#አስቿካይ_መልክት
እባካቹ share share አድርጉ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ
አምላክ አሜን።
ውድ የተዋህዶ ልጆች ሆይ እየ ሆነብን ያለው ነገር አይምሮን የሚነካ ቢሆንም ሁላችንም በ አንድነት ማውገዝ ይንኖርብናል።
ነገሩ እንድህ ነው ከዝህ በፊት ማንም አያይም ብለው ከጫማ ስር የጌታችንን መስቀል አትመው ለገበያ አቀረቡ የዋው የሃገሬ ሰው አውቆም ሳያቅም ይሁን መስቅል እየረገጠ መሄድን ተያያዘው ......እርሱ አልበቃ ብሎ እሄው አሁን ደግሞ እንደ በፊቱ ሳይደብቁ በአደባባይ በምስሉ ላይ እንደምታዩት በየ ሸራው በየ ሲሊፔሩ በሁሉም ጫማ አትመው እሄው አቀረቡልን .....
ያውም የጌታችንን ስዕል
ያውም የእመቤታችንን
ያውም የቅዱሳን የመላእክቶችን ስእል....
ሰዓልለነ ቅድስት፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ማነው ደፍሮ አምላካችንን እመቤታችንን ቅዱሳንን መላእክትን ስእል ደፍሮ የእግሩ መርገጫ የሚያደርግ????
ስለዝህ የስው ልጅ ሆይ ንቃ እንንቃ እሄን ተግባር የሚፈጽሙ አለምን ተቆጣጥረን በአንድ መንግስት እንገዛለን የሚሉ Illuminati ስለ ሆኑ እራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል።
እሄንን ያደረጉት ዋናው አላማቸው ኢትዮጵያንና ተዋህዶንለማጥፋት ነው
ይገርማል....... ያኔ አባቶቻችን በ ባዶ እጃቸው ምን የመሳሰለ ከባድ መሳሪያ የያዘ ጣልያንን ሲረቱ ሃገራችን መች ጠፋች??? ኢትዮጵያ በመሆንክ/ሽ ኩራት ልኖረን ይገባል....
ያኔ በ አህመድ ግራኝ በዮዲት ጉዲት በጣልያን ያልጠፋች ተዋህዶ ዛሬ በነዝህ እባቦች እንዴት ትጠፋለች??? ወጣት ሃገርህን ሃይማኖትህን መጠበቅ ነው አባቶችም አንድነት ፈጥራቹ በፍቅር ቤ/ክንን ምሩልን ከ አውሬው ጠብቁልን ?? መምህራነ ወንጌልም ወክታዊ ጉዳይ ላይ አትኩራቹ ህዝብን አነቃቁ ...
እግዝአብሔር ሃገራችን ይጠብቅልን
ተዋህዶ ሃይማኖታችንንም ይጠብቅልን
በፍቅር በአንድነት በፍቅር ያኑረን።
ወስበሃተ ለእግዝአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክብር አሜን።
page like .......shere share
መምህር ምረትአብ አሰፋ ትምህርቶች Facebook page

✝ስለ እርሱ አንብቡ !
እግዚአብሔር በአሳባቸሁ ውስጥ እንዲኖር ስለ እርሱ አብዝታችሁ አንብቡ ።
እርሱን ለማወቅ ስለ እርሱ አንብቡ ። እርሱን ካላወቃችሁት እንዴት እርሱን ልትወዱት ትችላላችሁ ?
ስለ እርሱ አንብቡ ፤ ስታነቡ ግን በሳይንሳዊ ወይም በፍልስፍና ጠባይ አታንብቡ ወይም ደግሞ ስለ እርሱ ጥናታዊ ጽሑፍ ወይም ትምህርት ለመስጠት አታንብቡ ። ነገር ግን ወደ እርሱ ጥልቀት ለመግባት ወይም እርሱ ወደ እናንተ ጥልቀት እንዲገባ አንብቡ። ለነፍሳችሁ ውድ የሆኑትን የእርሱን ባሕርያት ለማወቅ ስትሉ አንብቡ ይህ እውቀት አሳባችሁ ከእርሱ ጋር እንዲጣበቅና ፍቅሩ ከእናንተ ልብ ጋር እንዲቀናጅ ያደርግላችኋልና ። ስለ ስምምነቱ ስትሉም አንብቡ ። ከወደዱት ሰዎች ጋር ስላለው ግንኙነት በጠላቶቹ ላይ ስላለው አቋም ስትሉ አንብቡ ! በጽሑፎች ውስጥ ስለ እርሱ " ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል ..." [ መዝ 44÷2] የሚለውን ቃል በማንበብ የእርሱን ውበት ታውቁ ዘንድ አንብቡ ።
እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቀምሳችሁ ታዩ ዘንድ ስለ እርሱ አንብቡ ። ታዲያ ንባባችሁ ለልባችሁ ምግብ እንዲሆን እንጂ እንዲሁ ተራ ንባብ እንዲሆን አትፍቀዱ ።
ስለ እግዚአብሔር ብዙ ካነበባችሁ በእርሱ ዘንድ ያለውን ፍጹምነት በሙሉ ታገኛላችሁ ። እርሱን ስለምትወዱትም በሰለሞን መዝሙር ውስጥ ካለችው ድንግል ጋር አብራችሁ "...እርሱ ፈጽሞ ያማረ ነው " [ መኃ 5÷16] ትላላችሁ ።
ከወደዳችሁት ስለ እርሱ ማንበባችሁን ትቀጥላላችሁ ። እግዚአብሔር ስለ እርሱ የሚያነቡትን ስለ እርሱ ዜና የሚጠይቁትን ከእርሱ ታሪኮች መካከል አንዱን ለማወቅ የሚናፍቁትንና እርሱን የሚያደንቁትን ሰዎች ይወዳቸዋል ። ስለ እርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከአባቶች ብሒሎች ወይም ከቤተክርስቲያንና ከቅዱሳን ታሪክ ልታነቡ ትችላላችሁ ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ ለመዳሰስ ስትሞክሩ በጥበቡ በኃይሉና በርኅራኄው ውስጥ እንደምትወዱት ታውቃላችሁ ።
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ !!

"ይቅርታ ማድረግ ያለፈን ስህተት መርሳት ነው።"
እ .. ረ .. ስ .. ቸ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!
አንድ ምስኪን ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ። ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት "እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ አንድ የቤት ስራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት! ሴትዬይቱም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ አንድ ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት። ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው። "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሐ ገብቼ የተውኩት አንድ ኃጢአት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሐ ገብቼ የተውኩት ኃጢአት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እሱን ከነገረሽ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት። ሴትዬይቱም ወደቤቷ ሄደች።
ተመልሳ እንደማትመጣ ግን ገምተው ነበር አባ ነገር ግን በበነጋው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው። አባም ሴትየዬቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ሀጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ "አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች "እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት "እረስቸዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡ እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!
እ .. ረ .. ስ .. ቸ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!
የሰው ልጅ ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብየሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል እግዚአብሔር ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው ፍቅር ነዋ፤ ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔርን በኛ መጠን መትረን ንስሐ በገባንበት ኃጢአት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔር እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ሂፆጱ ያጠበውን ኃጢአታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት እሾህ ራሳችንን የምንገርፍ? ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት ቤት በቀለለ! በህይወታችን የገፋንና ያቆሰለንን ሰው በደል ከመርሳትኮ ሺህ ጊዜ ፍሪዳ እያረዱ "እንታረቅ" ማለቱ እጅግ ቀላል ነውኮ ...! ለዚያም ነው መሰል ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት አስተምረን ባሉት ጊዜ "እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አንተም ይቅር በለን" ብላችሁ ፀልዩ ያለን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ የይቅርታ ዘመን ያድርግልን የይቅርታ ልብ ይስጠን!
(እዚሁ ፌስ ቡክ መንደር የተገኘ )

እግዚአብሔርን መስማት ያሳርፋል!
አለማችን እግዚአብሔርን ባለመስማት በመመላለሷ ረፍትን አጥታለች። እኛም እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ አለምን እየሰማን መቅበዝበዝን ጨምረናል፡፡ እግዚአብሔርን መስማት ከሁሉ የሚልቅ ሥጋዊና መንፈሳዊ ረፍት የሆነ ሐሴትን የሚሰጥ የህይወት ለውጥ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መስማት ማለትም በቅዱስ ቃሉ እለት እለት መታነፅ መመላለስ ክርስቶስን ለመምሰል በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት ጥረት ማድረግ ነው፡፡
እግዚአብሔርን መስማት ሰይጣንን ካለመስማት ብሎም ከመቃወም ይጀምራል! እግዚአብሔርን መስማት ስንጀምር የጠላትን ሀሳብና እቅድ አለመስማትን እናጠነክራለን፡፡ ይህች አለም የውጊያ ቀጠና ናት ውጊያውም በጦር፣ በሚሳኤል፣ በሚታይ በሚዳሰሰው ያይደል ረቂቅ በሆነው ጾም ጸሎት ስግደት በተለይም ቃሉን በመስማት በተባሉ መሳሪያዎች ከመንፈሳውያን ሰራዊት ጋር የምናደርገው ውጊያ ነው፡፡ ይህንን ውጊያ ለማሸነፍ እግዚአብሔርን እንስማ ለስሙም ክብርን እንስጥ፡፡
እግዚአብሔርን ባለመስማት ብዙዎቻችን በክርስቶስ አካልነት አንድ መሆናችንን ዘንግተን በዘር ቆጠራ በብሔር በሽታ ተለክፈን የክርስቶስ ብልት መሆናችንን እያጣነው እንገኛለን፡፡ እግዚአብሔርን ስንሰማ ከዚህ ደም ቆጠራ ወጥተን ሁላችን በክርስቶስ ደሙ እንደተዋጀን እናውቃለን መዋጀታችንንም እርስ በርስ ተፋቅረን አንድነታችንን አጠናክረን እናሳያለን፡፡ እንኳን ወዳጅን ጠላትን መውደድ እግዚአብሔርን በመስማት እንማራለን፡፡ ለዚህም እግዚአብሔርን በመስማታችን እረፍት ሰላም ፍቅር አንድነት ይሆንልናል፡፡
አምላካችን እንድንሰማው በቅዱስ መንፈሱ ይርዳን!የድንግል ምልጃዋ አይለየን፡፡
#ሸዋፈራሁ_ዘእንድርያስ

ይቅር ስትል በትክክል መኖር ትጀምራለህ ይቅር ማለት የደካማዎች አይደለም። የበደሉህን ይቅር ማለት የመንፈስ ጥንካሬ እና በራስ የመተማመን ምልክት ነው። ይቅር ስትል ታድጋለህ። ይቅር ስትል ልብህ ይሽራል። ይቅር ስትል ቀጥ ብለህ ትቆማለህ። ይቅር ስትል አይኖችህ ንፁህ ይሆናሉ ከዚያም ፊት ለፊትህ ያለውን መንገድ በግልፅ ታየዋለህ። ብስጩነት የመንፈስ ህመም ነው። ይቅር ስትል በትክክል መኖር ትጀምራለህ!
እግዚአብሔር ይቅርታ የሚጠይቅ አንደበትን ይቅር የሚል ልብን ያድለን።
#merkato_tube

አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።
ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።
(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ሽማግሌ ወደ አንድ የሞባይል ጥገና ሱቅ ሔዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ሥራልኝ" ብለው ሰጡት።
የሞባይል ጠጋኙ ስልኩን አገላብጦ ከፈተሸው በኋላ
"አባባ ስልክዎ ምንም አልሆነም ይሠራል" አላቸው።
ሽማግሌው ዓይናቸው ዕንባ አቀረረና
"ስልኩ ካልተበላሸ ... ልጆቼ የማይደውሉልኝ ለምንድን ነው?" አሉ በደከመ ድምፅ።
★ ★ ★
ለወላጆቻችን የምናደርገው ትልቁ ሥጦታ ቢኖር ጊዜ መሥጠት ነው። የመኖራቸው ትርጉም የሚገባን ሲለዩን ነው። ዕድለኛ ሆነን ወላጆቻችን በሕይወት ካሉ አሁኑኑ እንደውል። ይህንን ለማንበብ ጊዜ ካገኘን መቼም ለነሱ ለመደወል ጊዜ አናጣም።
"በምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም መልካምም እንዲሆንልህ እናትና አባትህን አክብር" ዘዳ 5:16
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Audio
ምስባክ፦
ዘያበቊል ሣዕረ ለእንስሳ
ወሐመልማለ ለቅኔ እጓለ እመሕያው
ከመ ያውጽእ እክለ እምድር መዝ ፻፫፥፲፬
ትርጉም፦
ለእንስሳ ሣርን የሚያበቅል እርሱ ነው
ለሰው ልጆች አገልግሎት ለምለሙን የሚያበቅል እርሱ ነው
እህልን ከምድር ያወጣ ዘንድ
ዘያበቊል ሣዕረ ለእንስሳ
ወሐመልማለ ለቅኔ እጓለ እመሕያው
ከመ ያውጽእ እክለ እምድር መዝ ፻፫፥፲፬
ትርጉም፦
ለእንስሳ ሣርን የሚያበቅል እርሱ ነው
ለሰው ልጆች አገልግሎት ለምለሙን የሚያበቅል እርሱ ነው
እህልን ከምድር ያወጣ ዘንድ
“አንኳኩቼ አላገኘሁም” አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡
አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ “ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጀሮን የፈጠረ ይሰማል!”
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ገጽ 178)

“መንፈሳዊው ገበሬ”
(በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
“አንድ ገበሬ ዘር መዝራት ስላለበት ብቻ እንዲሁ አይዘራም፡፡ አስቀድሞ መሬቱን ማረስ፣ ማለስለስ አለበት፡፡ ካረሰ ካለሰለሰ በኋላ ዘሩን ይዘራዋል፡፡ አሁንም ግን መዝራቱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የዘራውን ዘር አፈር ሊያለብሰው ይገባዋል፡፡ እንዲያ ካላደረገ ወፎች መጥተው ይለቅሙታልና፡፡ ልክ እንደዚሁ እኛ ክርስቲያኖችም በእኛ ላይ የተዘራውን ዘር (ቃለ እግዚአብሔር) በየጊዜው እንደ ገበሬው የማንከታተለው ከሆነ በአየር ላይ እንደተዘራ ዘር ይሆንብናል፡፡ ሰይጣን ይለቅምብናል፤ የራሳችን ስንፍና እንዲጠወልግ ያደርጓል፤ ፀሐይ ያደርቋል፤ ጐርፍ ይወስዷል፤ እሾክ አንቆ ይይዟል፡፡
ስለዚህ ዘር ዘርቶ ዞር ማለት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ በየጊዜው መኮትኮት፣ ወፎችን ማባረር፣ የበቀለ አረም ካለ ማረም፣ ጭንጫ የበዛበት አከባቢ ካለ የለሰለሰ አፈር መጨመር፣ በየጊዜው መከታተል፣ አጥር ማጠር፣ እንዲሁም ማንኛውም የተዘራውን እህል ሊያበላሹ የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ምናልባት በሰብሉ እርሻ የገበሬው ትጋት ብቻ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም መሬቱ ግዑዝ ነገር ስለሆነ፡፡ በመንፈሳዊው እርሻ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ኃላፊነቱ የገበሬው ማለትም የመምህሩ ብቻ አይደለም፡፡ ከግማሽ ወይም ከዚያ በላይ የደቀመዝሙሩ (የምእመኑ) ኃላፊነት ነው፡፡ በርግጥ መምህሩ ዘሩን መዝራት አለበት፡፡ ነገር ግን ደቀ መዝሙሩ የተነገረውን ቃል ሁል ጊዜ መስማት ብቻ ሳይሆን ማድረግም አለበት፤ በግብር ፍሬ ማፍራት አለበት፤ የበቀሉ አረሞች ካሉ በየጊዜው መንቀል አለበት፡፡
የገበሬ ልጆች በሰብሉ መካከል የበቀለ አረም ካለ እንዲሁ ጫፍ ጫፉን ብቻ አይቈርጡትም፡፡ ከሥር ይነቅሉትና በመጨረሻም በእሳት ያቃጥሉታል እንጂ፡፡ በእኛ ላይ የበቀሉ አረሞችም (ጥርጥሮች፣ ክሕደቶች፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ማነቆ የሆኑብንን ነገሮች…) ከሥራቸው ነቅለን ልናቃጥላቸው ይገባናል፡፡”

++ #አባቶቻችን_እንዲህ_አሉ ++
"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም"
#ቅዱስ_ባስልዮስ
"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" #ቅዱስ_ቄርሎስ_ሳድሳዊ
"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" #ቅዱስ_ቆጵሮሳዊ
"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
#ቅዱስ_አትናቴዎስ_ዘእስክንድርያ
"እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል።
#ሰማዕቱ_ዮስጦስ (100 AD-165 AD)
"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር"
#ሊቁ_ጠርጡለስ (160 AD - 220 AD)
‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር››
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ
"ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡
የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ"
#ቅዱስ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

ኢየሱስ ክርስቶስ፡-
“ጨለማን ያሳደደው ብርሃን ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና የማይነዋወጥ መሰረትና የማይፈርስ ግንብ የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማህደር የለዘበ ቀንበርና የቀለለ ሽክም እርሱ ለአባቱ ሃይል ጥበቡም የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
“ለሁሉ ያስባል ሁሉንም፡፡ ያጠግባል ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል፡፡ የተዘጉ መስኮቶችን ይከፍታል ህሙማንን ይሰማቸዋል፡፡ የተደፈነችውን ጆሮ እንድትሰማ ያደርጋል፡፡ ከሰውነት የለምፅን ልብሶች ገፍፎ የስጋን መጎናፀፊያ ያለብሳል፡፡ የደረቀውን የእጅ ክንድ ያቀናል፣ የአንካሳውን እግር እንዲሄድ ያደርጋል ነፍስን ወደ ሕዋስዋ ይመልሳታል መንፈስንም በማደሪያዋ ያኖራታል፡፡ አለቆች ባሏቸው አጋንንት የእርያን መንጋ ያሰጥማል ከደከመችውም ሰውነት ደዌን ያርቃል፡፡
“ከክንፍህ የፅድቅ ፀሃይና የጥቅም ምንጭ የሚወጣ የፅድቅ ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ ጌትነትና ክብር ምስጋናም ይገባሃል ለዘላለሙ አሜን፡፡”
(ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ)

"ፍልሰታ መጣች"
"ሕጻኑም ወጣቱም ወንዱም ሴቱም ዕድሜው የገፋውም ሁሉም በፍቅር የሚጾሟት፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድዔትና በረከት የሚታፈስባት፡ ፍቅረ እግዚአብሔር በሰው ልቡና የሚሰለጥንባት ፈሪሃ እግዚአብሔር የሚያይልባት፡ የንሰሐና የምህረት ጾም ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡ በዓለም ያሉ ወደ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ያሉ ወደ ገዳማት የሚገሰግሱባት ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡"
እንኳን አደረሰን አደረሳችን

ለጸሎት “ጊዜ የለኝም” ማለት እጅግ አስጸያፊና ዘግናኝ ኃጢዓት ነው። አንድ ሰራተኛ(ባሪያ) “አሰሪዬን(ጌታዬን) የማነጋገሪያ ጊዜ የለኝም” ቢል እንዴት ያለ ድፍረት ይሆን..?? ፍጡሩስ ከፈጣሪው ጋር ለመነጋገር “ጊዜ የለኝም“ ቢል ምን ይደንቅ! ዋጋ ቢስ ለሆኑ ምንም ረብ ለሌላቸው ንትርኮች ከበቂ በላይ ጊዜ አለህ። ምነው ታድያ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን እንደ ጊዜ ማባከን ቆጠርከው..??
ብፁዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ብፁዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
#ህዝበ_ክርስቲያኑ_በፍልሰታ ፆም ለሃገር ሰላምና ፍትህ እንዲፀልይና የተቸገሩትንም እንዲረዳ ጥሪ ቀረበ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ የፍልሰታ ፆም መግቢያን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ሰው ሠራሽ በሆነ ምክንያት በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙና ከቅያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ማሰብና መደገፍ ይገባል ብለዋል፡፡
ምዕመኑ በፍልሰታ ፆም ወቅት የተቸገሩትን ባለው አቅም ሁሉ እንዲደግፍ እና ለሀገር ሰላም የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፆመ ፍልሰታ ነሃሴ 1 ፣ 2011 ዓ.ም ይጀምራል፡፡
ምንጭ:- ዋልታ

ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የነፍስ ምግብ እንጅ
አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ የሚልበት እንጂ። ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም ጠባዩን ለመግራት እንጂ። ይህ በመሆኑም አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው ።
ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ ብቻውን አይጓዝም። ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ። ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም፤ መብላት ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ።
ጾም ነፍስ ከፍ ብላ ሥጋን ከእርስዋ ጋር ከፍ የምታደርግበት ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ሥጋ ጓዙንና ሸክሙን የሚያራግፍበት ጊዜ ስለሆነ እግዚአብሔር ያለ ምንም እገዳ ለመንፈሳዊ ዘላለማዊነት ደስታ የሚሠራበት ጊዜ ይሆናል። ጾም ማለት ነፍስና ሥጋ በኀብረት መንፈሳዊ ተግባር ለማከናውን የሚጠቀሙበት ጊዜ ነው። በጾም ወቅት ነፍስና ሥጋ የነፍስን ሥራ ለመሥራት ይተባበራሉ። ይህም ማለት ለጸሎት ለተመስጦ ለክብርና ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ለመጋራት ይተባበራሉ ማለት ነው።
ብጹዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
@popeshenoudaa

#ጾመ_ፍልሰታ (ክፍል ፩)
📌“ፍልሰታ” የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት ይነገራል።
📌ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሣቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው። ፍትሐ ነገስትአንቀጽ፲፭
ሃይማኖታዊ መሠረት
እመቤታችን ከአባቷ ከቅዱስ ኢያቄም እና ከእናቷ ከቅድስት ሐና ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በአድባረ በሊባኖስ ተወልዳለች። “እምሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት ፦ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች “እንደተባለ ። እመቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ መቅደስ ዐሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ ዘንድ ዐሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የውዳሴ ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የመልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬ ነው።
#ቅዱሳን_ሐዋርያት_እና_አስከሬኗ ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ና ሲያውኩን ይኖራሉ: አሁን ደግሞ እሷም ተነሣች፣ ዐረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን በእሳት እናቃጥላት ብለው ተነሱ፡፡ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው መልአክ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ፡፡ የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በዐረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው በዐሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ ዐሳረፉት ። በ ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰዱቃውያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ሥርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፡፡ ሊያስተምር ወደ ሌላ ቦታ ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሣኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እነዚያ ትንሣኤየን ዕርገቴንም አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡
ይቀጥላል......
🔸# ዲ/ን ብስራተማርያም

✝ የዋሓት ምንድን ነው ?
የዋሓት ከብልጣብልጥነትና ከአታላይነት ሕይወት ነጻ መሆን ማለት ነው ። ከገራገርነትና ከአለመከለል ጋር የማይያያዝ ነው ። መድኃኒታችን ለዘሪው ምሳሌ ገራገርነትን ፤ አለመከለል ፤ የዋኀትነትን በተለያየ ምሳሌ አቅርቦታል ።
የሕይወት ልምድ አለመኖር ከጭንጫ መሬት ጋር ተነጻጽሮ ቀርቧል ። ጭንጫ ምድር ለአትክልት ማብቀያ ሥፍራ ሆኖ አያገለግልም ። ዘር ሲወድቅበት ምንም ውጤት ሳይኖረው ወፎች የሚለቅሙት ይሆናል ። የሕይወት ልምድ የሌለው ዝንጉ ሰው ከሰዎች ተሞክሮ የሚማርበት ድርጊቶች ወደ እርሱ ይመጣሉ ።
እርሱ ግን ለመማር ፈቃደኛ አይደለም ። ነገሮችን አጥርቶ መመልከትም አይቻለውም ። የሕይወት ልምድ የሌለው ሰው ነገሮችን አይለይም ። እውነተኛ ፍርድንም አይጠነቀቅም ። ስለዚህ ራሱን ችግር ውስጥ ያገኛል ። የልምድ ማነስ የእውቀት ማነስና ባዶ ኩራት ያጅበዋል ።
#ግልብነት በድጋያማ ቦታን ይመስላል ጥልቀት የለውም ። በዚህ ድጋያማ ሥፍራ የሚወድቅ ዘር ዕጣ ፈንታው ምን ይሆናል ? ይበቅላል ነገር ግን ወደ ታች ሥፍራ ይዞ ይበቅል ዘንድ አይቻለውም ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ይሞታል ። ግልብነት #ነገሮችን_ከላይ_ከላይ_የሚመለከት_ሰው_ምሳሌ_ነው ። የነገሮችን ጥልቀት ትርጉም አይመረምርም አይረዳም ።
#የዋሓት የጥሩ መሬት ምሳሌ ነው ። ሠላሳ ፤ ስድሣ ፤ መቶ ያማረ ፍሬ የሚያፈራ ምድር ምሳሌ ነው ። የዋሓት ሌሎችን ባሕርያት ያሻሽላል ። ሰው የልምድ ማጠር ቢኖርበት ወይም አስቀድመን የጠቀስናቸው የሥጋ ባሕሪያት ቢሰለጥኑበት የዋኅ ከሆነ ይማራል ። ምክንያቱም #የዋኃት_የጥበብ_እጮኛ_ናት ። የዋኅ ሰው ወደ ጥበብ ይቀርባል ። #የዋኃት_የትሕትና_ልጅ_ነው ። ትእቢትና ትዝህርት የሰውን ልብ የሚከለክሉ ናቸው ። ትኅትናና የዋሓት የቅድስና መሣሪያዎች ናቸው ። የዋኀትን ገንዘብ ያደረገ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መፈጸም የሚያስገኝውን ሽልማት እያሰበ ከውለታ ነጻ ነው ። ግልብነት ድርጊትንም ውጤትንም አይመለከትም ። የሕይወት ልምድ ማነስ አንድ ሰው የሚሰራውን ሥራ ውጤት ከግምት ውስጥ የሚያስገባ አይደለም ።
#አቡነ_ሽኖዳ_ሳልሳዊ

✝#ጾመ_ፍልሰታ (ክፍል ፪)✝
#ትንሣኤና_ዕርገቷ
ከርሱ በቀር ማንንም ትንሣኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም (ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን ) መግነዟን ሰጥታው ዐረገች። +ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት ዕኮ» አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም » እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ጴጥሮስም አንተ እንጂ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም አንተ እየተጠራጠርክ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ አለው፡፡ እርሱም የያዘውን ያውቃልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሄዶ መቃበሩን ቢከፍተው አጣት ደንግጾ ቆመ «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው » ሁኔታውንም ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው ሰጣቸውም። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደ የአህጉረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።
📌በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ዕርገትሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት፤ ጥንታዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች። ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።
የእመቤታችን ትንሣኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ውኃፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ፲ ላይ « ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ይላል። በዚህም ምእመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እመቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች።
🔖ንጉስ ሰሎሞንም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ …ዉበቴ»” የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ « ወትቀውም ንግስት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኍብርት ፤ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንደ ዐረገ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት ። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን ዕረፍቷን ትንሣኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።
ጾሙን አጋንንትን ድል የምንነሳበትና የበረከት ያድርግልን !
ምንጭ ÷ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘእሑድ