የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
ስለትሕትና የሚነገሩ ቃላት ሁሉ ምን ያህል
የተደነቁ ናቸው! ትሕትና ሰይጣን እንዲገዛ
ያደርገዋል። ይህ በታላቁ አባት አባ መቃርዮስ
ሕይወት ግልፅ ሆኖ እናገኘዋለን። ሰይጣን ተገልጾ አባ መቃርዮስን እንዲህ አለው "ከአንተ መራቅ እፈልጋለሁ።መቃርዮስ እኛ መድረግ የምንችለው ነገር ግን አንተ የማታደርገው ምንድን ነው? አንተ ትጾማለህ እኔም እንደ እንተ አልበላም፤ ነቅተህ ትጠብቃለህ እኔም አልተኛም፤ አነተ በበርሃ ብቻህን ትኖራለህ እኔም እንደ አንተ አደርጋለሁ ነገር ግን በእንድ ነገር አሸነፍከኝ" አለው። አባ መቃርዮስም በምን እንዳሸነፈው እንዲነግረው ሰይጣንን ጠየቀው። ሰይጣንም ''በትሕትና አሸነፍከኝ'' አለው።

ይህ ግልፅ ነው ሰይጣን ትሑት መሆን አይችልም። ሁልጊዜም ለራሱ ክብር ይሰጣል። ለዚህም ነው ትሕትና ሰይጣንን የሚያሸንፈው። ሰይጣን ገንዘቡ ማድረግ የማይችለውን ትሕትና ቅዱሳን ገንዘባቸው አድርገዋል። የሚየምኑትን ከማያምኑ ወገኖች፤ የእግዚአብሔር የሆኑ ወገኖችን የእግዚአብሔር ካልሆኑት የሚለያቸው ጥበብ ይሄ ነው።

ሰይጣን ገንዘቡን ወዳጅ ነው፤ ማንም ወገን ገንዘቡን ከያዘበት ከእርሱ አይርቅም ስለዚህ
የእግዚአብሔር ወገን መሆን ከፈለግህ የሰይጣንን ገንዘቡን መልስለትና የእግዚአብሔር ልጆች የያዙትን ገንዘብ ገብዘብህ አድርግ። የሰይጣን ገንዘቡ ትዕቢት፣ ራስን ማግነን፣ ከንቱ መታበይ ሲሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ገንዘብ ትህትና ነው።

'የሕይወት መዓዛ ከተባለው #የአቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ መጽሐፍ የተወሰደ'
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
እሳት የእግዚአብሔር #የወርቅ_ማዕጠንት የእመቤታችን ወርቅ የንጽሕናዋ ማዕጠንቱ እሳቱን እንደተሸከመ እመቤታችንም ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኗ የመሸከሞ ምሳሌ
JOIN OUR CHANNEL
@ethiopianorthodoxbooks
#የእመቤታችን_ስደት_ስደታችን_ነው!

አዎ በተወደደው ልጇ ፊት ያነባችው መሪር ዕንባ የሃጥያታች ማጠብያ ይሆን ዘንድ ተሰድዳለችና !

ከአባቶቿ ሀገር ወጥታ 3 ዓመት ከ 6 ወር በዱር በገደሉ ተንከራተተች !
የሚያገኟት ሁሉ " አንቺ አመልሽ ቢከፋ ነው እንጂ ደም ግባትሽስ ያማረ ነበር" እያሉ አፌዙባት ፤ ፊት የሚገርፉ የሰው አይኖች ልብ የሚወጉ የጦር ቃሎች ድንግል ማርያምን ብዙ ጊዜ #አስለቅሷት ፤ ጻዲቅ የሚሆን ዮሴፍ ስለ ደግነቱ ብዛት ፍየል ጠባቂ እረኛ ተብሎ ተሰደበ !

ለሰው ልጆች ሁሉ እሩሩህ የምትሆን ለፍጥረት ሁሉ የምታዝን ቤዛዊት አለም ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን #ጌታችን_መዳኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ይዛ #ከዮሴፍ እና #ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደች ፤መከራ፥ጭንቀት፥ ግፍ ፥ ከማንም በላይ #ታገሰች !

እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማር ያም ሆይ ስደትሽ ስደታችን ነው ፥መከራሽ ፥መከራችን ነው፥ሀዘንሽ ፥ሀዘናችን ነው በፍፁም አይገባም ላንቺ ፤ #ስደት_ይብቃሽ_ነይ_ወደ_አባቶችሽ_ሀገር_ተመለሽ! የእናታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ ፍቅራ በልባችን ይደርብን ባማላጅነቷን ትርዳን!
መልካም ፆም ይሁንልን ለበረከት ያድርግልን በቸርነቱም ይጠብቀን !
© Adugna brhanu መስከረም 26/11
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር


🎚🔆🎚🔆 አትማረኝ🎚🔆🎚🔆
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

በጣና ገዳማት ውስጥ የአቡነ አሳይ ዋሻ አለ በዚህ ዋሻ አንድ ያልተማረ የቤተክርስቲያንን ትምህርት የማያውቅ ሰው ጸሎት ሲጸልይ አንድ አባት በጀልባ ተሳፍረው ይመጡና ያገኙታል።
🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶
ወደ ደሴቷም አረፍ ልበል ብለው ሲገቡ ያ ወጣት ሲጸልይ ይሰሙታል ቀረብ ብለው ቢያደምጡ ይህ ሰው የሚጸልየው "አትማረኝ" እያለ ነው።

እኝህ አባት በጣም ይደነግጡና እንዲህ ያለ ጸሎት አለ ወይ አትማረኝ የሚል ማን ነው ያስተማረህ ሲሉት አንድ መነኩሴ ነው ያስተማሩኝ አላቸው።

እሳቸውም ይህማ ሰይጣን ነው በመነኩሴ ተመስሎ ያስተማረህ እንጂ አትማረኝ ብሎ ጸሎት የለም ብለው "አቡነ ዘበሰማያትን" አስተማሩት። ይኽ ሰው እንደምንም ታግሎ አባታችን ሆይን ከተማረ በኋላ እኝህን አባት ያሰናብታቸዋል።

እሳቸውም በጀልባ ተሳፍረው መንገድ ሲጀምሩ ይኽ ወጣት ወደ ቀደመ በዓቱ ገብቶ መጸለይ ሲጀምር ያን ጸሎት ረሳው። ምን ነበር ያስተማሩኝ ብሎ ቢያስብ ጠፋበት። ከበዓቱም ሮጦ ወጥቶ በጀልባ ተሳፍረው የሚሄዱትን አባት አስቁሞ "ምን ብለው ነው ያስተምሩኝ?" ብሎ ጠየቃቸው እኝህም አባት ሲያዩት ውሃ ላይ ቆሟል፣ በውሃ ላይ ነው ሮጦ የመጣው አትኩረው ቢመለከቱት ውኃው ላይ እንደቆመ ነው።

"በል የእኔ ልጅ እንደቀድሞው አትማረኝ እያልክ ጸልይ" አሉት ይባላል።
🙏🕯🙏🕯🙏🕯🙏🕯🙏🕯🙏🕯

ወጣቱ ባለማወቅ በሚጸልየው ጸሎት ውስጥ በቅቶ ነበር። እግዚአብሔር የሰማው ያለውን ሳይሆን የልቦናውን ነው።

የምንጸልየው ጸሎት የተዘበራረቀ ቢሆንም እንኳን እግዚአብሔር እያቃና ይሰማዋል።

ስለዚህም ከመጸለይ ወደ ኋላ አንበል እኛ የምንጸልየው ባይገባንም በዙሪያችን ያሉት አጋንንቶች ገብቷቸው ይሸሻሉ።

╭══•:|↠☞✝️✝️†↞☜⇣|: ══╮
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
╰══•:|↠☞†✝️✝️↞☜⇡|: :══╯
ሥርዓተ ማኅሌት ዘዘመነ ጽጌ "፪ኛ ሳምንት" "በዓለ አብርሃ ወአጽብሃ ወዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ" "ጥቅምት ፬"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤ መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢት ዓለም፤ ወልጡ አምልኮትየ በፀጋክሙ ፍፁም፤ እምአምልኮ ጣኦት ግሉፍ አሐዱ ድርኅም።

ዚቅ
ለሥሉስ ቅዱስ ጥዑም ቃሎሙ፤ ናርዶስ ፀገየ ውስተ አፉሆሙ።

ማኅሌተ ጽጌ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ ለእረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን (ጽላተ ኪዳን)፤ ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን።

ወረብ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ዘኮንኪ ለእረፍት ጽላተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/

ዚቅ
ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ ኅቡረ ንትፈሣሕ ዮም በዛቲ ዕለት።

ማኅሌተ ጽጌ
ፄነወኒ ተአምርኪ ሶበ ይነፍሑ ነፋሳት፤ ከመ ጼና ገነት ዘይጼኑ እምርኁቅ ፍኖት፤ መዓዛ አፈዋት ማርያም ወጽጌ መንግሥት ቡሩክ፤ ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት፤ ጽጌ ጽጌ ጽጌ አሮን ዘክህነት።

ወረብ
ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት/፪/
መዓዛ አፈዋት ማርያም መዓዛ አፈዋት ወጽጌ መንግሥት/፪/

ዓዲ (ወይም)
ወረብ
ጼነወኒ ተአምርኪ ነፋሳት ሶበ ይነፍሑ/፪/
መዓዛ አፈዋት ማርያም ወጽጌ መንግሥት ጽጌ መንግሥት አብርሃ ወአጽብሃ/፪/

ዚቅ
ሠርፀ መንግሥት ዘእምሥርወ ዕሤይ፤ ወጽጌ ንጽሕት ዘእምጒንደ ዳዊት፤ ወብኪ ይትሜዓዙ ኲሎሙ ቅዱሳን።

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

ወረብ
"እንዘ ተሐቅፊዮ"/፪/ ለሕፃንኪ ርግብየ ንጽሕ/፪/
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ/፪/

ዚቅ
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ፤ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፤ ወኲሉ ነገራ በሰላም።

ዓዲ (ወይም)
ወትወጽእ እምግበበ አናብስት፤ እምታዕካ ዘነገሥት እምቅድመ ሃይማኖት፤ ንዒ ርግብየ ሠናይት፤ ኲለንታኪ ሠናይት፤ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ ንዒ ርግብየ ሠናይት፤ ንዒ ርግብየ ሠናይት።

ማኅሌተ ጽጌ
ሶበ ዴገነኪ አርዌ በሊዓ ሕፃንኪ ዘኀለየ፤ በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጎይየ፤ አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ ጸገየ፤ ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሐየ፤ ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ።

ወረብ
ብእሲተ ሰማይ ማርያም ፀሐየ ዘትለብሲ/፪/
ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ ተአምረኪ/፪/

ዓዲ (ወይም)
አመ አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ/፪/
ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ ዘርእየ ተአምረኪ/፪/

ዚቅ
በሊዓ ሕፃናት ሶበ ኀለየ፤ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ፤ ዘምስለ ዮሴፍ ናዝራይ፤ ነገደት ቊስቋመ ናዛዚተ ኃዘን ወብካይ።

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምዕንቌ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/

ዚቅ
በወርቅ ወበዕንቊ ወበከርከዴን፤ ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ፤ መድኃኒቶሙ ለነገሥት።

ሰቆቃወ ድንግል
እፎ ጎየይኪ እምፍርሐተ ቀትል እምገፀ ሄሮድስ ቊንጽል፤ ወለተ አናብስት ግሩማን እለ ይጥሕሩ በኃይል፤ ኢፈቀድኪዮ በምድር ለመንግሥተ ዓለም ወብዕል፤ እስመ ልማዱ ትሕትና ለፍሬ ከርሥኪ ልዑል፤ ከማሁ ግዕዘኪ በምግባር ወቃል።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ እምሊባኖስ ትወጽእ መርዓት፤ ወትወጽእ እምግበበ አናብስት፤ እምታዕካ ዘነገሥት፤ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ፤ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል።

መዝሙር
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወዕፁብ፤ ለዘሃሎ መልዕልተ አርያም፤ አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ፤ ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩሃን ብሩህ፤ አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ፤ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንጹሐን ንጹሕ፤ አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ፤ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባሪ ያዕርፉ ባቲ፤ አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ፤ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን፤ ከመ ጽጌ ደንጎላት ዘውስተ ቌላት፤ ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።

ዓራራይ
በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት፤ በጊዜሁ ቆመ በረከት፤ ናርዶስ ጸገየ በውስተ ገነት፤ ሐመልማለ ገነት፤ አስካለ በረከት፤ ወሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት።

ዕዝል
ባረከ ዓመተ ጻድቃን፤ ወአጽገበ ከርሠ ርኁባን፤ ባዕል ውእቱ የአክል ለኲሉ፤ ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤ አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት።

ሰላም
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሐረገ ወይን፤ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ፤ ሐረገ ወይን፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት፤ ሐረገ ወይን፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ ሐረገ ወይን፤ ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤ ወጸገወ ሰላመ ለኲሉ።

╭══•:|↠☞✝️✝️†↞☜⇣|: ══╮
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
╰══•:|↠☞†✝️✝️↞☜⇡|: :══╯
🚫መርዝ ምንድነው?🚫

አንድ ሰው ለጠየቀው ጥያቄ የተሰጠው መልስ ውብ ነበር?

ማንኛውም ከሚያስፈልገን መጠን በላይ የሆነ ነገር ሁሉ መርዝ ነው። ስልጣን ፣ ሀብት፣ ድህነት፣ ንዴት፣ ስግብግብነት፣ ስንፍና፣ ጥላቻ ፣ ራስ ወዳድነት፣ ጉጉት፣ ወይንም ሌላ ማንኛውንም ነገር ሊሆን ይችላል።


ቅናት ምንድነው?
የሌሎችን በጎ ነገር አለመቀበል ነው። የሌሎችን በጎነት ብንቀበል ፣ መነሳሳት ይፈጥርልናል ።

ንዴት ምንድነው?
ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮችን አለመቀበል ነው። ያንን ብንቀበል ትእግሥት ይሆነናል።

ጥላቻ ምንድነው?
ጥላቻ አንድን ሰው እንዳለ በሰውነቱ መቀበል አለመቻል ነው። አንድን ሰው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ብንችል ግን፣ ያ ጥላቻ ፍቅር ይሆናል።

ሁሉ ነገር በጊዜው ይሆናል። ለሁሉም ጊዜ አለው
መጽሐፍ እንዲል👇


(መጽሐፈ መክብብ ምዕ. 3)
----------
1፤ ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።

. . .
4፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው

. . .
7፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤

ያለጊዜው የሚሆን ነገር ሁሉ መርዝ ይሆንብናል።

╭══•:|↠☞✝️✝️†↞☜⇣|: ══╮
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
╰══•:|↠☞†✝️✝️↞☜⇡|: :══╯
“ስብሐት ለከ ኢየሱስ በአፈ ኲሉ ውዱስ፤
ስብሐት ለከ ኢየሱስ ቀዳሴ ሥጋ ወነፍስ፤
ስብሐት ለከ ኢየሱስ ለዕሩቃን ልብስ፤
ስብሐት ለከ ኢየሱስ ዘኢትሠዐር ንጉሥ፤
ስብሐት ለከ ኢየሱስ ቃለ አብ ቅዱስ”

በኹሉም አፍ የተመሰገንኽ ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል፤ ሥጋንና ነፍስን ያከበርኽ ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል፤ ለተራቈቱት ልብስ የኾንኽ ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል፤ የማትሻር ንጉሥ ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል፤ ቅዱስ የአብ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል

መቅድመ ተአምረ ኢየሱስ
የዮሐንስ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ

በዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one
Audio
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one