የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
++ በሰንበት መፍረስ ++

የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡

ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡

ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ኝ የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡

እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!

ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 9 /2012 ዓ.ም.
ቪክቶሪያ
ፍቅር ምንድር ነው....???

እየሱስ ክርቶስ ወደ ምድር የመጣው ስለ ፍቅር ነው:: እየሱስ ክርስቶስ አዳምን ስላፈቀረው ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክትን ትቶ ስለ ፍቅር ብሎ መስዋእት ለመሆን መጥተዋል:: በመፅሐፍ ቅዱስም እየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ እንደሚያፈቅረው ይናገራል

በዚህ ዘመን ያለን ወጣቶችስ አፈቅርሻለሁ/አፈቅርሃለሁ ስንባባል የክርስቶስ ዓይነት መስዋእትነት መክፈል እንችላለን ....??

© ተመስገን ሓረጎት ህላዌ
፲፬/፭/፳፻፲፪
“እምነት” (TRUST)

ኦርቶዶክስ ስትሆን ክርስቶስ ወልድ ዋህድ፣ ፍጹም አምላክ ወሰብእ መሆኑን ለኛ ብሎ መከራ መቀበሉ መሰቀሉና በፍቃዱ ነፍሱ ከስጋው መለየቱ (መሞቱ) ከሙታን ተለይቶ መነሳቱን ማረጉን ተመልሶ በሙሉ ግርማው ለፍርድ እንደሚመጣ እናምናለን:: እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዘለዓለማዊ ድንግናዋ ፣ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ መሆንዋ ፣ ባማላጅነትዋ እናምናለን:: ቅዱሳን መላእክትም ባማልጅነታቸው አምነን እንቀበላለን ማረጋገጫ ብንጠየቅም ሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማረጋገጫ እናቀርባለን::

ኦርቶዶክስ ሆነን ሰውን ስናምነው(trust) እንዴት ነው ???

እንደ ማንኛውም ሰው እኛ ኦርቶዶክስውያን በተለያየ አጋጣሚ ብዙ ዓይነት ሰው እናገኛለን:: በእምነት፣ በስራ፣ በዜግነት ፣ በትምህርት ደረጃ ፣ በኢኮኖሚ አቅም የተለያየ እና የተደባለቀ ሰው እናገኛለን:: ታድያ እንዴት እንመናቸው ማንዋሉን ዓይተን እንዳንል ሰው ማንዋል የለውም ታድያ እዴት ነው ማወቅና ማመን እሚቻለው? እንደኔ እሚቻል አይመስለኝም ግን ማረግ እምንችለው አንድ ነገር አለ እሱም ለየትኛም ሰው ትክክለኛውን ክብር በመስጠት ቀና ቀናውን እያሰብን ከእኛ እሚጠበቀውን መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ:: እንደዚህ ስናረግ "ክፉ" ሰው እንደጅል ቆጥሮን ሊጎዳን ሊጠቀምብን ሊያታልለን ሊሞክር ይችላል ግን አይሳካለትም ምክንያቱም የሰራነው ስራ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው እና :: ግን እንዲህ ስንል ደግሞ ሁሌ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ መሆንን መርሳት የለብንም::

© ተመስገን ሓረጎት ህላዌ
፴/፭/፳፻፲፪
[የካቲት 4 በዓሏ የሚታሰብላት ከጒንጯ ደም የሚፈስሳት ተአምር አድራጊዋ የእመቤታችን ሥዕል እጅግ አስደናቂ ታሪክ (መነበብ የሚገባው)]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
የዚኽች አስደናቂ ሥዕልን ድንቅ ታሪክ ከመጻፌ በፊት ለወንጌል አገልግሎት ወደ ኖርዌ በኼድኊ ጊዜ ከጒንጮቿ ላይ ደም የሚፈስሳት ሁላችንም የምናውቃት የእመቤታችንን የታተመች ሥዕሏን በአንድ ወንድም ቤት ውስጥ በክብር ባማረ መልኩ ተቀምጣ አይቼ በመደነቅ፤ ሥዕሏን ከየት እንደገዛት ጠየቅኹት።

ርሱም በኖርዌ የዕቃ መሸጫ አጠገብ ወድቃ አግኝቶት ቶሎ ብሎ በገንዘቡ ገዝቷት፤ ቤቱ ወስዶ መብራት አብርቶ፤ ሽቱ ረጭቶ በክብር ባስቀመጣት ጊዜ ሌሊቱን ኹሉ እጅግ ዕጹብ ድንቅ የሚያሰኝ የዕጣን ሽታ ሲሸተውና የማዕጠንትና የምስጋና ድምፅ ሲሰማ እንዳደረ በነገረኝ ጊዜ፤ ልዑል እግዚአብሔርን በማመስገንና የተቀደሰ ሥዕሏን በመሳለም፤ የሥዕሏን ታሪክ ነገርኩት፡፡ ልጁ የገዛት ሥዕል ግን ዋናዋ የጥንቷ ናት ማለቴ ሳይኾን ያው አኹን የምንጠቀምባት ፖስት ያደረግኳት ዓይነት በዚያች በዋናዋ አምሳል የታተመችውንና የምትሸጠውን ሥዕል እንደኾነች ለማስታወቅ እፈልጋለኊ።

ይኽን በጥንት ጊዜ የነበራትን የተቀደሰ ታሪክ ለኹሉም መጻፍ እንዳለብኝ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበርና እነሆ ጊዜው ገጥሞልኝ በየካቲት 4 በመላው ዓለም በዓሏ የሚታሰብላትን ታሪኳን በበዓሏ ዕለት እነሆ ብያለኊ፡፡

ስለዚኽች ድንቅ ተአምር አባ ጽጌ ድንግል አስቀድሞ በማሕሌተ ጽጌ ላይ እንዲኽ ብሏት ነበር፡-
“ሥዕልኪ ማርያም ጸገየት ሥጋዌ
ከመ ዕፀ ገነት ትጸጊ ጽጌያተ ለሥርጋዌ
ሣሕለ ተአምርኪ እኩን ለትውልደ ትውልድ ዜናዌ
ቅብዕኒ ሐፈ ሥዕልኪ ወፈውስኒ እምደዌ
እስመ በኅምዙ አቊሰለኒ አርዌ”
(የገነት ዛፍ አበቦችን ለሽልማት እንደምታብብ ማርያም ሥዕልሽ ግዘፍን አበበች (ሥጋን የለበሰች መስላ ታየች)፤ የተአምርሽን ዜና ለልጅ ልጅ የምነግር እኾን ዘንድ የሥዕልሽን ወዝ ቀቢኝ፤ ከበሽታም አድኚኝ፤ አባብ አውሬ በመርዙ በኀጢአት አቊስሎኛልና) በማለት ተማፅኗታል፡፡

ይኸውም ከ829-842 ዓ.ም. በቤዛንታይን የነገሠው ንጉሥ ቴዎፍሎስ በቅዱሳት ሥዕላት ላይ በክፋት ተነሳሥቶ ዐዋጅ በማወጁ ወታደሮቹ በርሱ ትእዛዝ በእያንዳንዱ ቤት እየዞሩ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማጥፋት ፍተሻ ያደርጉ ነበር፤ በኒቅያ ከተማ አቅራቢያ አንዲት የተቀደሰች ሴት ነበረች፤ ቅዱስ ሉቃስ የሣላት የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም ውብ ሥዕሏን በቤቷ ውስጥ ደብቃ በማኖር በሥዕሏ ፊት መብራትን እያበራች ከልጇ እንድታማልዳት ትማፀን ነበር፡፡

የከሓዲው ንጉሥ ወታደሮቹም የአምላክ እናት ሥዕል በቤቷ እንዳለች በማወቃቸው ወደ ቤቷ በድንገት ዘልቀው ገቡ፤ ከመካላቸውም አንዱ ወታደር የእመቤታችንን ሥዕሏን በያዘው ጦር ጒንጯ ላይ ወጋት፡፡ ኾኖም ግን በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይኽ ክፉ ሥራው በተአምር ተተክቶ፤ ከተወጋው ከአምላክ እናት ፊት ላይ ደም ይፈስስ ጀመር፡፡

ይኽን ግሩምና ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜ ወታደሮቹ ደንግጠው ሸሽተዋል፤ ሴቲቱም ይኽነን ድንቅ ተአምር ባየች ጊዜ ሌሊቱን ሙሉ በሥዕሏ ፊት መብራትን አብርታ በአምላክ እናት በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ስትጸልይ ዐደረች፤ በነጋታውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ከጒንጮቿ ደም የፈሰሳትን የአምላክ እናት ሥዕሏን በባሕሩ ላይ እንድታስቀምጥ ታዘዘችና አስቀመጠቻት።

ሥዕሏም በባሕሩ ላይ በመንሳፈፍ በማዕበሉ እየተነዳች ያለምንም መስጠምና መርጠብ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ጉዞዋን አድርጋ ወደ አቶስ ደረሰች፡፡ ጊዜያቶች ካለፉ በኋላ ከዕለታት በአንዳቸው ምሽት በአቶስ ተራራ የአይቬሮን ገዳም መነኮሳት የብርሃን ምሰሶ በባሕሩ ላይ ተተክሎ እንደ ፀሓይ ሲያበራ ተመለከቱ፡፡

ይኽም ተአምር ለተካታታይ ቀናቶች በመቀጠላቸው በዚያ የተቀደሰ ተራራ በምናኔ ያሉ አባቶች ኹሉ በአንድ ላይ ተሰባስበው በማድነቅ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት ሥዕል በላዩ ላይ ወደ ተንሳፈፈበት ወደ ባሕሩ በመውረድ ወደ ሥዕሏ ለመጠጋት ቢሞክሩም ሥዕሏ ወደ ኋላዋ እየተመለሰች ሊያነሷት አልተቻላቸውም፡፡

በዚያው የአይቮሪዮን ገዳም ረድእ (የጉልበት አገልጋይ) ኾኖ የሚኖር አባ ገብርኤል የተባለው መነኩሴ ብቻ ሥዕሏን ከባሕር ውስጥ ማንሣት የሚችል እንደኾነ የአምላክ እናት ለመነኮሳቱ ገለጠችላቸው፤ በተመሳሳይም ለአባ ገብርኤል እመቤታችን ተገልጣለት “ወደ ባሕሩ ኺድ፤ ማዕበሉንም ሳትፈራ በባሕሩ ውስጥ በእምነት ተጓዝ፤ እናም ኹሉም ለዚኽ አንተ ላለኽበት ገዳም ያለችን ፍቅርና ርኅራኄ ምስክር እንዲኾኑ፤ ሥዕሌን ከባሕር አውጣ” በማለት ነገረችው፡፡

ከዚያም በአቶስ ተራራ ያሉት መናንያን ኹሉ አባ ገብርኤልን ይዘው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው፣ እያመሰገኑ፤ በማዕጠንታቸው ዕጣን እያጠኑ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት ሥዕል ወዳለበት ወደ ባሕሩ ኼዱ፤ አባ ገብርኤልም በደረቅ መሬት እንደሚጓዝ ያለምንም ፍርሃት ወደ ባሕሩ ውስጥ በመግባት በናፍቆት ኾኖ የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን በደረቱ ታቅፎ ተሳለማትና ወደ ባሕር ዳርቻ ይዟት ወጣ፤ እነርሱም በደስታ ኾነው እጅ ነሷት፡፡

ከዚያም ማግሰኞ በጠዋቱ ሥዕሏ ባረፈበት ቦታ ላይ በሚያመሰግኑበት ጊዜ ቀዝቃዛና ጣፋጭ ውሃ ከምድር ላይ ፈለቀላቸው፡፡ ከዚያም የእመቤታችንን ሥዕሏን በታላቅ ክብር በምስጋና ይዘው በመኼድ ወደ ቤተ መቅደስ አግብተው በመንበሩ ላይ አስቀመጧት፡፡

ነገር ግን በነጋታው መነኮሳቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መብራት ሲያበሩ የእመቤታችን ሥዕሏን ባስቀመጡበት ቦታ አላገኟትም፤ ይልቁኑ በመግቢያው በር ባለው ግድግዳ ላይ ተሰቅላ አገኟት፤ እነርሱም መልሰው በቦታዋ ላይ ቢያኖሯትም ተመልሳ በገዳሙ መግቢያ ላይ ተሰቅላ ያገኟት ነበር፤ ከዚያም እመቤታችን ለአባ ገብርኤል ተገልጻለት “ለወንድሞች እንዲኽ ብለኽ ንገራቸው፤ ከዚኽ በኋላ ሥዕሌን ማግባት የለባቸውም፤ የእኔስ ፈቃድ በእናንተ ልጠበቅ ሳይኾን እኔን በምልጃዬ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ልጋርዳችኊ እንጂ፤ ሥዕሌን በገዳሙ በምታዩበት ጊዜ ኹሉ የልጄ ምሕረትና ጸጋ ከእናንተ አይቋረጥም” አለችው፡፡

መነኮሳቱም ይኽነን ሰምተው በእጅጉ በመደሰት ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ክብር በገዳሙ በር አጠገብ አነስ ያለች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ገባሪተ ተአምራት ወመንክራት (ድንቅ ተአምር አድራጊዋን) የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን ወደ ውስጥ አገቧት፤ የተቀደሰች የሥዕሏ መጠሪያም “የአይቬሮኗ የአምላክ እናት” ስትባል በግሪክ “ፓርታኢቲሳ” ትባላለች።

ከዚያም በአይቬሮን ገዳም ያለችው የእመቤታችን ሥዕል ድንቅ ተአምር በዓለም ኹሉ ላይ ከተሰማ በኋላ በረከቷን ለማግኘት ክርስቲያኖች ወደዚያች ገዳም መኼድን ጀመሩ፤ ይኽ የተቀደሰ ሥዕሏና ታሪኳም ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለሙ ኹሉ ላይ ተሰማ፤ ዛሬም ምእመናን ይማፀኑበታል፡፡

ለአባ ገብርኤል የተለመነች እና በረከቷን እንዳሳደረችበት ዛሬም የምልጃዋ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም እንዳይለየኝ በመማፀን አባ ጽጌ ድንግል ስለዚኽች ሥዕል በማሕሌተ ጽጌ ላይ ባመሰገናት ምስጋና ጽሑፉን አበቃለኊ፡፡

“ቦ አመ ትትረከብ ምስለ ቃለ ነገር ጥዑም
ወቦ አመ ትትረአይ በለቢሰ አባል ልምሉም
ሥዕልኪ ማርያም ጽጌ ተአምር አዳም
ወአመ ዘበጣ በሰይፍ አይሁዳዊ ርጉም
እምኔሃ አንጸፍጸፈ ደም”
(ሥዕልሽ ቃልን ደስ ከሚያሰኝ ነገር ጋራ የምትገኝበት ጊዜ አለ፤ የለመለመ አካልንም ለብሳ የምትታይበት ጊዜ አለ፤ ማርያም ሥዕልሽ የተአምር አበባ ናት፤ ርጉም አይሁዳዊ በሰይፍ በመታት ጊዜ ከርሷ ሥዕል ደም ተንጠባጠበ) ይላል፡፡

የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በምልጃሽ እና በቃል ኪዳንሽ የማይጠገበው በረከትሽን ዕጽፍ ድርብ አድርገሽ አሳድርቢን፤ እስቲ እናንተም በተቻላችኊ መጠን በተሰማችኊ ልክ አመስግኗት። እመቤታችንም በዓለም ላይ ከፈሰሰው መቅሠፍት በቃል ኪዳኗ ትጠብቀን።
መንነት ዶ ይሽወጥ እዩ ......???

ኣብ ሕሉፍ እዋናት ናይ ክርስትና በዓላት ብፍላይ ደማ ናይ ኦርቶዶክስ ተውዋህዶ በዓላት ምኽንያት ብምግባር ዝዳለው ናይ ደርፍን ዳንኬራን ምሸታት ከምዝተቃወምና ዝፍለጥ እዩ:: ይኹን እምበር ሕዚ ኸኣ ካብኡ ብዝገደደ መንገዲ ጾምያ ኽኣቱ ኢሉ እሞ ንዑ ዕበዱታ ምባል ጀሚሮም ኣለው:: እዙይ ፍፁም ተቀባልነት ዘይብሉ ሃለውለው እዩ::
ከም ኣስተምህሮ ቤተክርስቲያንና ደርፍን ስኽራንን ካብቶም ዓበይቲ ሓጥያታት ዝቁፀሩ እዮም:: ብኸመይ ሒሳብ እዩ ደኣ ጾም ይኣቱ እሎ እሞ ንዑ ንዝለል ዝብሉና ...? ብናይ ቤተክርስቲያን ስራዓት ጾም እንትኣቱ ሓደ ኦርቶዶክስ ከም ኦርቶዶክስ ክገብሮም ዝግበኦ ነገራት ኣሎ:: ንሳቶም ኸዓ ናይ መንፈስ ድልነት ፣ ይቅረ ምባል ፣ ዝተፃላእናዮ ምትዕራቅ ፣ ዝፈፀምናዮ ሓጥያት እንተድኣ ሃልዩ ናብ መምህር ንስሃና ቀሪብና ምንዛዝን (ምንሳህ) ቀኖናና ምቅባልን ፣ ኣብቲ ጾም ግዘ እንህቦ መባእ ምድላውን ነዚኦም ዝኣመሰሉ ተግባራት ምፍፃም እዮም:: ካበይ ብዘምፅእዎ ኣስተምህሮ እዩ ደኣ ጾም መሐዚ ኮንሰርት ብዝብል መፈክ መንነትኹም ሽጡ ኦርቶዶክስነትኩም ዝብሉና ዘለው ......? ደቂ ኦርቶዶክስ ንሕበር ብሓባር ብምኳን ናብቲ ዝበሃል ዘሎ ቦታ ብዘይ ምኻድ ታሪኽ ንስራሕ::

© ተመስገን ሓረጎት ህላዌ
፱/፮/፳፻፲፪
በድሮ ጊዜ በባሕር ዳር የሚኖሩና ከዓሣ ውጪ ሌላ ምግብ የሌላቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህን ሰዎች ዓሣም ጭምር ጹሙ ማለት ሙቱ እንደማለት ነው፡፡ ክርስትና ግን ምንም አማራጭ የሌለው ጠባብ ሃይማኖት አይደለም፡፡ ስለዚህ ለእነዚህ ሰዎች ዓሣ እንዲበሉ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ አሁን እኛ ዓሣ እንብላ ብንል ምንም ምክንያት የለንም፡፡ ምክንያቱም ሌላ ምግብ አለንና፡፡ ስለዚህ ይህ ቀኖና ለእነዚህ ሰዎች ብቻ የሚሠራ እንጂ ለእኛ አይደለምና ይህንን አውቀን በጾም ጊዜ ዓሣ ከመብላት እንቆጠብ፡፡ መልካም ጾም ይሁንልን ይሁንላችሁ!!!
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ቃል የተቀበለችበት በዓል መታሰቢያ አደረሰን፡፡
በዕለቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚቀርበውን የምስጋና ቃል እንደሚከተለው አቅርበናል መልካም በዓል፡፡

ዋዜማ
ሃሌ ሉያ (፬) ርግብየ ይቤላ በእንተ የዋሃታ፤
በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ፤
እንዘ አመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤

ምልጣን
እንዘ አመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤

እግዚአብሔር ነግሠ
እንተ ክርስቶስ በግዕት እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ብሔር፤
በቤተልሔም አስተብረከት ዕጓለ አንበሳ ግሩመ ወለደት፡፡

ይትባረክ
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤
ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፡፡

ሰላም
ሃሌ ሉያ (3) ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋትሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤
የሐንፁ አሕዛብ አረፋተኪ በዕንቊ ክቡር፤
ወመሠረትኪ በወርቅ ንጹሕ ይሰግዱ ለኪ ውስተ ገጸ ምድር፤
በእንተ ዕበየ ክብርኪ አምላከ ፳ኤል ውእቱ ረዳኢኪ
ዘአድኀነኪ እምእደ ጸላዕትኪ፤
ወረሰየ ሰላመ ለበሐውርትኪ፡፡

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፡
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፡
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ፡
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል
ዚቅ
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤
እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፤
ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤
ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤
ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ፤
ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ;
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪየኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
ዚቅ
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኀኒት ለነፍስ ወሥጋ፤
እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ፤
ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዩ ፍኖተ፤
ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ መድኀኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ፡፡

መልክዐ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤
አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡
ዚቅ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤ አመ ይሰደድ እምገነት፡፡

ሰላም ለአእዛንኪ እለ ተበሥራ ኪዳነ፤
እም አፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ፤
አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእይኒ ደይነ ፤
እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ ፤
ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ፡፡
ዚቅ
ኪዳንኪ ኮነ ለኃጥአን ቤዛነ፣ ኪዳንኪ ኮነ ፣ ኪዳንኪ ኮነ ፤
ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ፡፡

ሰላም ለመዛርዒኪ ወለኵርናዕኪ ምጽንጋዕ፤
እለ ሐቀፋሁ ለክርስቶስ ባሕርየ መለኮት ኅቡእ፤
ማርያም ኅሪት እምነ መላእክት ወሰብእ፤
ተዝካረኪ ለእመ ገብረ በተአምኖ ጽኑዕ፤
በመንግሥተ ሰማይ ምስሌኪ ይነግሥ ኃጥእ፡፡
ዚቅ
አመ ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን ፤
ክፍልኒ ድንግል እቁም በየማን ፤
ምስለ አባግዕ ቡሩካን፡፡

ሰላም ለድንግልናኪ መክብበ ሕዋሳት ሐምስ፤
ወለአቊያጽኪ ክልኤ አዕማደ ነባቢት መቅደስ፤
ማርያም ታቦት ወጽላተ ኪዳን ሐዲስ፤
ቅብዕኒ ርጢነ ደም እስከ ሰኰና እግር ወርእስ፤
እስመ ደም ትፌውስ ሕማማ ለነፍስ፡፡

ዚቅ
ጾም ትፌውስ ቊስለ ነፍስ፤ ወታጸምም ኵሎ ፍትወታተ ዘሥጋ፤
ትሜሕሮሙ ለወራዙት ጽሙና ፤
እስመ ሙሴኒ ጾመ በደብረ ሲና፡፡

ሰላም ለመልክዕኪ እመልክዐ ሐና ወኤልሳቤጥ፤
ዘብዑድ ሥኑ ወልምላሜሁ ፍሉጥ፤
ማርያም ቅድስት ድንግልተ አፍአ ወውስጥ፤
ቤዛ ይኩነኒ ኪዳንኪ በገጸ ፈጣሪ ሥሉጥ፤
አመ ወርኀ ነጊድ የሐልቅ ወይጸራዕ ሤጥ
ዚቅ
ቃለ እግዚአብሔር እምድንግል አስተርአየ ፤
ኤልሳቤጥ ኮነት እስመ ወለደት ነቢየ፡፡

ምልጣን
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤
ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ ፤
አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ ፤
አማን ኪዳንኪ ኢየኃልቅ፡፡

እስመ ለዓለም
አድኅኒ እግዚኦ እምብእሲ እኩይ ፤
እምሰብእ ዓማፂ ወሐባሊ ባልሐኒ፤
እስመ አንተ ትቤ እግዚኦ ተመየጡ ኀቤየ፤
እዜከር ኪዳንየ ዘመሐልኩ ላቲ ለማርያም እምየ፤
ወፈኖክዎ ለዮናስ ብሔረ ነነዌ ከመ ይስብክ ሎሙ፤
ወእምዝ ጾሙ ወጸለዩ ሰብአ ነነዌ ወነስሑ፤
እግዚአብሔር ይቤ ዘጾመ ወጸለየ ወሰአለ እሙነ ይነሥእ ዕሤቶ ፡፡

አቡን
ሃሌ ሉያ ትቤላ ኤልሳቤጥ ለማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ሃሌ ሉያ፤
ሶበ ሰማዕኩ ቃለኪ፤ አንፈርዓፀ ዕጓል በውስተ ከርሥየ ፤
በፍሥሐ ወበሐሴት ሃሌ ሉያ፤
ወብፅዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ዘነገሩኪ በኀበ ልዑል ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወትቤ ማርያም ኵሉ ትውልድ ያስተበጽዑኒ፡፡

አራራይ
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ፤
ንባብኪ አዳም ከመ ፍሕሦ ቀይሕ ከናፍርኪ፤
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል ፤
ኢሳይያስኒ ይቤላ ሐዳስዩ ጣዕዋ ፤
ሰሎሞን ይቤላ እምአርምሞትኪ አዕይንትኪ ዘርግብ

ሰላም
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል ወኵሉ ነገራ በሰላም፡፡
++++
ወዴት እያመራን ነው....???

በዓለም ውስጥ ስንኖር ብዙ ዓይነት ግጭቶችን እናያለን:: ከቀላሉ የወንድም እና እህት የቤት ግጭት ጀምሮ እስከ ከባዱ የሂወት መስዋእትነት እሚያስከፍለው በአገራት መካከል እሚደረገው ጦርነት ድረስ እንመለከታለን::በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ ግጭቶች ሲፈጠሩ የማርገብያና የማስማምያ መንገዶቹ ለማየትም እንታደላለን::
ቤት ውስጥ ወንድማማቾች እና እህትማማቾች ሲጣሉ መክሮ ተቆጥቶ እሚያስማማ ወላጅ ኣባት ወይንም እናት ነው:: እናት እና ኣባት ( ባል እና ሚስት) ሲጣሉ ደግሞ የደረሰ ልጅ ካላቸው ልጃቸው ለማስማማት ይሞክራል:: ይሄ ካልተሳካ በሁለቱም ውገን ያሉት የቅርብ ቤተሰቦች ለመምከር እና ለማስማማት ይሞክራሉ:: ይህኛው ካልተሳካ ግን ቤተሰቡ በሙሉ ተሰብስቦ መምህረ ንሰሃቸውንም (የንስሃ ኣባታቸው) ነግረው እንዲመከሩ እና ችግራቸው እንዲፈቱ ይደረጋል::

"አገራት ሲጣሉስ....?"

በሁለቱም ወገን ያሉት የሃይማኖት መሪዋች የአገር ሽማግሌዎች ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በመሰባሰብ አገሮቹን ለማስማማት ይሞክራሉ:: በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያለ አማኝ ህዝብ ባላት አገር በሚያምነው ታቦት በሚሳለመው ደብር ተጠርቶ ቢለመን የታቦቴ ስም ከተነሳ ይቅርብኝ እናዳላችሁ ይሁን ብሎ የሚመለስ ህዝብ በሞላባት አገር ሃይምኖት እና የሃይማኖት መሪዎች ለሰላምም ይሁን ለጦርነት ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ::

ታድያ አሁን ምን ገጠመው .......?

ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ እንደሚያውቀው መነኩሴ አገር የለውም :: ምክንያቱም ይህንን ዓለም በቃኝ አልፈልገውም ብሎ ረግጦ እንደቆሻሻ ጥሎ የአምላክ መንገድ ፍለጋ ሁሉም ነገሩ ለአምላክ ሰጥቶ እሚኖር ስለሆነ:: በጳጳሳት እና ኤጲስ ቆጶሳት ደግሞ የበለጠ ይከብዳል ምክንያቱም ህዝቡን እንደ ጎበዝ እረኛ መጠበቅ ስላለበት:: ታድያ ጳጳስ ሲኮን የሚጠብቁት ህዝብ የትውልድ ቦታቸው ሳይሆን ሲኖዶሱ የወሰነላቸውን ነው ::ሲኖዶሱ ከፈቀደላቸው ተግባር በተቃራኒ መስራት የተከለከለ ነው :: ታድያ ሰሞኑን እያየነው ያለውን ነገር ምንድር ነው? የሲኖዶሱ አባላት የሲኖዶሱ ውሳኔ ተቃውመው አደባባይ ላይ እስከ መውጣት ደርስዋል:: ይህ ምን ማለት ነው... ? ምንስ አንድምታ አለው ... ? መልሱን ለአምባብያን ትቻለሁ:: ሰላም

ኦርቶዶክስ ክብሬ
ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር !!!

© ተመስገን ሓረጎት ህላዌ
፲፮/፮/፳፻፲፪
"የጾም ጥቅሙ ምንድር ነው ...??"

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

ከምግብና ከመጠጥ ያልተቆጠበ ሰው ለክርስቶስ ሕይወቱን መስጠት እንደሚከብደው ግልጽ ነው። ድፍረት ያላት ነፍስ ቀጣይነት ባለው መንፈሳዊ ልምምድ ራስን መግዛት ለሥጋ ፈቃድ የሚያስፈልገውን ምግብና መጠጥ በመተው የሥጋ ፈቃድን ድል መንሳትንና የሥጋ ፈቃድ ለነፍስ ፈቃድ ማስገዛት ይቻላታል። ይህች ነፍስ የሚመጣባትን ከባድ ነገር ሁሉ እስራትም ቢሆን ግርፋትም ቢሆን መቋቋም ይቻላታል።

በእግዚአብሔርና በተጋድሎ የፀኑ ሰዎች ሥጋቸውን እስከሞት ድረስ አሳልፈው በመስጠት ሰማዕትነትን መቀበል ይቻላቸዋል። በአካላዊ ስሜት ብቻ ሳይሆን ከመጾም በሚገኘው መንፈሳዊ ጥቅም ሰማዕታት ጾምን የስልጠና ትምህርት ቤት አድርገውታል። የጾም ቀናት የሚጠቅሙን ለመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ በኃጢአታችን እንድንፀፀት እና ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ብቻ ሳይሆን ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ያለንን ፍቅር ለመግለጽም ይጠቅሙናል። ሰማዕታት የጾምን፣የፀሎትን እና የብሕትውናን ሕይወት የኖሩ ናቸው። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው በዚህችም ዓለም የሚጠቅሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ የዚህች ዓለም መልክ አላፊ ነው"1ኛ ቆሮ 7፥34

እውነተኛ ጾም አንድን ሰው ራሱን እንዴት መቆጣጠር እንዳለበት ያሰለጥነዋል። ቀሪ ሕይወቱን እንዴት መኖር እንዳለበት እንዲያውቅ ያደርገዋል። ራስን መቆጣጠር ለቅድስና ሕይወት መሠረት ነው። ጾም ቅጣት ሳይሆን ደስታ ነው።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ (የሕይወት መዓዛ)
Like our page on Facebook
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
የተወደዳችሁ ምዕመናን እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚቀበለውን ህይወት ለመኖር አንፈልጋለን? ለመሆኑ ይህ ሊሆን የሚችለው እንዴት ብንመላለስ ነው? መልሱን ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮቱ ከንቱ ነው፡፡ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ወላጆች የሌሉአቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በችግራቸው መጠየቅ በዓለምም ከሚገኝ ርኩሰት ሰውነትን መጠበቅ ነው፡፡›› በማለት ይመልስልናል( ያዕ 1፡26-27)፡፡ በክርስቶስ ደም የተቀደሰና የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰውነታችንን በዓለም ከሚገኝ ርኩሰት መጠበቅ የሰማያዊ ርስት ወራሾች ያደርገናል፡፡ በዓለም የሚገኘውን ርኩሰትም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የሥጋ ሥራ›› በማለት ገልጾታል፡፡ ‹‹እርሱም ዝሙት፣ርኩሰት፣መዳራት፣ጣዖት ማምለክ፣ሥራይ ማድረግ፣ መጣላት፣ ኩራት፣ የምንዝር ጌጥ፣ ቅናት፣ ቁጣ፣ ጥርጥር፣ ፉክክር፣ምቀኝነት፣ ዘፋኝነት፣ መጋደል፣ ስካር ፣ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው፡፡›› እነዚህን የሚያደርጉ ሰዎችም ከመንግስተ እግዚአብሔር በአፍአ ወይም በውጭ እንደሚቀሩ ሲያስረዳ ‹‹አስቀድሜ እንደነገርኋችሁ ይህን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን መንግስት አያይም›› ብሏል ( ገላ5፡19)።
እናም ሁላችንም ህዝበ ክርስትያን በዚህ የጾም ወቅት ከእነዚህ የስጋ ስራዎች በመቆጠብ ለራሳችን ፣ለሕዝባችን ፣ለሃገራችን እና ለዓለም ሁሉ ምህረት እምንለምንበት መሆን አለበት::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር!!!

© ተመስገን ሓረጎት ህላዌ
፳፫/፮/፳፻፲፪
ክርስቶስ vs በርባን

ክብር ለእርሱ ይድረስ እና አምላካችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከ በርባን ጋራ እሚነፃፀር ሆኖ አደለም vs ብለን ያቀረብናቸው ነገር ግን ክርስቶስ በመዋእለ ስጋዌው አይሁዶች ጲላጦስ ፊት አስቁመው ከሰውት ነበረ :: ጲላቶስም ከመረመረው
ቡሃላ ከበደል ሁሉ ነፃ መሆኑን ያውቅ ነበር እና ደግሞም ፋሲካም ነበረና እንደልማዳቸው የሞት ፍርዱን ያስቀሩታል ብሎ በማሰብ ክርስቶስ ልፍታላቹህ ወይስ በርባንን ብሎ ጠየቃቸው :: በፋሲካ አንድ እስረኛ የመፍታት ባህሉን ነበራቸው እና ::

በርባን ማን ነው ??
በርባንማለት በአገሪቱ የታወቀ ወንጀለኛ ሲሆን ከወንጀሉም ብዛት የተነሳ ታስሮ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ሞቱን የሚጠባበቅ ሰው ነው ::

ጲላጦስንም ይሄንን ስለሚያውቅ ሁለት ተቃራኒ የሆኑትን ለንፅፅር እንኳን እማይመቹትን ለንፅፅር ኣቀረበላቸው :: ለአይሁዳውያኑ እና ለካህናት አለቆች ግን ምርጫው ቀላል ነበረ :: ልቦቻቸው በክርስቶስ ጥላቻ ስለ ታውሩ በርባንን ፍታልን ክርስቶስን ስቀልልን እያሉ ይጮሁ ነበር ::

ኣሁን በዚህ ዘመንስ .....???

ለስሙ በ 40 እና በ 80 ቀናችን ልጅነትን አግኝተን በክርስቶስ ስም የተጠራነውን እኛ በዚህ ዘምን ማንን እየመረጥን ነው ...? ማንን ሰቅለን ማንን እየፈታን ነው ..? ምናልባት ይህንን ጥያቄ ለብዝዎቻችን ግርምት ሊፈጥርልን ይችላል :: ግን በዚህም ዘምን ሆነን ከሁለቱ አንዱን እያደረግን ነው :: እንዴት ..? መቸም ክብር ይግባው እና ጌታችን በፈቃዱ ወደዚች ምድር መጥቶ ተሰቅሎ ሞቶ ተነስቶ ካዳነን ፳፻ ዓመት ኣልፎታል ግን አሁንም በየቀኑ ይህንን ታሪክ እየደገምነው እንውላለን :: እስቲ ስንቶቻችን ነን ቤተክርስቲያን ከማደር በየጭፈራ ቤቱ ማደርን እምንመርጠው ...? አረ ስንቶቻችን ነን ቅዳሴውን ከማድመጥ ዘፈን ማድመጥ እሚቀናን ...? እረ ስንቶቻችን ነን ስጋወደሙ ከመብላት እና ከመጠታት በጾም ወራት ሳይቀር የበሬና የፍየል ስጋን አማርጠን በልተን ዊስኪ መጠታትን እምናጣጥመው ...? እና ይሄንን ስናደርግ በርባንን መረጥን ማለት ኣደል ? እስቲ ሂወታችንን ቆም ብለን እንየው የክርስትናው መንገድ እየለቀቅን ነው ወይስ ኣሁንም በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን ብለን ራሳችንን እንመርምር እማይዋሸው ህሊናችን ጋራ መልሱን እናገኘዋለን :: በዚሁ የጾም ወቅት ከእድፍ ተግባራችንን በምቆጠብ ወደ እርሱ እምንቀርብበትን ወራት ያፋጥንልን ::

አሜን ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር !!!

መነሻ ሃሳብ :- ዲ/ን ሄኖክ ጛይሌ /ሕማማት መፅሐፍ/
ፅሑፍ :- © ተመስገን ሓረጎት ህላዌ
፳፰/፮/፳፻፲፪
መዝሙር ዘመጻጒዕ

አምላኩሰ ለአዳም ለዕረፍት ሰንበተ ሠርዐ ወይቤልዎ አይሁድ በዓይ ሥልጣን ትገብር ዘንተ ወይቤሎሙ ኢየሱስ አነኒ እገብር አንትሙኒ እመኑ ለግብርየ ወይቤሎሙ አነ ውእቱ እግዚአ ለሰንበት እግዚኣ ለሰንበት ወልድ ዋሕድ ወይቤሎሙ ብውሕ ሊተ እኅድግ ኃጢአተ በዲበ ምድር እስብክ ግእዛነ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን አቡየ ፈነወኒ

ትርጒም፦

የአዳም ፈጣሪ ለዕረፍት ሰንበትን ሠራ አይሁድ ይህንን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ ብለው ጠየቁት ኢየሱስም እኔ እሠራለሁ እናንተም ሥራዬን እመኑ የሰንበት ጌታ እኔ ነኝ አላቸው የሰንበት ጌታዋ ወልድ ዋህድ ነው አላቸው በምድር ላይ ኃጢአትን እተው/ይቅር እል ዘንድ ሥልጣን አለኝ ነጻነትን እሰብክ ዘንድ የዕውራንን ዓይን አበራ ዘንድ አባቴ ላከኝ አላቸው

የዕለቱ ምስባክ፦ 

እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኲሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ መዝ ፵፥፫

ትርጉም፦

እግዚአብሔር በሕማሙ አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውንም ከደዌው የተነሣ ይለውጥለታል
እኔስ አቤቱ ይቅር በለኝ እላለሁ

ምሥጢር፦

ታሞ ሳለ በመኝታው ይረዳዋል ማለት ሕመሙን እንዲችለው ያደርጋዋል አንድም አስታማሚ ይሰጠዋል። እሳት በገል ውኃ በቅል ይዞ የሚረዳው ሰው ይሰጠዋል።

ከደዌው አድኖ ጤናውን ይመልስለታል ማለት የሠላሳ ስምንት ዓመቱን ሕመምተኛ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ይለዋል

እኔ ግን ለይቅርታ ለፈውስ የሚያበቃ ሥራ የለኝምና ይቅር በለኝ እላለሁ

መልእክት፦

እደ ምሕረቱን እንዲዘረጋልን "አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ - እኔ ግን መልካም ሥራ የለኝምና አቤቱ ይቅር በለኝ እላለሁ" እንበል ከልባችን ሆነን። መሠረታዊው ችግራችን አፋችን የሚናገረውን ልባችን የሚያምንበት አለመሆኑ ነውና ለልባችን ልቡናን እንዲሰጥልን ተግተን እንጸለይ። በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ሠራዒው ካህን "ሀበነ እግዚኦ ልበ ወልቡና - አቤቱ ልብና ልቡናን ስጠን" ብሎ እንደሚጸልየው ማለት ነው። 

የዕለቱ ወንጌል፦

ዮሐ ፭፥፩ - ፳፭

ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ
ኮሮና ፣ ጸሎትና ንፅህናን መጠበቅ

በዚህ ጊዜ አብዛኞቹ የዓለምችን ከተሞች በዚህ ወረርሽኝ ተተቅትዋል :: በሃገራችን ከገባም አንድ ሳምንት ሊሆነው ነው :: ብዙ የሃይማኖታዊ ፅሑፎችን በማህበራዊ ሚዲያ በመለጠፍ እሚታወቁ ሰዎች ይህ በሽታ የመጣው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለማክበራችን ነው ስለዚህ ይህን መከላከል እምንችለው በጸሎት ብቻ ነው እሙሉ ፅሑፎች እየተበራከቱ መጥተዋል :: ከእነርሱ ባላውቅም ይህ ሓሳብ ትክክልም ስህተትም ነው ከሚሉት ወገኖች አንዱ እኔ ነኝ::
ትክክል ናቸው ብየ እማምነው ይህ ሕመም የግዚአብሔር ቁጣ ነው እኛ ሰዋች ከቀን ወደ ቀን ተግራችን እየከፋ ከሰው ተግባር ወደ ሰይጣናዊ ተግባር እየተቀየረ ስራዎቻችን እግዚአብሔርን ከሚያስደስቱ ሰይጣንን ማስደሰት ከጀመሩ ሰንበትበት ስላሉ እግዚአብሔር ልጆቹን እንዳንጠፉበት የአባትነቱን ሊኮረክመን ስለፈለገ ነው ባይ ነኝ::
እማልስማማበት ግን መከላክያ መንገድ ጸሎት ብቻ ነው በሚለው ሓሳብ ላይ ነው :: ትክክል ነው ከዚህ መቅዘፍት እና ቸነፈር እምንድነው በጸሎና በምህላ ነው ግን መከላክያ መንገዶቹን ሳንጠቀም እራሳችንን ለበሽታው ተጋላጭ በማድረግ ከበሽታው ነፃ እሆናለሁ ማለት ግን አግባብ አይመስለኝም:: ምክንያቱም አንደኛ በጸሎተ ብቻ ለመዳን ፍፁም የሆነ እምነት ያስፈልጋል እናም እኛ በዚያ ደረጃ እሚደርስ እምነት የለንም:: ሁለትኛ ግን ክርስቶስ ራሱ ያስተማረን ነገር አለ ::
የሉቃስ ወንጌል 4
9-11፤ ወደ ኢየሩሳሌም ደግሞ ወሰደው፤ በመቅደስም ጫፍ ላይ አቁሞ፡— ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፥ እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል፡ ተብሎ ተጽፎአልና፡ የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ከዚህ ወደ ታች ራስህን ወርውር፡ አለው።
12፤ ኢየሱስም መልሶ፡— ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎአል፡ አለው።
ስለዚህ የግል ንፅህና መጥበቅ መከላክያ ምንገድ እያለ ንፅህናየን አልጠብቅም በጸሎተ ብቻ እከላከለዋለሁ ማለት እግዚአብሔር አምላክን መፈታተን እንዳይሆን እንጠንቀቅ::

ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር !

© ተመስገን ሓረጎት ህላዌ
፲፩/፯/፳፻፲፪