+ ኢየሱስ እናቱን ተቆጥቷት ይሆንን? +
የቃና ሰርግ ቤት ታሪክ ለጊዜው እናቆየውና አንድ ልጅ በአደባባይ በሰዎች ፊት እናቱን በምንም ምክንያት ቢቆጣ እንኳን ከሃይማኖት አንጻር ከሥነ ምግባርም አንጻር የሚደገፍ ሥራ አይደለም፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችን ‹እናቱን በቁጣ ተናገራት› የሚለው አስተሳሰብም እንዲሁ ብዙ የሚያመጣው ጣጣ አለ፡፡ ‹‹እናትና አባትህን አክብር›› ‹‹እናቱን የሰደበ ይሙት›› የሚለውን ሕግ የሠራ አምላክ ‹እኔን ምሰሉ› እያለ ለሰው ልጆች አርኣያ ሊሆን በመጣበት በዚህ ዓለም ራሱ እናቱን በአደባባይ በሰው ፊት ያቃልላታል ብሎ ማሰብ እጅግ ከባድና ለብዙ ሰዎች የኃጢአትን በር ወለል አድርጎ ከፍቶ መረን የሚለቅ ነው፡፡ (ዘጸ. ፳፥፲፪ ፣ ፳፩፥ )
እመቤታችንን የጎዱ መስሏቸው ‹ጌታ እናቱን ተቆጣ› ብለው የሚሰብኩ ሰዎችም ሳያውቁት እየተናገሩ ያሉት በእመቤታችን ላይ ሳይሆን በራሱ በጌታችን ላይ ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው?›› ብሎ የተናገረ ንጹሐ ባሕርይ ነው፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፮) ‹የሚጤስን የጧፍ ክር የማያጠፋ ፣ የተቀጠቀጠ ሸንበቆን የማይሰብር› በአነጋገሩ ጭምት ነው፡፡ ስንክሳሩም ‹‹ወንድሜ ምእመን ሆይ ጌታችን ለንጽሕት እናቱ ለድንግል ማርያም ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ጊዜዬ ገና አልደረሰም በማለቱ የክብርት እናቱን ቃል እንዳቃለለ አታስብ›› ይላል፡፡ (ስንክ. ጥር ፲፪ ቁ. ፵)
በማስከተልም ‹‹ጌታችን የሰማያዊውና የመለኮታዊ አባቱን ክብር እንደጠበቀ ይታወቅ ዘንድ እንዲሁ ከእርስዋ ፍጹም ሥጋንና ፍጽምት ነፍስን ነሥቶ ከመለኮቱ ጋር ያዋሐደውን የእናቱን ክብር ጠበቀ፡፡ በወንጌል ይታዘዛትና ይላላካት ነበር ተብሎ እንደተጻፈ›› ይላል፡፡ (ስንክ.ጥር ፲፪ ቁ. ፵፪)
በእርግጥም ጌታችን የባሕርይ አባቱን አብን ክብር እንደጠበቀ በራሱ አንደበት ‹‹አባቴን አከብራለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፱) ለእመቤታችንና ለአሳዳጊው ዮሴፍም እንዲሁ ‹‹ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ሉቃ. ፪፥፶፩) እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ስለ ወይኑ የነገረችውም የልጅዋን መታዘዝ በልብዋ ትጠብቀው ስለነበር እና እንደሚታዘዛት ታስብ ስለነበር ነው፡፡
እስቲ ነገሩን ሌሎች ከሚያዩበት ማዕዘን ለመመልከት እንሞክር፡፡ እውነት ግን ጌታችን እናቱን ሊቆጣ የሚችልበት ምን ምክንያት ነበረው? ከላይ እንደተመለከትነው የለመነችው ስለ ራስዋ ጥቅም አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ልመናዋ ከሚያስፈልግ ነገር ውጪ ይደረግ የተባለ አላስፈላጊ የቅንጦት ልመና አይደለም፡፡ በሰርግ ቤት ሙሽሮችን ለዕድሜ ልክ ውርደት ሊዳርግ የሚችል የወይን ጠጅ እጥረት በተከሰተበት ሰዓት ‹ወይን እኮ የላቸውም› ብሎ ማመልከት እንኳን በሩኅሩኁ አምላክ ፊት ይቅርና በእኛ በጨካኞቹ የሰው ልጆች ፊት እንኳን ሊያስቆጣ የሚችል ነገር አይደለም፡፡
የለመነችው እንደ አይሁድ ምልክት ለማየት ጓጉታ አይደለም፡፡ እንደ ፈሪሳዊያንና ሰዱቃውያን ‹አይተን እንድናምንህ ምን ምልክት ትሠራለህ?› ‹ከሰማይ ምልክት ልናይ እንወዳለን› የሚል የፈተና ጥያቄ አልጠየቀችም፡፡ (ማቴ. ፲፮፥፩ ፤ዮሐ. ፮፥፳) ተአምር የማየት ምኞት አድሮበት እንደጠየቀው እንደ ሄሮድስም በአጋጣሚው ልጠቀምና ተአምር ልይ ብላም አይደለም፡፡ (ሉቃ. ፳፫፥፰) ደግሞስ ያለ ወንድ ዘር በማኅጸንዋ አድሮ በታተመ ድንግልና ሲወለድ ያየች እናት ሌላ ምን ተአምር ሊያስደንቃት ይችላል?
የሰርጋቸው ቀን የኀዘናቸው ቀን ሊሆን ስለተቃረበ ሙሽሮች ተጨንቃ መለመንዋ እንዴት የሚያስቆጣ ሊሆን ይችላል? ያለጊዜው ስለለመነችውና ስለቸኮለች ተቆጣት እንዳንል ልመናዋን ትንሽ ብታዘገየው ኖሮ ነገሩ ይፋ እየሆነ ፣ ሙሽሮቹ መዋረዳቸው ነው፡፡ ስለዚህ የደረሰችው በሰዓቱ ነው፡፡
የጌታችን አሠራር እንዲህ አልነበረም፡፡ የቅዱስ ጴጥሮስ አማት በንዳድ በታመመች ጊዜ እንዲፈውሳት ሲለምኑት እሺ ብሎ ንዳዱን ገሥፆ አላቀቃት፡፡ (ሉቃ.፬፥፴፱) የአንድ መቶ አለቃ ልጅ በታመመ ጊዜ የአይሁድ ሽማግሌዎች ሊያማልዱ በመቶ አለቃው ተልከው መጡ፡፡ ጌታችን ከይሁዳ ነገድ መሆኑን በማሰብም ‹‹ይህን ልታደርግለት ይገባዋል፤ ሕዝባችንን ይወዳልና ምኵራብም ራሱ ሠርቶልናል ብለው አጽንተው ለመኑት። ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ።›› የመቶ አለቃውንም ልጅ በመጨረሻ ፈወሰው፡፡ (ሉቃ. ፯፥፪-፮) እነዚህ ሰዎች ተአምር እንዲያደርግ ሲጠይቁት እሺ ያለ ጌታ እናቱ ስትለምነው ይቆጣል ብለን እንዴት እንቀበል? የአይሁድን ሽማግሌዎች እንኳን ያልተቆጣውን ጌታ በምን አንደበታችን እናቱን ተቆጣ ልንለው ይቻለናል?
ከሁሉ በላይ ቅዱስ ዳዊት ‹‹ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን›› እንዳለው በረከሰ አንደበታችን ፣ በሚወላውል ልባችን ፣ በሚባክን ሃሳባችን ወደ እርሱ የምንጸልየውን የእኛን የኃጢአተኞቹን ጸሎት ለምን ጸለያችሁ ብሎ ያልከለከለ አምላክ ንጽሕት እናቱ በፍጹም ትሕትና ለለመነችው ልመና የቁጣ ምላሽ ሠጠ ማለት እንዴት እንደፍራለን? ዳዊት ‹‹በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ›› ብሏል፡፡ እርሱ በልቡ በደል ስለሌለ ጌታ ከሰማው በሃሳብዋ ድንግል የሆነች እናቱን እንዴት አልሰማትም እንላለን? (መዝ. ፷፮፥፲፱-፳)
እመቤታችን የጠየቀችው ይህን ያህል የማይጠየቅ ነገር ነው እንዴ? የመንግሥትህን እኩሌታ ፣ የሥልጣንህን ፈንታ ሥጠኝ አላለችውም፡፡ የጠየቀችው ስለ ድሆቹ ሙሽሮች ነው፡፡ እኛ በረባ ባልረባው ስንዘበዝበው የምንውለውና የምናድረው ታጋሽ አምላክ ለእናቱ ለእኛ የሠጠውን ነገር ይነሣል ማለት ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ ‹አብን አሳየንና ይበቃናል› ፤ ‹እሳት ከሰማይ ወርዶ ሕዝቡን ያጥፋቸው› ፤ ‹በግራ ቀኝህ አስቀምጠን› የሚሉ ደቀ መዛሙርትን ታግሶ ለሦስት ዓመት ከሦስት ወራት ያስከተለ ጌታ ቅድስት እናቱ ተገቢ ልመና በተገቢ ሰዓት ስትለምነው ሊቆጣ አይችልም፡፡
እንደ ወንጌሉ ብቻ ከሔድን ደግሞ እመቤታችን ከዚህ በፊትና በኋላ ምንም ነገር ስትለምነው አልተጻፈም፡፡ በወንጌል ለተጻፈው ለዚህ ብቸኛ ልመናዋም መልሱ ቁጣ ነው ብለን አምነን መቀመጥ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ፈጽሞ የሚዋጥልን ሃሳብ አይደለም፡፡ በልጅነትዋ ወልዳው ለተሰደደችው ፣ በነፍስዋ የኀዘን ሰይፍ ላለፈባት እናቱ አንዴ ብትለምነው ተቆጣ ብለን እንዴት እንናገራለን?
ጌታችን በዚህ ሰርግ ቤት እንኳንስ እንዲህ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የሚተረጉመው ‹ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ› የሚል የአክብሮት ንግግር ተናግሮ ቀርቶ ፤ ለእናቱ የተናገረው በቀጥታና በግልፅ የቁጣ ንግግር ቢሆን ኖሮ እንኳን ጾመን ጸልየን ፣ ወድቀን ተነሥተን ምሥጢራዊ ትርጉሙን እንፈልጋለን እንጂ ሰማይና ምድር ቢነዋወጥ ‹ጌታ እናቱን ተቆጣ› ብለን አናምንም!!!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ቃና ዘገሊላ ገጽ 81

" ሰው ብቻ አትሁኑ"
✍መጋቤ ሐዲስ እሸቱ
" ሰው ብቻ አትሁኑ...ሰው ብቻ ማለት ምንድን ማለት ነው? ብዬ ሳስብ፤ የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ በሚለብሰው ልብስ፣ በሚነዳው መኪና የኑሮን ስኬት የሚለካ ማለት ነው? እስከ ሞት የሚኖር ማለት ነው? እንደ እንስሳ። "...ታላቁ ሊቅ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል "ሰው እግዚአብሔር ሲለየው" ይላል። ሰው እግዚአብሔር ሲለየው፤ ጠባዩ እንደ አራዊት፤ አመጋገቡ እንደ እንስሳ፣ ሆኖ መልኩ ብቻ የእግዚአብሔር ሆኖ ይቀራል። በጣም ቀለል ባለ አገላለጽ ሲምካርዱ የወጣ ሞባይል(mobile ) ማለት ነው ። ጥሪ የማይቀበል፤ ለጉትቻ ማንጠልጠያ ብቻ የተሰራም ጆሮ አለ።"...እኔ በዕውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ ዐይናማዎቹ ሲያወሩም ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት የሰዉ አስተሳሰብ ነው።... የሰዉ አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ ይፈርሳል። ጃፓንና ቻይና ሀገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን አልምተው ነው። አስተሳሰቡ ያልለማ ሕዝብ የለማውን ያወድማል።"
"ቤታችሁ ገብታችሁ እንድታጤኑት ነው። እነዛ. (ምንትስ) የምንላቸው ክርስቲያኖችን አርደዋል... ምዕራባውያኑ ደግሞ ክርስትናን እራሱን አርደውታል።....ወንድ ለወንድ፣ ሴት ለሴት፣ በቤተክርስቲያናቸው እያጋቡ፤ ክርስትናን አጋድመው ያረዱ ምዕራባውያን ናቸው። (ይህን ሁሉ ያመጣውም) የምዕራባውያን ልክ ያጣ ነጻነትና ገደብ ያለፈ ዝርክርክነት ነው።" "እንደምታዩት እኔ ዐይነ ስውር ነኝ። ቀላል አይደለም.... እንክዋን ዘውትር ዓይን አጥቶ አንድ ቀን መብራት ሲሄድ ስንት እንደምታማርሩ ታውቅታላችሁ። አንድ ቀን ግን አልቅሼ አላውቅም። ከሞት ወዲያ መብራት አለ። ከመቃብር በላይመብራት አለ። ... ወደ መቃብር ሲወርድ ማንም ዓይነ ስውር ነው። ማንም ዐይኑ እያየ የተቀበረ የለም። ተስፋችን ግን ምንድን ነው? ከሞት ወዲያ ሕይወት አለ። ከሞት ወዲያ ብርሃን አለ።"
"...አንድ አንድ ጊዜ እመኛለሁ። የማይረባ ነገር ስናይ (ዓይናችንን) የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር... መልካም ነገር እስክናይ ድረስ ለጊዜው የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር። "አሁን እንደው ጆሮ በካርድ የሚሰራ ቢሆን ሐሜት እንሰማ ነበር?(ከፍተኛ ሳቅ)... የምንፈልገውን (ብቻ) አውርተን ስዊች ኦፍ እናደርገው ነበር። ስንት ዞማ ጸጉር ይዞ አስተሳሰቡ የከረደደ አለ። "ጀርመን ሀገር ሄጄ ሲነግሩኝ፤ ባለ አምስት ኮከብ የውሻ ሆቴል አለ ተባለ። እኛ ሀገር አምስት ኮከብ ሆቴል ገብተው የበሉ ትንሽ ዝና (ሀብት) እና ትንሽ ሥልጣን ያላቸው ናቸው። ማን ይገባል ከነሱ ውጪ። ግን ሰዋች ነን። የጀርመን ውሻ ዛሬም ውሻ ነው ለዘላለምም ውሻ ነው። እኛ ግን ሰው ነን። እንደ ሰው አስቡ (ምዕመናን) በማርያም።" "...የንጉሠ ነገሥቱ የክርስቶስ አልጋ ወራሾች ነን... የደስታችሁ ልኬት የደስታችሁ ሚዛን ምግብና መጠጥ አይሁን፤ መኪናና ቤት ዝናንም አታርጉ። እኛ መለኪያችን
ጽድቅ ነው። መለኪያችን መንግሥተ ሰማያት ነው። ያ የምንገባበት ቤት ደግም የተዋበ፣ የደመቀ፣ መብራት ውሀ የማይሄድበት፤ 24 ሰዓት ክርስቶስ የሚያበራበት፤ 24 ሰዓት የሕይወት ውሀ የሚጠጣበት፤ ሀብታም፤ ደሀ፣ ተራ ሰው የማይባልበት፣ እገሌ ግባ እገሌ ውጣ የማይባልበት ቦታ ነው።
ሁላችንንም የመንግስቱ ወራሽ ያድርገን።

ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ ክርስቶስ የሰጠህን ስጦታ ላልተፈረገ ግብር አታውለው፡፡ እጅን የሰጠህ እንድትሰርቅበት ሳይሆን ትእዛዛቱን እንድትፈጽምበት፣ በጎ ምግባርን እንድትሠራበት፣ ለጸሎት እንድትነሣበት፣ የወደቁትን እንድታነሣበት ነው፡፡ ጆሮን የሰጠህ ተርታ ወሬን እንድትሰማበት ሳይሆን ቃሉን እንድታደምጥበት ነው፡፡ አንደበትን የሰጠህ እንድትሰድብበትና እንድትረግምበት ሳይሆን እንድትዘምርበት፣ እንድታመሰግንበት፣ እንድትመክርበት ነው፡፡ እግርን የሰጠህ ወደ ክፋት ሳይሆን ወደ በጎ ስፍራ እንድትፋጠንበት ነው፡፡ ሆድን የሰጠህ ለመብል ሳይሆን ጥበብን እንድትማርበት ነው፡፡ ፈቲውን የሰጠህ እንድታመነዝርበትና እንድትዳራበት ሳይሆን ልጆችን ትወልድበት ዘንድ ነው፡፡ ልቡናን የሰጠህ ሰዎችን እንድትወቅስበት ሳይሆን እውነትን ታውቅበት ዘንድ ነው፡፡ ገንዘብንና ጉልበትን የሚሰጠን ሰማያዊ ቤታችንን እንድንሠራበት ነው፡፡ ...እንኪያስ የክርስቶስን ስጦታ በአግባቡ ተጠቀምበት፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
++ አበው ስለ እመቤታችን ዕረፍት እንዲህ አሉ ++
‹ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
‹‹ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ›› ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Homily on the Dormition)
‹‹የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው›› ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ (aka Doctor of Dormition)
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አስተ ር እዮ ማርያም

"አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ"
ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወጣት የንስሀ አባቱን ለማግኘት ተንስቶ ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳል። ፀሎቱን አድርሶ ግቢ ውስጥ ቁጭ እንዳለ አባ ይመጡና በመስቀል ባርከው ደባብሰው ወደ በአታቸው ይዘውት ይገባሉ። ታድያ ልክ እንደ ገባ የክርስቶስን ስነ ስቅለት የእሾሁን አክሊል ያይና በሀሳብ ወደ ቀራንዮ ይሄዳል። አባ ምነው ልጄ እኔን እዚህ ትተህ አንተ ወደ ቀራንዮ ሄድክ ሲሉት ከሀሳቡ ባህር ወጥቶ ቁጭ አለ።
አባ አየህ ልጄ ምን ሆነ መሰለህ ብለው ጨዋታ ጀመሩለት። "በአንድ ሀገር ትልቅ የባቡር መንገድ ነበር ታድያ የባቡሩ መንገድ ታቹ ባህር ነው በጣም ትላልቅ አዞዎች አሉበት። አንድ ቀን ታድያ ይህ መንገድ ኃይለኛ ዝናብ በመጣሉ ምክንያት ይፈርሳል። አንድ ህፃን ልጅ ይህን ሁኔታ አይቶ ኖሯል ባቡሩ እዛ ቦታ ሳይደርስ ለማስቆም ወሰነና የአደጋ ምልክቶችን ፅፎ በተለያየ ርቀት 2 ቦታዎች ላይ አስቀመጠ። ከዚያም 3ኛው ላይ ባንዲራ ይዞ እራሱ ቆመ ባቡሩም መጣ ልክ የመጀመሪያውን የአደጋ ምልክት ሲያይ ይህ የዱርዬዋች ስራ ነው ብሎ ተበሳጭቶ አለፈ። ሁለተኛውንም እንዲሁ አለፈ። በሶስተኛው ህፃኑ ጋር ደረሰ ጥሩንባውን እያጮኸ ዘወር በል አለው ልጁ ግን በጭራሽ ዘወር ሳይል ባቡሩ እዛው ፈጨው የባቡሩ አሽከርካሪ በጣም ደነገጠ ተሳፋሪዎችም ወረዱ ልጁን ሲያዩት የለም ደቋል። ነገር ግን በእጁ የነበረው ወረቀትና ባንዲራ ወድቆ አገኙት አንስተው ሲያነቡት በዝናቡ ምክንያት ድልድዩ መፍረሱን ነበር የሚያሳየው። እውነትም ጠጋ ብለው ሲያዩ ድልድዩ ፈርሶ አዞዎቹ ብቅ ብቅ ብለው መልአከ ሞት የሚጥልላቻውን ነፍስ የሚጠብቁ ነበር የሚመስሉት። ከዛ ሁሉም በጣም አዘኑ አለቀሱ ለእነርሱ መትረፍ ያ ህፃን ልጅ የከፈለውን መስዋዕትነት ተገነዘቡ አንዱ ስለ ሁላቸው ሞቶ እነርሱን አተረፈ። ይህ ሁሉ ስለ ሰዎች ፍቅር ነው።"
አየህ ልጄ ክርስቶስም ለኛ እንዲህ ነው አሉት ሳያውቁ ሁለቱም በጣም አልቅሰው ነበር በልጁ ታሪክ። "አባቴ እኔ'ኮ ከንቱ ሰው ነኝ እግዚአብሔር እኔን ይቅር ይለኛል?" አላቸው "ልጄ እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነው። ግን መጀመሪያ አንተ ቀዶ ጥገና ያልስፈልግሃል" አሉት። "ምን አይነት ቀዶ ጥገና አባቴ?" "ይሄውልህ ልጄ የእስከ አሁኑን ልብህን ልናክመው ይገባል ዳግመኛ ወደ ቀደሞው መጥፎና ኃጢአት የበዛበት ህይወት እንዳትመለስ። ከዚያ ንስሀ የሚባለውን የህይወት መድኃኒት ትወስድና ትድናለህ" አሉት፡፡ ወጣቱም ሁሉን ተናዞ ንስሀ ገብቶ ተፀፅቶ ትላንትን ዳግም ላያየት ከእውነት ጋር ታርቆ ጤናማ ህይውቱን መኖር ጀመረ።
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር

የካቲት 2 - የበረሃው ኮከብ የአባ ጳውሊ ዕረፍት
በዚህች ቀን በግብጽ በርሃ ታላቅ አምድ ወደቀ፤ ይህም የባህታውያን ሁሉ አለቃቸው የሆነ አባ ጳውሊ ነው። ስርዓተ ብሕትውና በጳውሊ ስርዓተ ምንኩስና በእንጦኒ ተጀምሯል ይላል፤ ጳውሊ አባቱ ባለጸጋ ነበር ሲሞት ለታላቅ ወንድሙ በጴጥሮስ እጅ አድርጎ ኃላ አካለ መጠን ሲያደርስ ከፍለህ ስጠው ብሎት ተናዞ አረፈ፤ አባ ጳውሊ አካለ መጠን ሲደርስ “ደረስሁ ልጅ ፈላሁ ጠጅ” የአባቴን ገንዘብ ከፍለህ ስጠኝ አለው አይሆንም አልሰጥህም አለው ምነው ቢለው ልጅ ነህ ታጠፋዋለህ ብዬ ነው ይለዋል አላጠፋውም ስጠኝ ይለዋል ግድማ ካልኸኝ ብሎ ብዙውን አስቀርቶ ጥቂቱን፤ መልካሙን አስቀርቶ ተራ ተራውን ሰጠው አባ ጳውሊ በዚህ ተበሳጭቶ ዳኛ ጋር ሄደ በመንገድ ላይ አንድ ባለጸጋ ሞቶ ሊቀብሩት ሲወስዱት አየ አባቴ ባለጸጋ ነበር ሞተ ይሄም ባለጸጋ ነበር ሞተ እኔስ ነገ እሞት የለምን ብሎ ወደ ወንድሙ ተመልሶ ወንድሜ ገንዘቡ ላንተ ይሁን ትቼልሃለው ብሎ ከቤት ወጠ፤ መጀመሪያ ለ 3 ቀን ከመቃብር ቤት ገብቶ ጸለየ በ3ኛው ቀን ከሰማይ ግማሽ ህብስት ወረደለት፤ ገረመው፤ ፈጽሞ ሳይለዩ እንዲህ ከሆነማ ፈጽሞ ቢለዩማ እንደምን ያለ ተአምር በተደረገ ብሎ አናብስት አናምርት አካይስት አቃርብት ካሉበት ነቃዐ ማይ ልምላሜ ዕፅ ከሌለበት ድሩክ ለተአቅቦ ይለዋል ዘር ተክል ከማይገኝበት ከጽኑ በርሃ ገባ፤ የሰው ፊት ሳያይ ለ 80 ዓመት በተጋድሎ ኖሯል። ምግቡን ግማሽ ህብስት በየቀኑ የሚያመጣለት ቁራ ነበር።
የእረፍቱ ቀኑ ሲደርስ ከአባ እንጦንስ ጋር በእግዚያብሔር ፈቃድ ተገናኝተው ብዙ ነገር ተጨዋወቱ በተለይም በኃለኛው ዘመን ስለሚነሱት መነኮሳትና፤ ግብጽ በሙስሊሞች እንደምትወረር ብዙ ሚስጢር አወሩ ብዙ ትንቢትም ተናገሩ፤ ከዚህ በኃላ አባ ጳውሊ አስኬማ መልአክ አምጣልኝ ብሎ ይልከዋል፤ አባ እንጦስ ወደ ገዳሙ ሄደ የ2 ቀን ጎዳና ነው ሲመለስ በርሃው ላይ ሰማያውያን መልአክ ሰፍረውበት ሲዘምሩ ሲያመሰግኑ አየ፤ ልብን የሚመስጥ የእጣን መዓዛም አሸተተ፤ ምንድር ነው ? ብሎ አንዱን መልአክ ይጠይቀዋል አባ ጳውሊ ሞቶ ነፍሱን እያሳረግን ነው ይለዋል ይሄን አስኬማ አምጣልኝ ብሎኝ ነበር ምን ላድርገው? ይለዋል፤ ጸሎት አድርሰህ አድርግለት፤ ደግሞም መቃብሩን የሚቆፍሩ አንበሶች ይመጣሉ ቦታውን ለክተህ ስጣቸው አለው፤ ወደ ገዳሙ ሲገባ እጁን መስቀልያ እንደዘረጋ ሞቶ አገኘው የሚጸልይ እንጂ የሞተ አይመስልም ነበር አስኬማውን አድርጎለት ሲያበቃ ከራስጌው ቆሞ ኤልያስ ልበልህ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ልበልህ እያለ አለቀሰለት፤ ሁለት አንበሶች መቃብሩን ቆፈሩለት ገንዞ ቀበረው። 80 ዘመን ሙሉ ለብሶት የኖረው የሰሌን ልብስ ነበረችው ወስዶ ለሊቀ ጳጳሱ ለአባ አትናቴዎስ ሰጠው፤ በዚህች ልብስ አባ አትናቴዎስ ብዙ ተአምራትን ሰረቶበታል ይልቁንም ሙት አስነስቶበታል።

“ከነነዌ ሰዎች በላይ የከፉ ማን ነበር? ከነነዌ ሰዎች በላይ ግራውንና ቀኙን የማያውቅ ማን ነበር? ምንም እንኳን ድንጋይ ጠርበው ዕንጨት ቆርጠው የሚያመልኩ አሕዛብ ቢኾኑም፣ ምንም እንኳን ስለ ሀልወተ እግዚአብሔር ምንም ባያውቁም፣
ምንም እንኳን ስለ ፈሪሐ እግዚአብሔር ከማንም ነቢይ ባይማሩም ዮናስ መጥቶ አንዲት አረፍተ ነገር ስለ ነገራቸው ብቻ በሦስት ቀን ውስጥ ኹሉንም ተዉት፡፡ ዘማዊው ንጹሕ ኾነ፡፡ ስግብግቡ ለጋሽ ኾነ፡፡ ቁጡውና ተሳዳቢው መራቂ ኾነ፡፡ ሰነፉ ሰው ለጦም ለጸሎት ብርቱ ኾነ፡፡ ከክፋታቸውም አንዱን ወይም ኹለቱን ብቻ የተዉት አይደሉም፤ ኹሉንም ተዉት እንጂ፡፡ ምንም እንኳን የበደላቸው ጽዋ ሞልቶ መንበረ ጸባዖትን ለቁጣ የቀሰቀሰ የነበረ ቢኾንም ተመለሱ፡፡ ሲመለሱም እግዚአብሔር በቁጣ ሳይኾን በምሕረት ዓይን አያቸው፡፡ ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጸተ፡፡ ተወዳጆች ሆይ! የነነዌ ሰዎች ምንም አሕዛብ ቢኾኑም በሦስት ቀን ውስጥ ብቻ እንዲኽ ማራኪየኾነ ንስሐን ከገቡ፥ እጅግ ብዙ ዘመናትን ተምረን ያልተለወጥን እኛው ክርስቲያኖች እንደምን ይፈረድብን ይኾን?”
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
እንኳን ለጾመ ነነዌ በሰላም አደረሰን....ጾሙ ለሀገራችን ሰላምን የምንለምንበት ያድርግልን

ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት )
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡
‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ›› የሚልና ይህንን የመሳሰለ ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ሌላም ስም አለው ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ?
በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡
በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡
«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምስጢሩ አምላክ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት = ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3-13፡፡
ሳምንቱ ሙሴኒ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት» «ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ» ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚያጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ከአለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው ምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24-18፤ 1ኛ.ነገ.19-8፤ ማቴ. 4-1-4/፡፡

Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቅድሰት የዐቢይ ጾም ሑለተኛ
ቅድሰት የዐቢይ ጾም ሑለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው፡፡ ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡
‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ክቡር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡ መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ ቅዱስ፡ ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡ የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ቅዱስ›› የሚለው ቃል ለሰዎች፡ ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ፡ ለዕለታት ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡
እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም ይህንን ሲያስተምረን ነው፡፡ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡
ብርሃን ከጨለማ ጽድቅ ከኃጢአት ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለርኩሰት አልጠራንምና›› ያለንም ለዚህ ነው፡፡ /1ተሰ 4÷7/ እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበትን አላማ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች እንዲህ ገልጾላቸዋል ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ሰማያዊ ሥፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ብሎ ካመሰገነ በኋላ ‹‹ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳን ንጹሐንና ያለነውር በፍቅር ያደርገን ዘንድ ለእርሱ መረጠን›› ኤፌ 1፡3-4 አስቀድሞ ስለወደደንና ስላከበረንም ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ መልኩ የሚያስፈልገንን ሁሉ አዘጋጅቶ በእጆቹ ካበጀን በኋላ የሥነ ፍጥረት ዘውድ አድርጎ በገነት አኖረን ፡፡( ዘፍ 1፡26፤መዝ 8፡1)
የቀደመው አዳም አታድርግ የተባለውን በማድረጉ በንዝህላልነትና በስንፍና በከይሲ ዲያብሎስም ምክር ተዋረደ፡፡ በሞተ ሥጋ ላይም ሞተ ነፍስ ፤በርዕደተ መቃብር ላይ ርዕደተ ሲኦል ተፈረደበት፡ በባሕርዩ ሞት ገባበት፡ ተዳደፈ፡፡ ክፉ ፍትወታት የሚያጠቁትና የሚያሸንፉት የዲያብሎስና የኃጢአት ባርያ ሆነ፡፡ በማይለወጥ ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ግን ጠፍተን እንድንቀር አልተወንም፡፡ በሰጠን ተስፋ፡በተቆጠረው ሱባኤና በተነገረው ትንቢት መሰረት ዘመኑ ሲደርስ በተዋህዶ ሰው ሆነ፤ የተዋረደ ሥጋችንን አከበረ፡፡ በከበረ ደሙ ዋጀን፤ ከኃጢአታችን አጠበን፡፡ በእርሱ ምክንያት የእግዚአብሔር ልጆች ተባልን ፡፡ጌታችንና መድኃኒታችን ሰው የሆነውና ለመዳናችን የሆነውን ዋጋ ሁሉ የከፈለው ለእኛ ያለውን ፍቅርና ለኃጢአት ያለውን ጥላቻ ለእኛ ለማሳየት ነው፡፡ ‹‹ ነገር ግን የኃጢአትን ሥራ ይሽር ዘንድ ከእርሱ ጋር የተሰቀለውን አሮጌውን ሰውነታችን እንደሆነ ይህን እናውቃለን ›› የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ (ሮሜ 6፡6) እኛን ወደ ቀደመ ክብራችን ለመመለስ የተከፈለውም ዋጋ ታላቅ ከሆነው የጋብቻ ምስጢር ጋር በማያያዝ እንዲህ ገልፆታል ‹‹ ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርሰቲያን ራስዋ አዳኝዋም እንደሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና … ወንዶችም ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደዳት ራሱንም ስለእርስዋ ቤዛ አድርጎ እንደሰጠላት ሚስቶቻቸውን ይውደዱ፡፡ በውኃ ጥምቀትና በቃሉ ይቀድሳትና ያነጻት ዘንድ የነጻችና የተቀደሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላይዋ እድፈት ወይም ርኩሰት እንዳይገኝባት ቤተ ክስቲያኑን ለእርሱ የከበረች ያደርጋት ዘንድ…›› ኤፌ 5፡23-28 ስለዚህ ጌታችን በደሙ ኃጢአታችንን እንደ ቸርነቱ ይቅር ብሎናል፡፡ኤፌ 1፡7 ከእንግዲህ የራሳችን አይደለንም፡፡ በሰውነታችንም ኃጢአትና ዐመፃን ልናደርግበት አይገባም፡፡‹‹በዚህ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አታንግሷት፤ ለምኞቱ እሺ አትበሉት፡፡ ከሙታን ተለይቶ እንደተነሳ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጉ እንጂ ሰውነታችሁን ለኃጢአት የዐመፅ የጦር መሣሪያ አታድርጉት፤ ሰውነታችሁንም ለእግዚአብሔር የጽድቅ የጦር መሣሪያ አድርጉ››ተብለናል፡፡ (ሮሜ6፡12-13)
የተወደዳችሁ ምዕመናን እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚቀበለውን ህይወት ለመኖር አንፈልጋለን ፡፡ ለመሆኑ ይህ ሊሆን የሚችለው እንዴት ብንመላለስ ነው? መልሱን ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮቱ ከንቱ ነው፡፡ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ወላጆች የሌሉአቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በችግራቸው መጠየቅ በዓለምም ከሚገኝ ርኩሰት ሰውነትን መጠበቅ ነው፡፡›› በማለት ይመልስልናል( ያዕ 1፡26-27)፡፡ በክርስቶስ ደም የተቀደሰና የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰውነታችንን በዓለም ከሚገኝ ርኩሰት መጠበቅ የሰማያዊ ርስት ወራሾች ያደርገናል፡፡ በዓለም የሚገኘውን ርኩሰትም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የሥጋ ሥራ›› በማለት ገልጾታል፡፡ ‹‹እርሱም ዝሙት፣ርኩሰት፣መዳራት፣ጣዖት ማምለክ፣ሥራይ ማድረግ፣ መጣላት፣ ኩራት፣ የምንዝር ጌጥ፣ ቅናት፣ ቁጣ፣ ጥርጥር፣ ፉክክር፣ምቀኝነት፣ መጋደል፣ ስካር ፣ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው፡፡›› እነዚህን የሚያደርጉ ሰዎችም ከመንግስተ እግዚአብሔር በአፍአ ወይም በውጭ እንደሚቀሩ ሲያስረዳ ‹‹አስቀድሜ እንደነገርኋችሁ ይህን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን መንግስት አያይም›› ብሏል ( ገላ5፡19)።
በሕይወታችን ሁሉ የምግባርና የሃይማኖት ፍሬ አፍርተን መገኘት ለቅድስና የጠራንን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ነው፡፡ እነዚህንም ነገሮች ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የመንፈስ ፍሬዎች ›› ብሏቸዋል፡፡ እነርሱም ‹‹ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ምጽዋት፣ ቸርነት፣ እምነት፣ ገርነት ንጽሕና›› ናቸው፡፡ ገላ 5፡22 እግዚአብሔር ማደርያው ይሆን ዘንድ የመረጠውን ሰውነታችንን እርሱ የሚከብርበትን ሥራ ልናደርግበት ያስፈልጋል፡፡ ‹‹በሕይወት የሚኖሩትም ስለ እነርሱ ቤዛ ሆኖ ለሞተውና ለተነሣውም እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው የሚኖሩ እንዳይሆኑ እርሱ ስለሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ›› እንደተባለ በሕይወታችን ሁሉ ፋቃዱን በመመርመርና በመፈጸም በቅድስና ልንኖር ይገባናል፡፡ 2ቆሮ 5፡15 ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣በማኅበራዊ ኑሯችን፣ በምንበላው ምግብ፣ በምንለብሰው ልብስ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን በፊታችን ያለ

ውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል(ዕብ 12፡1)። ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Source: http://www.eotc-mkidusan.org/
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Source: http://www.eotc-mkidusan.org/
Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ምኩራብ (ሦስተኛው ሰንበት)
ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት «ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ» «ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ» እያለ ኢየሱስ በአይሁድ ምኩራብ ማስተማሩን እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሆኖ ስለተሰጠ ነው፡፡
የዚህም በዓል ታሪክ ዝርዝር ሁኔታው በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 21፡12-13 ተጠቅሷል፡፡ ቆላስ 2፡16-23 «እንግዲህ በመብል ወይ በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፣ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው፡፡ ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፣ ባላየውም ያለፈቃድ እየገባ፣ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ፤ እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፣ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም፣ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል፡፡ ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ እንደሰው ሥርዓትና ትምህር ት፡- አትያዝ አትቅመስ፣ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም ሁሉ እንደምትኖሩ ስለምን ትገዛላችሁ) እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና፡፡ ይህ እንደገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቈን ጥበብ ያለው ይመስላል፣ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም፡፡» ያዕ 2፡14-26 «ወንድሞቼ ሆይ፣ እምነት አለኝ የሚል፣ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፣ ከእናንተ አንዱም በደህና ሂዱ፣እሳት ሙቁ፣ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጧቸው ምን ይጠቅማቸዋል እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፣ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል፡፡ በእግዚአብሔር አንድ እንደሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል፡፡ አንተ ከንቱ ሰው፣ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፣ በሥራም እምነት እንደተፈጸመ ትመለከታለህን መጽሐፍም አብርሃምም እግዚአብሔር አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ፡፡
ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ፡፡ እንደዚሁም ጋለሞይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው፡፡» የሐዋ.ሥራ 1ዐ፡1-9 « በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነው ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ፡፡ ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል፡- ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው እርሱም ትኩር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ ጌታ ሆይ ምንድር ነው አለ፡፡ መልአኩም አለው፡- ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን ዐረገ፡፡ አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ፡፡ እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቁርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል፡፡ የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ ከሎሌዎቹ ሁለቱን፣ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፣ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ ኢዮጴም ላካቸው፡፡ እነርሱም በነገው ሲሄዱ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፣ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው ወጣ፡፡
ምስባክ-
መዝ 68፡9
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡
የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፡፡
ወንጌል፡-
ዮሐ 2፡12-25 «ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀመዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፣ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ፡፡ የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ ወደ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፣ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ፣ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፣ርግብ ሻጮችንም ይህን ከዚህ ውሰዱ፡፡ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደተጻፈ አሰቡ፡፡ ስለዚህ አይሁድ መልሰው ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክ ት ታሳየናለህ አሉት፡፡ ኢየሱስም መልሶ ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው ስለዚህ አይሁድ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፣ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን አሉት፡፡ እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተመቅደስ ይል ነበር፡፡ ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ፡፡ በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፣ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፣ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና፡፡»
(ማህበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ)

± ዕፅ ይገድላል ፤ ዕፅ ያድናል ±
‹ዕፅ ይቀትል ፤ ወዕፅ ያሐዩ› የሚል የታወቀ የሊቃውንት አባባል አለ ፤ ይህ ብሂል በተደጋጋሚ ከዕፅዋት ህክምና ጥበብ ጋር ተያይዞ ሲጠቀስ ይሰማል፡፡ በእርግጥም እግዚአብሔር በዕፅዋት ውስጥ እጅግ ብዙ መድኃኒትን በማስቀመጡ በተሠጠው ጥበብ ለመመርመር ለቻለና የተመራመሩትን ሊቃውንት አክብሮ መስማት ለቻለ በዕፅዋት ምክንያትነት ከብዙ ደዌ ሊፈወስ ይችላል፡፡
የዚህ ብሂል አሳብ ግን ከህክምና ርዕሰ ጉዳይ በላይ ዘልቆ የሚሔድ ጥልቅ ሃይማኖታዊ አሳብ ነው፡፡ በዕፀ በለስ ፍሬ ቀጥፎ በመብላቱ ምክንያት የሞት ሞትን የሞተው የሰው ልጅ በዕፀ መስቀል ላይ በተሰቀለው በሕይወት ፍሬ በክርስቶስ ምክንያት መዳኑን የሚያስረዳ እጅግ ገላጭ ንግግር ነው፡፡ ‹‹በገነት መካከል ባለው ዕፅ በሰው ልጅ ወገን ሁሉ ላይ ሞት እንደገባ እንዲሁ የሁሉ ጌታ በምድር መካከል በላይዋ በተሰቀለባት ዕፅ ሞት ይፈርሳል›› ዕፅ ይገድላል ዕፅ ያድናል ሲባልም በሕሊናችን ቀድመው ሊመጡ የሚገባቸው ሁለት ዕፅዋት የገደለን ዕፀ በለስና የዳንንበት ዕፀ መስቀል ናቸው፡፡
ሔዋን በሰይጣን ምክር ዕፀ በለስን ከባልዋ ጋር ከበላችና በዚያም ምክንያት ሞት በሰው ልጅ ላይ ከመጣ በኋላ በሰው ልጅ ሕሊና ውስጥ ሦስት ነገሮች ለዘመናት የውድቀት ምልክቶች ሆነው ቆይተዋል፡፡ ለአምስት ሺህ ዘመናት የሰው ልጅ ውድቀት ምልክቶች ሆነው የቆዩት ሴት ፣ እንጨትና ሞት ነበሩ፡፡ የሰው ልጅም ድንግሊቱ ሔዋን የዕባብን ቃል በመስማቷ እና ከእንጨቱ በመብላትዋ ምክንያት ሞት መጣብን እያለ ሴትንና ዕንጨትን ከሞት ጋር በአንድ ላይ እያነሣ ሲወቅስ ኖሮ ነበር፡፡
እግዚአብሔር በአዳም ላይ የፈረደውን ፍርድ በራሱ ላይ ለማድረግ ሰው ከሆነባት ቅጽበት ጀምሮ ግን ይህ ሁሉ ተለወጠ፡፡ ድንግሊቱን ሔዋንን ያነጋገራት ሴት የጥፋት ምልክት በመሆንዋ ፈንታ ንጽሕት ድንግል ማርያምን ቅዱስ ገብርኤል አነጋገራት፡፡ እርስዋም እንደ ሔዋን ‹አምላክ እሆናለሁ› ብላ በትዕቢት በማሰብ ፈንታ ‹እነሆኝ የጌታ ባሪያው› በማለትዋ ሴት የጥፋት ምልክት መሆንዋ ቀርቶ የመዳን ምልክት እንድትሆን አደረገች፡፡
ዕንጨት የሰው ልጅ ጥፋት ምልክት መሆኑ ደግሞ በዕለተ ዓርብ መድኃኔ ዓለም በእንጨት ላይ በመሰቀሉ ተወገደ ፡፡ የመጨረሻው የጥፋት ምልክት ሞትም በክርስቶስ ሞት ስለሞተና በጌታ ሞት ስለዳንን ሞት የጥፋት ሳይሆን የድኅነት ምልክት ሆነ ፤ እኛም ‹ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ፤ ሞትም ጥቅም ነው› ብለን መዘመር ጀመርን፡፡
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዕንጨት ተሰቅሎ የሰው ልጅን ነጻ እንደሚያወጣ አስቀድሞ በልዩ ልዩ ምሳሌዎች ውስጥ ገልጦ ነበር፡፡ ‹‹ሙሴ በምድረ በዳ ዕባብን እንደሰቀለ የሰው ልጅም እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል›› ብሎ ጌታችን ራሱ ከጠቀሰው ምሳሌ እንጀምር፡፡ (ዮሐ. ፫፥፲፬)
እስራኤላውያን እግዚአብሔር ከሰማይ መናን እያወረደ ከዓለት ውኃን እያፈለቀ ፣ ቀኑን በደመና ሌሊቱን በብርሃን እየመራቸው በነበረበት ወቅት የተደረገላቸውን እየዘነጉ ከተሰጣቸው ይልቅ ያልተሰጣቸውን እያሰቡ ፈጣሪን ደጋግመው ሲያማርሩ ነበር፡፡ ከእነዚህ ጊዜያት በአንዱ ከምድረ በዳ ዕባቦች መጥተው ሕዝቡን ነደፉ ፤ ከእስራኤልም ብዙዎች ሞቱ፡፡ (ዘጸ. ፳፩፥፮)
በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ‹እግዚአብሔርን በድለናል ዕባቦችን ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን› ብለው ወደ ሙሴ ተማጸኑ፡፡ ‹‹ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ፡- ዕባብን ሠርተህ ፤ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው፡፡ ሙሴም የነሐሱን ዕባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ ፤ ዕባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የነሐሱን ዕባብ ባየ ጊዜ ዳነ›› (ዘኁ. ፳፩፥፰‐፱)
እግዚአብሔር በዕባብ የተነደፉትን ሰዎች እንዲሁ በቃሉ መፈወስ ሲቻለው ሙሴን ከነሐስ ዕባብ እንዲሠራ ፤ ከፍ አድርጎ በዕንጨት ላይ እንዲሰቅል ያደረገው ስለ ምንድር ነው? ከዕባቦቹ አንዱን አስገድሎ ማሰቀል ሲቻለው የነሐስ ዕባብ ማሠራትስ ለምን አስፈለገው? ቢፈልግ እንዳስለመደው በትርህን ጣለውና ዕባብ ሲሆን ስቀለው ማለት አይችልምን? ሕዝቡስ የተሰቀለውን የነሐስ ዕባብ ሲያይ መዳኑ ስለምንድር ነው?
እግዚአብሔር በዚህ ታሪክ ውስጥ በዕባብ ስለተነደፉት እስራኤላውያን ሳይሆን በዕባብ ስለተነደፍነው የሰው ልጆች ማሳየት የፈለገው ምሥጢር ስለነበር ነው፡፡ ደግሞ የት አግኝቶ ነው ዕባብ የነደፈን? ልትሉ ትችላላችሁ! በገነት ሳለን የነደፈንና ለሞት የዳረገን ዕባብ አይደለምን? እኛን የነደፈን ከእርግማን በኋላ በሚረጨው መርዙ ሳይሆን ‹ዕፀ በለስን ብትበሉ አምላክ ትሆናላችሁ› በሚል መርዝ ነበር፡፡
ሰማዕቱ ዮስጢኖስ እንዳለው ‹‹እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ምሥጢሩን ገለጠ፡፡ ለአዳም ኃጢአትን ያስተዋወቀውን ዕባብ ኃይሉን እንደሚሰባብር አሳየ፡፡ በዕባቡ የተነደፉትን (የሰው ልጆች) እንደሚያድን በማሳየትም በእርሱ ያመኑትን ሁሉ ከክፉ ሥራ ፤ ከጣዖት አምልኮና ከሌሎችም ኃጢአቶች በመስቀሉ እንደሚያላቅቃቸው አስረዳ››
እስራኤልን በመርዙ የነደፋቸው ዕባብ ቢሆንም እነርሱ እንዲድኑ የተሰቀለው ግን መርዝ በውስጡ የሌለበት የናስ ዕባብ ነው፡፡ ይህም የቀደመው ዕባብ ዲያብሎስ በኃጢአት መርዝ የነደፈንን የሰው ልጆች ለማዳን የተሰቀለው ክርስቶስ በኃጢአተኞች ፈንታ ተሰቀለ እንጂ ኃጢአት የሌለበት መሆኑን ያስረዳናል፡፡ ‹‹ዕባቡ የአዳም ዘርን ሁሉ የነከሰውን ገዳዩን ኃጢአት ያመለክታል፡፡ ይህ ዕባብ የሰውን ነፍስ ነክሶ የክፋትን መርዝ በውስጡ ጨመረበት፡፡ ከሰማያት በሚመጣ ረድኤት ካልሆነ በቀር ከዚህ መርዝ የምናመልጥበት አንዳች መንገድ አልነበረም፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅ ሥጋን ተዋሕዶ ተገለጠ፡፡ ‹እግዚአብሔርም የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ላከ› ተብሎ እንደተጻፈ ‹ኃጢአትን በሥጋ ኮነነ›› ይላል ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ (ሮሜ. ፰፥፫‐፬)
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ‹‹የናሱ ዕባብ በተፈጥሮው ሊሰቃይና ሊሞት እንደማይችል ሁሉ የተሰቀለው ክርስቶስም በአምላካዊ ባሕርይው የማይሞት ነው›› ይላል፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ደግሞ የናሱን ዕባብ አለመንቀሳቀስና አለመተንፈስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ በሞቱ ለገደለው ሞት ምሳሌ አድርጎ ያስተማረበት ሲሆን ‹ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ?› የሚለውን ቃል ከሐዋርያው ተውሶ ‹አንተ ዕባብ ሆይ መርዝህ የታለ?› ሲል እናገኘዋለን፡፡
እስራኤላውያን ከዕባቡ መርዝ የዳኑት የተሰቀለውን ዕባብ በመመልከታቸው ብቻ ነበር፡፡ ‹‹ወደ ዕባብ ተመልክቶ ከዕባብ መርዝ መዳን ማለት ምን ማለት ነው? በሞተው አምኖ ከሞት መዳን ማለት ነው›› ወደ ዕባቡ የሚመለከቱ ሰዎች መዳናቸው ‹‹እውነተኛውን የክርስቶስ ትምህርት የሚከተሉና በማይናወፅ እምነት ወደ እርሱ የሚመለከቱ ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንደሠጣቸው ያስረዳል፡፡ ዕባቡ እጅግ ከፍ ብሎ መሰቀሉ ክርስቶስ በመስቀል መከራው ማንም ሰው ለማየት በማያቅተው ሁኔታ ለሁሉም መገለጡን ያመለክታል››

እግዚአብሔር በዕንጨት ላይ ተሰቅሎ በዕንጨት ምክንያት የሞተውን ሰው እንደሚያድን ያሳየበት ሌላው ነቢይ ነቢዩ ኤልሳዕ ነበር፡፡ የኤልሳዕ ተማሪዎች ወደ መምህራቸው መጥተው ‹‹እነሆ በፊትህ የምንቀመጥበት ሥፍራ ጠብቦናል ፤ ወደ ዮርዳኖስም እንሒድ ከእኛም እያንዳንዱ ከዚያ ምሰሶ ያምጣ የምንቀመጥበት ሥፍራ በዚያ እንሥራ አሉት›› ከዚህ በኋላ እንጨት ቆርጠው ለማምጣት ተሠማሩ፡፡ ‹‹ከእነርሱም አንዱ ምሰሶውን ሲቆርጥ የምሳሩ ብረት ወደ ውኃው ውስጥ ወደቀ ፤ እርሱም ፡- ጌታዬ ሆይ ወየው ወየው የተዋስሁት ነበረ ብሎ ጮኸ፡፡ የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ ፡- የወደቀው ወዴት ነው? አለ፡፡ ስፍራውንም አሳየው ፤ እንጨትም ቆርጦ በዚያ ጣለው ብረቱም ተንሳፈፈ›› (፪ነገሥ. ፮፥፩‐፮)
ኤልሳዕ ጥልቅ ባሕር ውስጥ የወደቀውን ብረት ለማውጣት እንጨት ቆርጦ ወረወረ ፤ በዚህም እንጨት ምክንያት የሰጠመው ወጣ ፤ ሰማዕቱ ዮስጢኖስ ይህንን ታሪክ ክርስቶስ በሲኦል የሰጠመውን የሰውን ልጅ ስላዳነበት ስለ መስቀሉ ዕንጨት ይተረጉመዋል፡፡ ‹‹ኤልሳዕ የዕንጨትን ቅርፊት ወደ ውኃው ወረወረ ፤ በዚህም የነቢያት ልጆች ቤታቸውን ለመገንባት ሲሉ ዕንጨት የቆረጡበትን መጥረቢያ ከሰጠመበት አወጣው፡፡ ክርስቶስም በኃጢአታችን ከሰጠምንበት በመስቀሉ ዕንጨት አወጣን››
በዚህ በኤልሳዕ ታሪክ ላይ ከተለመደው የተፈጥሮ ሕግ ውጪ የሆነ ነገር ተደረገ፡፡ ወደ ጥልቁ ባሕር እንጨቱን በወረወረው ጊዜ መጥለቅ ጠባዩ ያልነበረው እንጨት ወደ ውስጥ ሰጥሞ ፤ መጥለቅና መስጠም የለመደውን መጥረቢያ ይዞት ወጣ፡፡ በዕለተ ዓርብ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ያደረገውም ይህንን ነበር፡፡ ሞት በሚገባው በአዳም ልጅ ፈንታ የማይሞተው አምላክ ሞተ ፤ እርሱ መስጠም ሳይገባው ወደ ጥልቁ ሰጥሞ ሰውን ከሰጠመበት የሞትና የሲኦል ባሕር አወጣው፡፡
የዕንጨትን ነገር ካነሣን በሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም አንዲት ቅኔ እናብቃ፡፡ እንደሚታወቀው ጌታችንን እንደ ወላጅ አባት ያሳደገው ቅዱስ ዮሴፍ በሙያው አናጢ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ጌታችን ለአረጋዊው እየታዘዘ ስላደገ የዕንጨት ሙያንም አብሮት ይሠራ ነበር፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በአንድ መዝሙሩ ላይ ይህንን እውነታ ከመስቀሉ ጋር አገናኝቶ ሲቀኝ ‹‹የተቤዣቸውን የሰው ልጆችን ለማሻገር መስቀሉን ድልድይ አድርጎ የሠራው አናጢ የተመሰገነ ነው›› ብሏል፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
"ሕማማት" ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ

#ሥርዓተ_ዑደት_ዘሆሣዕና
1.ምስባክ
ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር
ወቆማ እገሪነ ውስተ አዕፃድኪ ኢየሩሣሌም
ኢየሩሣሌምሰ ሕንፅት ከመ ሀገር
መዝ፩፳፪(121)…፩(1)-፫(3)
ወንጌል
ማቴ 15፡29-39
መዝሙር
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ፤እስመ እምጽዮን ይወጽእ ሕግ፤ወቃለ እግዚአብሔር እምእየሩሳሌም፤ንሳለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት፤ተቀበልዋ ለታቦት፤እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን።
ምልጣን
ንሳለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት፤ተቀበልዋ ለታቦት፤እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን።
ምዕዋድ
እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን ዋካ ይእቲ ወብርሃን
2.ምስባክ
ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ
በእምርት ዕለት በዓልነ
እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ
መዝ ፹(80)-፫(3)-፬(4)
ወንጌል
ማቴ 21፡1-11
መዝሙር
ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ሰመያ አብርሃም ወይቤላ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር፤ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ፤በእምርት እለት በዓልነ፤ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ምልጣን
ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ፤በእምርት እለት በዓልነ፤ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ምዕዋድ
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
3.ምስባክ
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አለስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላኢ
ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ
መዝ ፰(8) ፡ ፪(2)
ወንጌል
ማር 11፡ 1-11
መዝሙር
ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ወትቤ ጽዮን አርኃው ሊተ አናቅጸ ይባዑ ሕዝብ ብዙኃን፤ወያዕትቱ ዕብነ እምፍኖት፤ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት፤ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ፤ይብሉ ሆሣዕና በአርያም።
ምልጣን
ወያዕትቱ ዕብነ እምፍኖት፤ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት፤ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ፤ይብሉ ሆሣዕና በአርያም።
ምዕዋድ
ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
4.ምስባክ
እምስራቀ ፀሐይ እስከነ ዓረብ
ይትአኰት ስሙ ለእግዚአብሔር
ልዑል እግዚአብሔር መልዕልተ ኵሉ አሕዛብ
መዝ ፻፲፪(112/113)፡፫(3)--፬(4) መዝ ፵፱(49)፩1()፡፪(2)
ወንጌል
ሉቃ 19 ፡ 28—40
መዝሙር
ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ባረኮ ያዕቆብ ለይሁዳ ወልዱ፤ወይቤሎ ሀሎ ንጉሥ ዘይወጽእ እምኔከ፤ዘየሐፅብ በወይን ልብሶ፤ወበደመ አስካል ሰንዱኖ፤ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ፤ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
ምልጣን
ዘየሐፅብ በወይን ልብሶ፤ወበደመ አስካል ሰንዱኖ፤ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ፤ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
ምዕዋድ
ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
5.ምስባክ
ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር
ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን
እስመ አፅንዐ መናሥግተ ኆኃትኪ
መዝ ፻፵፯(147)፤፩(1)—፪(2)
ወንጌል
ዮሐ 12፤ 12-26
መዝሙር
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ባዑ ውስተ ሀገር ወበዊአክሙ ትረክቡ ዕዋለ አድግ ዕሡረ ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ
ምልጣን
ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ
ቅኔ ማህሌት
ሃሌ ሉያ፤አልጺቆ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ርእያ ለሀገር፤ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን፤ነዋ ንጉሥኪ በጽሐ ብርሃንኪ ዮም ሰላምኪ።
ምልጣን
ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ፤በጽሐ ብርሃንኪ ዮም ሰላምኪ፤ተፈሥሒ በሕዝብኪ ዮም ሰላምኪ፤ ይትሐፈሩ ጸላዕትኪ ዮም ሰላምኪ፤ሰላምኪ ሰላምኪ ዮም ሰላምኪ።
ስርዓተ ቅዳሴ
ወደ ቅደሴ ሊገቡ ሲሉ ካህናቱ መስዋዕቱን ይዘው ወደ መቅደሱ ይደርሱና እንዲህ በማለት ይጣራሉ
ይ.ዲ
አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት/፫/ (3 ጊዜ)
ይ.ካ
መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት/፫/
ይ.ዲ (ዳግም)
አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት/፫/
ይ.ካ
መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት/፫/
ይ.ዲ
እግዚአብሔር አምላከ ኃያላን
ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት
አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት
ይ.ካ
ይባዕ ንጉሠ ስብሐት
ይባዕ አምላከ ምሕረት
በሰሙነ ሕማማት የሚሞቱት ወንድሞች እና እህቶቻችን ጸሎተ ፍትሃት ስለማይደረግላቸው ጸሎተ ፍትሃት ውይም መስተብቁዕ የተሰኘው ጸሎት በእለተ ሆሣዕና ይደረግላቸዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሰሙነ ህማማት ሰኞ፡-
መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ-እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡
በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡
በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
አንጽሆተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦
ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተመቅደስ ሄደ፤ ቤተመቅደስ፣ቤተጸሎት፣ ቤተመሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡
በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

የሰሙነ ህማማት ማክሰኞ
#የጥያቄ_ቀን_ይባላል፡-
ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡
ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተዓምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. 21፥23-27፣ ማር. 11፥ 7-35፣ ሉቃ.21፥23-27፣ ማር.11፥27-33፣ ሉቃ. 20፥1-8/፤ እርሱም ሲመልስ፤ «እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይ ነውን? ወይስ ከሰዉ? በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ወይስ በሰው ፈቃድ?» አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፤ ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው» ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተዉት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡
#የትምህርት_ቀንም_ይባላል፡-
በማቴ. 21፥28፣ ምዕ. 25፥46፣ ማር.12፥2፣ ምዕ.13፥37፣ ሉቃ. 20፥9፣ ምዕ. 21፥38 የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፣ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበቱ መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡
✟🍀🌸 🌸🍀✟

"የሰሙነ ህማማት ረቡዕ"
ምክረ አይሁድ ይባላል፦
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡/ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6/ የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፦
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት /ባለሽቱዋ ማርያም/ «ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ» ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡
የእንባ ቀንም ይባላል፦
ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡/ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8/ ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡
እንበለ ደዌ ወህማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

ሰሙነ ህማማት ዘሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስ)
በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ ማቴ. 26፣ 36-46 ዮሐ.17
#ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡
#የምስጢር_ቀን_ይባላል
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡
#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል
ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል /ሉቃ. 22፣20/ ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡
#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት /ዮሐ. 15፣15/፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡

የሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ
ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያን ልዩ ቀን ነው፡፡ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁ ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግብር ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት፣ ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን፤ አሳዳጅ አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡
#የስቅለት_ዓርብ ይባላል
የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለ ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል። (ማቴ 27፡35)
#መልካሙ_ዓርብ ይባላል
ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ሲያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ። በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይር ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርአያ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ ስላደረገውና በዕለተ ዓርብ በሞቱ ሕይወትን ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡
በዚህ ዕለትም ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱ ፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ ተአምራት አሳይቷል፦
1. ፀሐይ ጨልማለች
2. ጨረቃ ደም ሆናለች
3. ከዋክብት ረግፈዋል
4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዷል
5. ምድር ተናወጣለች (ተንቀጥቅጣለች)
6. መቃብሮች ተከፍተዋል
7. ሙታን ተነስተዋል
በዓመት አንድ ጊዜ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን የምንውልበትና በዋዛ ፈዛዛ ልናሳልፈው አይገባም፡፡