የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
ስለትሕትና የሚነገሩ ቃላት ሁሉ ምን ያህል
የተደነቁ ናቸው! ትሕትና ሰይጣን እንዲገዛ
ያደርገዋል። ይህ በታላቁ አባት አባ መቃርዮስ
ሕይወት ግልፅ ሆኖ እናገኘዋለን። ሰይጣን ተገልጾ አባ መቃርዮስን እንዲህ አለው "ከአንተ መራቅ እፈልጋለሁ።መቃርዮስ እኛ መድረግ የምንችለው ነገር ግን አንተ የማታደርገው ምንድን ነው? አንተ ትጾማለህ እኔም እንደ እንተ አልበላም፤ ነቅተህ ትጠብቃለህ እኔም አልተኛም፤ አነተ በበርሃ ብቻህን ትኖራለህ እኔም እንደ አንተ አደርጋለሁ ነገር ግን በእንድ ነገር አሸነፍከኝ" አለው። አባ መቃርዮስም በምን እንዳሸነፈው እንዲነግረው ሰይጣንን ጠየቀው። ሰይጣንም ''በትሕትና አሸነፍከኝ'' አለው።

ይህ ግልፅ ነው ሰይጣን ትሑት መሆን አይችልም። ሁልጊዜም ለራሱ ክብር ይሰጣል። ለዚህም ነው ትሕትና ሰይጣንን የሚያሸንፈው። ሰይጣን ገንዘቡ ማድረግ የማይችለውን ትሕትና ቅዱሳን ገንዘባቸው አድርገዋል። የሚየምኑትን ከማያምኑ ወገኖች፤ የእግዚአብሔር የሆኑ ወገኖችን የእግዚአብሔር ካልሆኑት የሚለያቸው ጥበብ ይሄ ነው።

ሰይጣን ገንዘቡን ወዳጅ ነው፤ ማንም ወገን ገንዘቡን ከያዘበት ከእርሱ አይርቅም ስለዚህ
የእግዚአብሔር ወገን መሆን ከፈለግህ የሰይጣንን ገንዘቡን መልስለትና የእግዚአብሔር ልጆች የያዙትን ገንዘብ ገብዘብህ አድርግ። የሰይጣን ገንዘቡ ትዕቢት፣ ራስን ማግነን፣ ከንቱ መታበይ ሲሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ገንዘብ ትህትና ነው።

'የሕይወት መዓዛ ከተባለው #የአቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ መጽሐፍ የተወሰደ'
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር