“ወጣትነህ ? “
ወጣት ነህን ወጣት በመሆንህ ገና ብዙ ዘመን አለኝ ዕድሜዬ ገና ነው ብለህ አትተማመን ተለክቶ የታወቀ ቀሪ ጊዜ ያለህም አድርገህ አታስብ ‹‹የጌታ ቀን ድንገት እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና›› 1ኛ ተሰ5፤2 ስለዚህ ምክንያት የእድሜያችንን መጨረሻ አስቀድመን እንዳናውቀው አደረገ ከዛሬ ዕለት ጀምሮ በትጋት ዝግጅታችንን እንጀምር ዘንድ በለጋ ዕድሜያችን ሲቀጩ በየቀኑ አታይምን ስለዚህም አንዱ ሲመክር እንዲህ ብሏል “ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አትዘግይ ከዛሬ ነገ እመለሳለሁ እያልህ አትቁጠር” ሲራ 5፤8 ዛሬ ነገ እመለሳለሁ ስትል አንድ ቀን ባቋራጭ እንዳትወሰድ፤ ስለዚህ ሽማግሌውም ይህንን ምክር ልብ ይበል ወጣቱም ይህንን ነገር ተረድቶ ተግባራዊ ያርግ ዘንድ ይሁን ወይስ በምቾትና ሁሉ ነገር ተሟልቶልህ የምትኖር እስካሁን ችግር የሚባል ደርሶብህ የማታውቅ ባለጸጋ ነህን እንዲህም ቢሆን ቅዱስ ጳውሎስ የሚለውን ስማው “ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል” 1ኛ ተሰ 5፤3 የዚህ ዓለም ነገሮች ሁሉ ተለዋዋጮች ናቸው እኛ በራሳችን የወደፊት ሕይወትና ሁኔታ ላይ ማዘዝ የምንችልና የሰለጠን አይደለንም ነገር ግን በጽድቅ ሥራ ላይ የሰለጠንን እንሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና››
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ ገጽ 134

October 24, 2018
ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ ክርስቶስ የሰጠህን ስጦታ ላልተፈረገ ግብር አታውለው፡፡ እጅን የሰጠህ እንድትሰርቅበት ሳይሆን ትእዛዛቱን እንድትፈጽምበት፣ በጎ ምግባርን እንድትሠራበት፣ ለጸሎት እንድትነሣበት፣ የወደቁትን እንድታነሣበት ነው፡፡ ጆሮን የሰጠህ ተርታ ወሬን እንድትሰማበት ሳይሆን ቃሉን እንድታደምጥበት ነው፡፡ አንደበትን የሰጠህ እንድትሰድብበትና እንድትረግምበት ሳይሆን እንድትዘምርበት፣ እንድታመሰግንበት፣ እንድትመክርበት ነው፡፡ እግርን የሰጠህ ወደ ክፋት ሳይሆን ወደ በጎ ስፍራ እንድትፋጠንበት ነው፡፡ ሆድን የሰጠህ ለመብል ሳይሆን ጥበብን እንድትማርበት ነው፡፡ ፈቲውን የሰጠህ እንድታመነዝርበትና እንድትዳራበት ሳይሆን ልጆችን ትወልድበት ዘንድ ነው፡፡ ልቡናን የሰጠህ ሰዎችን እንድትወቅስበት ሳይሆን እውነትን ታውቅበት ዘንድ ነው፡፡ ገንዘብንና ጉልበትን የሚሰጠን ሰማያዊ ቤታችንን እንድንሠራበት ነው፡፡ ...እንኪያስ የክርስቶስን ስጦታ በአግባቡ ተጠቀምበት፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
January 27, 2019
“ከነነዌ ሰዎች በላይ የከፉ ማን ነበር? ከነነዌ ሰዎች በላይ ግራውንና ቀኙን የማያውቅ ማን ነበር? ምንም እንኳን ድንጋይ ጠርበው ዕንጨት ቆርጠው የሚያመልኩ አሕዛብ ቢኾኑም፣ ምንም እንኳን ስለ ሀልወተ እግዚአብሔር ምንም ባያውቁም፣
ምንም እንኳን ስለ ፈሪሐ እግዚአብሔር ከማንም ነቢይ ባይማሩም ዮናስ መጥቶ አንዲት አረፍተ ነገር ስለ ነገራቸው ብቻ በሦስት ቀን ውስጥ ኹሉንም ተዉት፡፡ ዘማዊው ንጹሕ ኾነ፡፡ ስግብግቡ ለጋሽ ኾነ፡፡ ቁጡውና ተሳዳቢው መራቂ ኾነ፡፡ ሰነፉ ሰው ለጦም ለጸሎት ብርቱ ኾነ፡፡ ከክፋታቸውም አንዱን ወይም ኹለቱን ብቻ የተዉት አይደሉም፤ ኹሉንም ተዉት እንጂ፡፡ ምንም እንኳን የበደላቸው ጽዋ ሞልቶ መንበረ ጸባዖትን ለቁጣ የቀሰቀሰ የነበረ ቢኾንም ተመለሱ፡፡ ሲመለሱም እግዚአብሔር በቁጣ ሳይኾን በምሕረት ዓይን አያቸው፡፡ ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጸተ፡፡ ተወዳጆች ሆይ! የነነዌ ሰዎች ምንም አሕዛብ ቢኾኑም በሦስት ቀን ውስጥ ብቻ እንዲኽ ማራኪየኾነ ንስሐን ከገቡ፥ እጅግ ብዙ ዘመናትን ተምረን ያልተለወጥን እኛው ክርስቲያኖች እንደምን ይፈረድብን ይኾን?”
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
እንኳን ለጾመ ነነዌ በሰላም አደረሰን....ጾሙ ለሀገራችን ሰላምን የምንለምንበት ያድርግልን

February 17, 2019
“አንኳኩቼ አላገኘሁም” አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡
አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ “ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጀሮን የፈጠረ ይሰማል!”
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ገጽ 178)

July 22, 2019