸ. 23÷20 መዝ. 90÷11-13 )
ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡(ዘካ.1÷12)
በፈሪሀ እግዚአቤሔር እና በአክብሮተ መላእክት ያሉትን ድናቸዋል (ዘፍ.49÷15 መዝ.3÷37)
« እግዚአብሔር ሃይሉን የሚገልጥበትን ቅጣቱን ሊያሳይ ቢወድ አስቀድሞ መርጦ በወደዳቸው ለይቅርታ የተዘጋጁ የይቅርታ መላእክትን ያመጣል» (ሮሜ.9÷22)
ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀመናብርትን ድንቅ ገቢር ተአምራቱን ያዩ ምዕመናን
……የወላድ ማኅፀን እንዲፈታ
ስለተሸመ ከጌታ
አዋላጅ ብትኖር ባትኖርም
ሐኪም ሩፋኤል አይታጣም
በምጥ ጊዜ ሲጨነቁ የባላገር ሴቶች ሁሉ
የመልአኩን መልክ አንግተው ማርያም ማርያም ይላሉ
ማየጸሎቱን ጠጥተው ቶሎ ፈጥነው ይወልዳሉ ……
እያሉ ደጅ ጠንተው ይማጸኑታል፡፡
ዜና ግብሩን ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከተናገረለት በመነሳት በቅዱሳን ላይ ድንቅ የሆነ እግዚአብሔር በመልአኩ አድሮ ያደረጋቸውን ተግባራት አበው የበረከት ምንጭ በሆነ ድርሳኑ ላይ አኑረው የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ሰጥተውናል፡፡ በጉልህ ሠፍረው ከምናገኛቸው ብዙ ድንቅ ሥራዎች መሀል ጥቂቶቹን እነሆ
~~~> በሥነ-ስዕሉ የተማጸኑ፣ በምልጃው ታምነው የጸኑ ቴዎዶስዮስንና ዲዮናስዮስን በገሃድ ተገልጾ ለንግስናና ለጵጵስና ክብር አብቅቷቸዋል፡፡
~~~> የንጉስ ቴዎዶስዮስ ልጅም ጻድቁ አኖሬዋስም በፈጣሪው ህግ እየተመራ የሊቀ መናብርቱን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ አሳንጾ ሲያስመርቅ ለበለጠ ክብር ልቡን አነቃቅቶ ለታናሽ ወንድሙ ለአርቃዴዋስ የነጋሢነት ስልጣኑን ትቶ መንኖ በስውርና በጽሙና እዲኖር ረድቶታል፡፡
~~~> በሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን አባቶች ለሊቀመናብርቱ ክብር በአሣ አንበሪ ጀርባ ላይ ያሳነጹትን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ በወደቡ አጠገብ በእስክንድሪያ ሳለች ጠላት ዲያቢሎስ አነዋውጾ ለምስጋና የታደሙትን ምዕመናን ሊያጠፉ አሣ አንበሪውን ቢያውከው ወደ ሊቀመናብርቱ ተማጽነው እርዳን ቢሉ ፈጥኖ ደርሶ በበትረ መስቀሉ (ዘንጉ) ገሥጾ ከጥፋት ታድጓቸዋል፡፡
በቅዱስ መጽሐፍም እንደተገለጠው
~~~> ሣራ ወለተ ራጉኤልን አስማንድዮስ ከተባለው የጭን ጋንኤን ሲታደጋት የጦቢያን አባት የጦቢትን ዓይን አበራለት (መጽሐፍ ጦቢት)
ከዚህም አልፎ የይስሐቅን እናት ሣራን፣ የሶምሶንን እናት (እንትኩይን) ምክነታቸውን የቆረጠ ወልዶ ለመሳም ያበቃቸው ይኸው ፈታሔማኅጸን የልዑል እግዚአብሔር መልአክተኛ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ከመልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት ያሳድርብን አሜን !!!
✥እንኳን ለጽጌ ጾም የሁለተኛ ሰምንት በሰላም አደረሳችሁ✥

2012 የሁለተኛ ሰምንት ሰንበት የጽጌ ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋር አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

❖ሰላም ለአፉክሙ / ነግሥ /

ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕጾሁ ሰላም፤
ጽጌያቲሁ ሥላሴሁ ለተዋህዶ ገዳም፤
መንገለ አሐዱ አምላክ ነዋየ መጻኢት ዓለም፤
ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤
እምአምልኮ ጣዖት ግልፍ አሐዱ ድህርም፡፡

❖ዚቅ፦ ለሥሉስ ቅዱስ ጥዑም ቃሎሙ ፨ናርዶስ ጸገየ(ፈረየ) ውስተ አፉሆሙ ፡፡
✥በከመ ይቤ መጽሐፍ /ማኅሌተ ጽጌ/

❖በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤
ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ (ጽላተ) ኪዳን፤
ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤
ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡

✥ወረብ፦

በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ዘኮንኪ ለዕረፍት ትእምርተ ኪዳን፤
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን።

✥ዚቅ፦ ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፨ ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፨ ኅቡረ ንትፈሣሕ ዮም፨ በዛቲ ዕለት፡፡

✥. እንዘ ተሐቅፊዮ /ማኅሌተ ጽጌ/

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ፡

✥ወረብ፦

ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል፤
ወንዒ ሠናይትየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ።

✥ዚቅ
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት ንባብኪ አዳም ፤
ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ ፤
እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት ፤
አልቦ ዘይመስል ዘከማኪ ክብረ ፤
እግዚኣ ለሰንበት በማኅፀንኪ ተፀውረ።

✥ ክበበ ጌራ ወርቀ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

✥ወረብ፦

ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምንቆ ባሕርይ፤
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ።

✥ዚቅ፦

ይእቲ ተዓቢ እምአንስት ፨ እሞሙ ለሰማዕት ፨ ወእኅቶሙ ለመላእክት ፨ መድኃኒቶሙ ለነገሥት ፨ አክሊል ንጹሕ ለካህናት ፨ ብርሃኖሙ ለከዋክብት።

✥አንብርኒ ማርያም / ማኅሌተ ጽጌ /

አንብርኒ ማርያም ውስተ ልብኪ ከመ ሕልቀት፤ ወከመ ማዕተብ ፁርኒ በመዝራዕትኪ ልዕልት፤
በእንተ ርስሐትየሰ ኢትመንንኒ ንግሥት፤
እስመ ወሀብኩ ንብረትየ ለፍቅርኪ ሞት፤ ዘአሰገርዎሙ ለሰማዕት በጽጌሁ ሕይወት፡፡

✥ወረብ፦

አንብርኒ ማርያም ውስተ ልብኪ ከመ ኅልቀት ወከመ ማዕተብ ዘትእምርት በመዝራዕትኪ ልዕልት፤
በእንተ ርስሐትየሰ ኢትመንንኒ ኢትመንንኒ በእንተ ርስሐትየ።

✥ዚቅ
አ ሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት
አሠ ወንጌለ መንግስት አውፈዮሙ
አ ሰንበተ ክርስቲያን ለዕረፍት ሠርዓ ሎሙ
አ ከመ ወርቅ በእሳት ፈተኖሙ
አ ወከመ ጽንሐሐ መሥዋዕት ተወክፎሙ
አ ሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት

ኢየሱስ ስዱድ/ሰቆቃወ ድንግል/

ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን ❖ኢየሱስ ግፉዕ ምስካየ ግፋዓን ❖እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን ❖ኢየሱስ ነግድ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕፃን ❖ወልደ አብ ፍቁር በኀበ ሰብእ ምኑን❖መኃልይ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን

✥ወረብ

ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን
መኃልይ ብካይ ኮነኒ ኮነኒ ዘእሙ ኅዘን

ዚቅ
አንተ ውእቱ ምርጉዞሙ ለጻድቃን❖ተስፋሆሙ ለስዱዳን ❖መርሶሙ ለእለ ይትሀወኩ❖ብርሃነ ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው ፧

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

@mezgebehaymanot ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ

በቴሌ ግራም
😘 " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም
@mezgebehaymanot ሰርች search በማድርግ ይቀላቀሉ😍

በ Facebook " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

መሰከረም 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ(ጣፎ)የተፃፈ ደጋሚ ተለቀቀ

ወስብሐት ወለመስቀሉ
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
እንኳን ለጾመ ጽጌ ሦስተኛው ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ

2012 ሦስተኛው ሰምንት ሰንበት የጽጌ ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋር አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

❖. ነግሥ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ ✥ሃሌ በ፱ ሐረገ ወይን፨ ሃሌ ሉያ(፱ ጊዜ) ሐረገ ወይን
እንተ በምድር ሥረዊሃ፨ ወበሰማይ አዕፁቂሃ፨
ሐረገ ወይን ፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ፨
ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት፨
ሐረገ ወይን ፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፨
ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፨ ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ።

ማኅሌተ ጽጌ
ቀስተ ደመና ማርያም ትምህርተ ኪዳኑ ለኖኅ ❖ዘእግዚአብሔር ሤመኪ ለተዝካረ ምሕረት ወፍትሕ ❖ህየንተ ቀሰፋ ለምድር ወአማሰና ❖ በአይኅ❖በእንቲአኪ አሠርገዋ በጽጌ ኩሉ አቅማኅ ❖ከመ በከዋክብት አሠርገዎ ለሰማይ ስፋሕ❖

❖ወረብ

ቀስተ ደመና ማርያም ትምህርተ ኪዳኑ ለኖኅ ትምህርተ ኪዳኑ ለኖኅ
በእንቲአኪ አሠርገዋ አሠርገዋ ለምድር በጽጌ አቅማኅ❖

❖ዚቅ
ንጉሥኪ ጽዮን❖አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት ወለሰማይኒ በከዋክብት ❖ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን ❖

✥. እንዘ ተሐቅፊዮ /ማኅሌተ ጽጌ/

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ፡

✥ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።(ልሳኑ በሚለው )


ዚቅ
✥በሰላም ንዒ ማርያም ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ ❖በሰላም ንዒ ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል ❖በሰላም ንዒ ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል ❖በሰላም ንዒ ምስለ ኩሎሙ ቅዱሳን በሰላም ንዒ ምስለ ወልድኪ አማኑኤል በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም ❖


✥ ክበበ ጌራ ወርቀ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

✥ወረብ፦

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየኃቱ እምንቆ ባሕርይ፤
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ።(መላከ ሰላም በሚለው)

✥ዚቅ፦

በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርኬዴን ❖ ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት ❖ወንገሥት ይተቀነዩ ለኪጨ❖ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለንገሥት ❖

✥ / ማኅሌተ ጽጌ /

ይትባረክ ጽጌኪ ማርያም ለልብየ ፍቅረኪ ዘከፈሎ ❖ወኢያርኃቀ እምኔየ ለኪዳንኪ ሣህሎ ትምህርተ ኪዳንኪ ይሁብ ለዘማውያን ተደንግሎ ❖ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ❖ ፈለገ እሳት ወደይን እምስጠመ ኩሎ❖

✥ወረብ፦
ይትባረክ ጽጌኪ ማርያም ፍቅረኪ ዘከፈሎለ ልብየ ❖
ወኢያርኃቀ እምኔየ ሣህሎ ለኪዳንኪ❖


✥ዚቅ
አስተብጽዕዎ ወይቤልዋ እለ ይነብሩ ፈለገ እሳት ❖ሰአሊ ለነ ማርያም ቅድስቱ ለእግዚአብሔር ❖

❖ / ሰቆቃወ ድንግል/ብክዩ ኅዙናን

ብክዩ ኅዙናን ሐልየክሙ ስደታ፣
ወላህዉ ፍሡሓን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፣
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤
ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤
ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኲሉ ፍኖታ፡፡

ወረብ፦

ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም፤
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል።

ዚቅ፡-

አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓልኪ በሐቂፍ ፨ አድባራተ ዔልኪ ከመ ዖፍ ፨ እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጸፍ ፨ እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ።

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

@mezgebehaymanot ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ

በቴሌ ግራም
😘 " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም
@mezgebehaymanot ሰርች search በማድርግ ይቀላቀሉ😍

በ Facebook " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

መሰከረም 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ(ጣፎ)የተፃፈ ደጋሚ ተለቀቀ

ወስብሐት ወለመስቀሉ
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
#ከማኅበረ_ሥላሴ_አንድነት_ገዳም_የተላከ_መልዕክት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ ለ 15 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ።


#በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ለምትገኙ_ኦርቶዶክስ
_ክርስቲያኖች_በሙሉ_ከጥቅምት_24_እስከ_30_ከ
ህፃናት_እስከ_ሽማግሌ_ማንም_ሳይቀር_በማህበረ_መ
ነኮሳቱ_አማካኝነት_ፆም_ታውጇል::
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱአምላክ አሜን
በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኛችሁና በደሙ የዋጃችሁ በኢትዮጵያ
የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ በቤታችሁም ያላችሁ
በህመም ምክንያት በሆስፒታል ያላችሁ በማረሚያ ቤት ያላችሁ
በጦር ሜዳም ያለችሁ እንዲሁም በተለያየ ስፍራ የምትገኙ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሰላምታችንን
በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡
እኛ ማኅበረ ስላሴ እንድነት ገዳም የምንገኝ ማኅበረ መነኩሳት
በሀገራችን ሰላም መታጣት ምክንያት ከሀዘናችን ጋር አምላክ
አበው ክብር ምስጋና ይግባዉ ደኅና ነን፡፡
እግዚአብሔር ገና ሃያ ሁለቱን ስነ-ፍጥረት ፈጥሮ ሳያበቃ
ሳጥናኤል በዓለተ ረቡዕ በሶስተኛዉ ሰማይ በጌታ ላይ በማመጽ
በጀመረዉ ጸብ ምክንያት ከመላዕክቱ ጋር ተዋግቶ ተሸንፎ ወደ
ምድር ተጥሎ እነሆ ያለ እረፍት ለሰባ ሺ አምስት መቶ አመታት
በመላዉ ዓለም ደም ሲያፈስ ቆይቷል፡፡ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ፡፡
ጌታ የተሰጠዉ የቀጠሮ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ታግሶታል፡፡
አሁን ግን ከወትሮዉ ለየት ያለዉ ነገር የእግዚአብሔር ቤተ -
መቅደስ በሆነችዉና የቅዱሳን የአስራት ሀገር በተሰኘችው
በኢትዮጵያ ሀገራችን የሳጥናኤል ጭፍሮች ክተት ሰራዊት ምታ
ነጋሪት ብለዉ ዘምተዉ በታሪክም ያልሰማነዉ በዘመናችንማ
አይተን የማናቀዉ የአርስ በአርስ እልቂት እንኳን ከክርስቲያን
ከሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ ድርጊት ተፈጽሟል እየተፈጸመም
ነዉ፡፡
ሰይጣን ብቻዉን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ከሰዉ ጋር ሆኖ
በሰዉ ልብ አድሮ ግን ምንም የሚቀረዉ የሀጢያት ሥራ የለም፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፡፲፭ ላይ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ
ያለዉ የጌታ ቃል ተጥሷል፡፡
ቀድሞ አንድ ሰዉ ለሥራም ሆነ ለንግድ ወይም ለተለያየ
ጉዳይ ወደ ማያዉቀዉ ወደ ሚያዉቀዉም በኢትዮጵያ ክፍላተ
ሀገር ወይም ክልል ሲዘዋወር ለሀገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ነኝ
ብሎ አይጨነቅም፡፡ የእግዚአብሔር እንግዳ ተብሎ ከመሸበት
ገብቶ እግሩን ታጥቦ ቤት ያፈራውን በልቶ ጠጥቶ ከመልካም
ምንጣፍ ተኝቶ አድሮ ሲነጋ ተነስቶ መርቆ ቀሪዉን ምንገድ
ይጓዛል፡፡
ዛሬ ግን ያ ቀረና የእግዚአብሔር እንግዳ እራቱ ጥይትና ገጀራ
መጠጡ ደም ሆኗል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ ፳፭፥፵፪ ላይ
የተጠቀሰዉ እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበላችሁኝም ብራብ
አላበላችሁኝም የሚለዉ የጌታ ቃል ትዉልዱን እየተዋቀሰዉ ነዉ፡፡
በእርግጥም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ ብሎ ዮሐንስ
ወንጌላዊ እንደተናገረዉ እንግዶች የሰላም ተጓዦች መሆን
ይጠበቅባቸዋል፡፡ነገር ግን የሰላም ሰዎችም አብረዉ
ተጨፍልቀዉ የጥፋት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነ
እግዚአብሔር አሁንም ታግሶናል፡፡እኛ አሁን ከሞት የተረፍነዉ
ከጥላ ያረፍነዉ በጽድቃችን አይደለም በቸርነቱ ለንስሐ ጊዜ
ተሰጥቶን ነዉ እንጅ፡፡
ነቢያት ስለ ጥፋት ሲተነብዩ በሰዉ ልጅ ሐጥያት ከእግዚአብሔር
የሚታዘዘዉን መቅሰፍት ማስገንዘባቸዉን እንጅ ጥፋት ዝም ብሎ
ደርሶ የሚታዘዝ አይደለም፡፡
አሁን በኃጢያታችን ምክንያት እየተጎነጨነዉ ያለዉ መከራ ከዚህ
በፊት ብዙ የተነገረ ቢሆንም በትንቢተ ዮናስ ታሪካቸዉ
እንደተጠቀሰዉ እንደ ሰብዓዊ ነነዌ ወደ እግዚአብሔር በጾም
በጸሎት ሆኖ በመለመን በማልቀስ መከራዉን ማስቀረት
እንዲቻል ቅዱሳን በመጽሐፍት አስተምረዉናል፡፡
በኖህ ዘመን ምድር በዉሃ ሙላት የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት
ነዉ፡፡ በሎጥ ዘመን በሰዶም ሀገር የተቃጠለችዉና ከምድረ ገጽ
የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት ነዉ፡፡
ዛሬስ እየተሰራ ያለዉ ኃጢያት በዚያ ዘመን ከነበረዉ ያንሳልን ?
ያን ጊዜስ በንስሀ ላልተመለሱ ሰዎች ፈርዶ ያጠፋቸዉ አምላክ
ዛሬስ ፈርዶ ማጥፋቱ ይሳነዋል ወይ ? አይሳነዉም
እንዲያዉም እንደ ዘመናችን ኃጢያት ብዛትና ክብደት
ላልፈረደብን እግዚብሔር እያመሰገንን ይህን መልዕክት
በያላችሁበት ሲነበብላችሁ ከሰማችሁት በኋላ ወደ ልባችሁ
ተመለሱ ከእንግዲህ ወዲህ በዘር ፣ በጎሳ ፣ በቋንቋ ፣ በሀገር ፣
በብሔር መለያየት ይብቃ ፣ መገዳደል ይብቃ ፣ መዘራረፍ ይብቃ
፣መሰደድም ይብቃ አጠቃላይ የጥፋት ዘመቻ ይብቃ፡፡ ወደ
ቀድሞ ኢትዮጵያዊ አንድነታቸን እንመለስ በኅብረት ተቻችለን
እንኑር፡፡
የኃጢያታችንን ካባ አዉልቀን በነብስም በሥጋም የሚያድነንን
የንስሐ ካባ እንልበስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፥፲፪ ላይ እኔ
እንደወደድኳችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ብሎ ጌታችን ባዘዘብ
መሰረት ጥላቻን አስወግደን የዘር ፣የጎሳ፣ የቋንቋ ፣ የክልል
ልዩነት ሳይኖረን እርረ በእርሳችን እንዋደድ፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፬፥፳፯ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ያለዉ ጌታ
ቃሉ አይለወጥም እና ይህ ከሆነ ብቻ እዉነተኛዉን ሰላም
ማግኘት ይቻላል፡፡
የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ነብዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ምዕ
፩፥፲፱ ላይ ‹‹ እሺ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት
ትበላላችሁ እምቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኃለች
የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና›› የሚለዉን የትንቢት ቃል
ዛሬም በእኛ ኢትዮጵዊያን ላይ እንዳይደርስብን ለእግዚአብሔር
ቃል እንታዘዝ እና ክፋትን ሁሉ ትተን ንስሀ ገብተን የምድርና
በረከት እንብላ፡፡ አለበዚያ ግን ምሕረት በእጁ የሆነ አምላክ
መዓተም በእጁ ነዉና ምርጫዉ ግን የእናንተ ነዉ፡፡ በሀገራችን
ሰላም ይሰፍን ዘንድ ማንኛዉም ክርስቲያን የተጣላ ታርቆ ፣
የበደለ ክሶ ፣ ይቅር ተባብሎ ፤ ከጥቅምት ፳፬ እስከ ጥቅምት ፴
ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም ድረስ ልጅ አዋቂ ሳይለይ እስከ ዘጠኝ ሰዓት
እየጾማችሁ በሀዘን በለቅሶ ምህላ በመያዝ ከእግዚአብሔር
ምህረትና ይቅርታ በጋራ እንድንለምን እኛ የማኅበረ ሥላሴ
አንድነት ገዳም ማኅበረ መነኮሳት ሁሉን በፈጠሩ በቅድስት
ሥላሴ ስም አምላክን በወለደች በእናታችን በቅድስት ድንግል
ማርያም ስም በታላቅ አክብሮት መልዕክታችንን ለመላዉ ሕዝበ
ክርስቲያን አስተላልፈናል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም ይስጥልኝ
የሞቱትን ሁሉ ነብስ ይማርልን
የጠፋዉን የተቃጠለዉን የወደመዉን ንብረት ሆሉ ይተካላችሁ
አሜን ይሁን ይደረግልን
መምህር አባ ወልደ ሰንበት ነጋሽ
የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም አበመኔት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Share share share share share share

1 ሰው ለ 15 ምዕመን
እንኳን ለጾመ ጽጌ አራተኛው ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ

2012 አራተኛው ሰምንት ሰንበት የጽጌ ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋር አብረን ለማመስገን ይረዳን #ምልቱን #አካቶ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

✥ነግሥ / ሰላም ለአብ /

ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም፤
ለወልድ ሰላም ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤
ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም
ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም ፤
ለሰማእታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም፡፡

✥ዚቅ፦

ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት፡፡

✥ትመስል እምኪ / ማኅሌተ ጽጌ /

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤
ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤
ወካዕበ ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤
እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤
ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ፡፡

✥ወረብ፦

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እምኪ፤
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም።

ዚቅ፦

እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ፨ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ፨ ከመ ትኲኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ፨ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለም፡፡

✥እንዘ ተሐቅፊዮ /ማኅሌተ ጽጌ/

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ፡፡

✥ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ (መላከ ሰላም በሚለው )

✥ዚቅ፦

ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ፨ ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን ፨ አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና ፨ እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት ፨ ወእኅቶሙ ለመላእክት ፨
አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና።

✥ክበበ ጌራ ወርቅ / ማኅሌተ ጽጌ /

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቆ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ
ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

✥ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቊ ባሕርይ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግስቱ።(ርዕሰ አውደ አመት በሚለው )

✥ዚቅ፦

ሰአሊ ለነ ማርያም ፨ አክሊለ ንጹሐን ብርሃነ ቅዱሳን።

✥ዘንተ /ዘኒ/ ስብሐተ / ማኅሌተ ጽጌ /

ዘንተ (ዘኒ) ስብሐተ ወዘንተ ማሕሌተ፤
ተአምርኪ ጸገየ ወፈረየ ሊተ፤
ከመ እሰብሕ ዳግመ እንዘ እጸውር ጸበር፤
ምስለ እለ ሐጸቡ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ ድርገተ፤
ውስተ ባሕረ ማህው ድንግል ክፍልኒ ቁመተ።

✥ወረብ፦

ምስለ እለ ሐፀቡ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ፤
ክፍልኒ ቊመተ ድንግል ድንግል ውስተ ባሕረ ማኅው።

✥ዚቅ

ገጹ ብሩህ ከመ ፀሐይ ❖ወእምኲሉ ስነ ሠርጉ ሰማይ ❖(ለጊዮርጊስ ላይ)ለእስጢፋኖስ ኅሩይ ዘተወልደ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ❖አልባሲሁ በደመ በግዕ ዘሐፀበ ❖ወእምሠረቅት መርዔቶ ዓቀበ

✥እስከ ማዕዜኑ / ሰቆቃወ ድንግል /

እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ፤
ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤
ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ
እምግብፅ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

✥ወረብ፦.

በከመ ይቤ ዖዝያን ዖዝያን ለክብረ ቅዱሳን ፤
እምግብፅ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡሁ።

✥ዚቅ፦

ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ፨ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ።
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

@mezgebehaymanot ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ

በቴሌ ግራም
😘 " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም
@mezgebehaymanot ሰርች search በማድርግ ይቀላቀሉ😍

በ Facebook " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

መሰከረም 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ(ጣፎ)የተፃፈ ደጋሚ ተለቀቀ

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

መሰከረም 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ(ጣፎ)የተፃፈ ደ
በስመኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሃዱ ኣምላክ ኣሜን። ከ ገዳሞች ኣባቶች የተላከ ጥብቅ ማሳሰብያ ጀሮ ያለዉ ይስማ። 2012 የ መከራ ዘመን ነው። መከራዉ ምን ብትሉኝ ረሃብ ቸነፈር ራስ በራስ መጨራረስ ነው እና። በተቻለን ኣቅም ከ ጥቅምት24 - ጥቅምት30 ጾም ስለ ታወጀ ሁላችን እንጹም ጾሙ እስከ 9:00 ሰዓት ነው። እምንጾመዉ ስለራሳችን እና ስለ ሃገራችን ነው ስለ ሌላ ሰዉ ወይ ሰለ ሌላ ሃገር ኣይደለም!!!!!! Pleace shire እናደርገዉ ስንት ሚድን ሰዉ ስላለ pleace
2012 #የአምስተኛውና የመጨረሻው የጽጌ ማኅሌት
ከሊቃውንቱ ጋር በጋራ ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።የዓመት ሰው ይበለን መልካም በዓል ስል መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

✥. ነግሥ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕጾሁ ሰላም
ጽጌያቲሁ ሥላሴሁ ለተዋህዶ ገዳም
መንገለ አሐዱ አምላክ ነዋየ መጻኢት ዓለም፤
ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤
እም አምልኮ ጣኦት ግልፍ አሐዱ ድህርም፡፡

✥ዚቅ፦
ወበጽጌት ምድረ አሠርጎከ ፨ ውስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፨ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ ፨ ወከመ ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ፨ ጒርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ
ዘወይጠል፨ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ።

✥ ኢየኃፍር ቀዊመ / ማኅሌተ ጽጌ /
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤
ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤
ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤
ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፡
ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡

✥ወረብ ፦
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ፤
ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ።
ዚቅ፦
እለትነብሩ ተንሥኡ፡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፡
ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፡
ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፡
ጽልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል ፡
መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡

✥. እንዘ ተሐቅፊዮ /ማኅሌተ ጽጌ/
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ፡፡

✥ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት።

✥ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎኅ ሠናይት፨ ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ
ጳጦስ ፨ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት፡፡

✥. ክበበ ጌራ ወርቅ / ማኅሌተ ጽጌ /
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፡ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

✥ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምንቆ ባሕርይ፤
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ ።

✥ዚቅ፦
አክሊል ዘእምጳዝዮን ተደለወ ፨ ጌራ ባሕርይ ወቀጸላ ወርቅ ጽሩይ፨
በቤተልሔም ተወልደ እምድንግል ብሥራትክሙ መሃይምናን ፨ እምአፈ ዮሐንስ
ሥርግው ተቀስመ አፈው ፨ ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማዕከለ አኃው፡፡

✥ ኅብረ ሐመልሚል / ማኅሌተ ጽጌ /
ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ
አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፡
ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፡
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፡
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፡
ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡

✥ወረብ፦
ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ፤
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት።

✥ዚቅ፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ ፨ ሃሌ ሉያ ፨ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ፨ ይግበሩ ለኪ
ኰሰኰሰ ወርቅ፡፡
✥. ተመየጢ / ሰቆቃወ ድንግል /
ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፡
ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፡
በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፡
ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ ፡
በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡

✥ወረብ፦
ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ፤
ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ።
ዚቅ፦
ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት፡
ወንርአይ ብኪ ሰላመ፡
ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፡
እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር፡
ሑረታቲሃ ዘበስን፡ ለወለተ አሚናዳብ፡፡

#የሰንበት #መዝሙር
ሃሌ ሉያ (በ፭) ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን ወፈርዪ ኲሉ ዕፀወ ወገዳም ቀንሞስ
ዕቊረ ማየ ልብን ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ጸገዩ ጽጌያት ጸገዩ ደንጓላት
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር። ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር
በስነ ጽጌያት ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር ። እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ
ለምሕረት ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር ። ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት
ወለመድኃኒት።

#አመላለስ #ዘመዝሙር
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት ወለመድኃኒት።

✥ 2012 ዓ.ም የጽጌ ማኅሌት ተፈጸመ ለቀጣይ ዓመት ቸር ያገናኘን ✥

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

@mezgebehaymanot ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ

በቴሌ ግራም
😘 " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም
@mezgebehaymanot ሰርች search በማድርግ ይቀላቀሉ😍

በ Facebook " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

መሰከረም 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ(ጣፎ)የተፃፈ ደጋሚ ተለቀቀ

ወስብሐት ወለመስቀሉ ክቡር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
በአንድ ወቅት አንድ አገልጋይ ቅዳሴ እያስቀደሰ
ያለቅሳል፡፡ አጠገቡ ያሉ ሰዎች "ምን አይነት ቅዱስ ልብ አለው?" ብለው ሲንሾካሾኩ ሰማ፡፡

ቅዳሴው ካለቀ በኋላ ልጁ ወደ አደነቁት ሰዎች ጠጋ ብሎ "እናንተ እንደኔ ያላለቀሳችሁት የምትጸጸቱበት በደል ስለሌለባችሁ ነው፡፡ እኔ ግን በጌታ ፊት ከሁሉ በደለኛ ስለሆንኩ ከእናንተ ተለይቼ ለማልቀስ ተገድጃለሁ" አላቸው፡፡

መንፈሳዊነትና ትህትና ክርስቶስን ወደ መምሰል የሚያድጉ የክርስቲያኖች ልዩ መገለጫ ናቸው፡፡
ይህንን Integrity,መልካም እሳቢ!! የተሰኘው የ Facebook ግሩፕ Join እንድርጋችሁ ጏደኞቻችሁን invite እንድታደርጉ በእግዚአቢሔር ስም እንጠይቃለን
የመንፈስ ቅዱስ በገና የሆነ ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ጌታ ልደት ከደረሰው ዝማሬ መካከል እንዲህና እንዲህ አለ

★ ★ ★

ብዙ ሴቶች "ድንግል ትጸንሳለች" የሚለውን ትንቢት ሰሙ የነገሥታት ሴት ልጆችና የባለጠጋ ልጆች [መሲሑን] ሊወልዱ በተስፋ ተጠባበቁ:: እርሱ ግን ከድሆች ልጅ ተወለደ::

ጌታ ሆይ በአንተ ምክንያት የነገሥታት ልጆች በድሆች ልጅ ቀኑ:: ወደ ደሃዋ ቤትም ነገሥታት እጅ መንሻ ይዘው ሔዱ

እናትህ በፍቅርና በፍርሃት ውስጥ ሆና በፊትህ መቆም ይገባታል:: ወደ ልጅዋ የምትጸልይ እናት : ወደ እናቱ ተስፋ የሚያደርግ ልጅ የሆነ አምላክ እንደምን ያለ ነው?

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

ዮሴፍ እግዚአብሔር ወልድን እንደ ሕፃንነቱ አቀፈው ፣ እንደ አምላክነቱም አገለገለው። በመሐሪነቱ እጅግ ደስ አለው በፈራጅነቱ ግን እጅግ ፈራው።

እንዲህ ሲል:
የልዑልን ልጅ ለእኔ እንደ ልጅ ይሆን ዘንድ ማን ሠጠኝ? እናትህ በጸነሰች ጊዜ ተቆጥቼ ነበር ፣ በስውር ልተዋትም አስቤ ነበር። በማኅፀንዋ ውስጥ ከድህነቴ ሊያወጣኝና ባለጠጋ ሊያደርገኝ የሚችል የተሰወረ ሀብት እንዳለ አላወቅሁም ነበር። ከእኔ ዘር የሚሆን ዳዊትስ አክሊል የደፋ ንጉሥ ነበር ፣ እኔ ግን የተናቀ ደሃ ሆንሁ። እንደርሱ ንጉሥ በመሆን ፈንታ አናጢ ሆንኩ። አሁን ግን እነሆ አክሊል ወደ ቤቴ መጣ ፣ የአክሊላት ሁሉ ጌታ በእቅፌ ነውና!

★ ★ ★

እናትህ በብዙ የምስጋና ቃል አመሰገነችህ : ያለ ወንድ ዘር መውለድ ለቻለች ለእርስዋ የምስጋና ቃል አይጠፋትም::

ድንግል ማርያም ሕፃኑን እያባበለች በመደነቅ ቃል ነደደች
እንዲህ ስትል
"ድንግሊቱን እጸንስ ዘንድ የሰጠኝ ማን ነው?
ይህንን አንድ ሲሆን የበዛ ፣ ታናሽ ሲሆን ታላቅ የሆነ ፣ ከእኔ ጋር ሲሆን በሁሉ የሞላ ሕፃን የሠጠኝ ማን ነው?
....
በእኔ [ማኅጸን] ውስጥ እያለህ ከእኔም ውጪ በሁሉ ቦታ ነበርህ ፣ በወለድሁህ ጊዜም ረቂቅ አምላክነትነህም ከእኔ ውስጥ አልወጣም። በእኔ ውስጥ ነህ ፣ ከእኔም ውጪ ነህ! ይህ ነገር ለእኔ ለእናትህን ያስደነቀኛል።

የሚታየው ሰውነህን በፊቴ ባየሁ ጊዜ የማይታየው አምላክነትህን በሕሊናዬ አየዋለሁ። ቅዱስ ሆይ በሚታየው ሰውነትህ ውስጥ አዳምን አየዋለሁ ፣ በማይታየው መለኮትህ ውስጥ ደግሞ በአንተ ሕልው ሆኖ የሚኖረውን እግዚአብሔር አብን አየዋለሁ።

አንተ ምንጭ ሆይ ለአንተ ለማጠጣት የጡቶችን ምንጭ እንዴት ልከፍታቸው ይቻለኛል? ሁሉን ከገበታህ የምትመግብ ሆይ እኔ አንተን ልመግብህ እንዴት ይቻለኛል? የክብርን ነጸብራቅ የተጎናፀፍከው ሆይ እንደምን በጨርቅ ልጠቀልልህ እችላለሁ?

ምን ብሎ እንደሚጠራህ አንደበቴ አያውቅም። አእላፋት ስሞች ለአንተ አይበቁህም ፣ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ስትሆን የሰው ልጅ ነህና ፣ የዳዊት ልጅ ስትሆን የማርያም ልጅ ነህና!

ልጄ ሆይ ከእኔ ጋር ሆነህ ሳለ ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር በመሆንህ አልቀናም። ለሚያምንብህ አምላክ ነህ ፣ ለሚያገለግልህ ጌታ ነህ ፣ ለሚወድህም ሁሉን ያንተ ታደርገው ዘንድ ወንድም ነህ!"

የአንደበቶች ሁሉ ጌታን አንደበት እንደሌለው ያደረገው ምን ይሆን? ልጄ ሆይ አንተን በድንግልና መፅነሴን ክፉ ሰዎች እየዘለፉ ነው።
ቅዱስ ሆይ ለእናትህ አንደበት ሁነኝ ፣ አንተን ከማን እንደፀነስሁህ ይረዱ ዘንድ ተአምርህን አሳይ።

ሁሉን የምትወድደው ሆይ ስለ አንተ ብዬ የተጠላሁ ሆንሁ ፣ ለሰው ልጆች መሸሸጊያ የሆንህ አንተን በመፅነሴ መከራን ተቀበልሁ።
አቤቱ በዮናስ ላይ እንደተቆጣ ባሕር በእናትህ ላይ ተቆጥቷል።
ሔሮድስ የተባለ ማዕበል የባሕርን ጌታ ሊይዝህ ፈልጓል። የእናትህ ፈጣሪዋ ሆይ ወዴት እንደምሸሽ ንገረኝ"

/የመንፈስ ቅዱስ እንዚራ ቅዱስ ኤፍሬም በየመዝሙራቱ መካከል ከተናገራቸው ተመርጦ የተተረጎመ/
ታኅሣሥ 23 2012 ዓ ም
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
(Hymns On the Nativity of Our Lord፣ St Ephrem the Syrian)
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ እምቅድስት ድንግል፤ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ፤አማን መንክር ስብሐተ ልደቱ፡፡ 🌲🌲🌲መልካም የልደት በአል ይሁንልን🌲🌲🌲