የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
እግዚአብሔርን መስማት ያሳርፋል!

አለማችን እግዚአብሔርን ባለመስማት በመመላለሷ ረፍትን አጥታለች። እኛም እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ አለምን እየሰማን መቅበዝበዝን ጨምረናል፡፡ እግዚአብሔርን መስማት ከሁሉ የሚልቅ ሥጋዊና መንፈሳዊ ረፍት የሆነ ሐሴትን የሚሰጥ የህይወት ለውጥ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መስማት ማለትም በቅዱስ ቃሉ እለት እለት መታነፅ መመላለስ ክርስቶስን ለመምሰል በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት ጥረት ማድረግ ነው፡፡

እግዚአብሔርን መስማት ሰይጣንን ካለመስማት ብሎም ከመቃወም ይጀምራል! እግዚአብሔርን መስማት ስንጀምር የጠላትን ሀሳብና እቅድ አለመስማትን እናጠነክራለን፡፡ ይህች አለም የውጊያ ቀጠና ናት ውጊያውም በጦር፣ በሚሳኤል፣ በሚታይ በሚዳሰሰው ያይደል ረቂቅ በሆነው ጾም ጸሎት ስግደት በተለይም ቃሉን በመስማት በተባሉ መሳሪያዎች ከመንፈሳውያን ሰራዊት ጋር የምናደርገው ውጊያ ነው፡፡ ይህንን ውጊያ ለማሸነፍ እግዚአብሔርን እንስማ ለስሙም ክብርን እንስጥ፡፡

እግዚአብሔርን ባለመስማት ብዙዎቻችን በክርስቶስ አካልነት አንድ መሆናችንን ዘንግተን በዘር ቆጠራ በብሔር በሽታ ተለክፈን የክርስቶስ ብልት መሆናችንን እያጣነው እንገኛለን፡፡ እግዚአብሔርን ስንሰማ ከዚህ ደም ቆጠራ ወጥተን ሁላችን በክርስቶስ ደሙ እንደተዋጀን እናውቃለን መዋጀታችንንም እርስ በርስ ተፋቅረን አንድነታችንን አጠናክረን እናሳያለን፡፡ እንኳን ወዳጅን ጠላትን መውደድ እግዚአብሔርን በመስማት እንማራለን፡፡ ለዚህም እግዚአብሔርን በመስማታችን እረፍት ሰላም ፍቅር አንድነት ይሆንልናል፡፡
አምላካችን እንድንሰማው በቅዱስ መንፈሱ ይርዳን!የድንግል ምልጃዋ አይለየን፡፡

#ሸዋፈራሁ_ዘእንድርያስ