የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
#የእመቤታችን_ስደት_ስደታችን_ነው!

አዎ በተወደደው ልጇ ፊት ያነባችው መሪር ዕንባ የሃጥያታች ማጠብያ ይሆን ዘንድ ተሰድዳለችና !

ከአባቶቿ ሀገር ወጥታ 3 ዓመት ከ 6 ወር በዱር በገደሉ ተንከራተተች !
የሚያገኟት ሁሉ " አንቺ አመልሽ ቢከፋ ነው እንጂ ደም ግባትሽስ ያማረ ነበር" እያሉ አፌዙባት ፤ ፊት የሚገርፉ የሰው አይኖች ልብ የሚወጉ የጦር ቃሎች ድንግል ማርያምን ብዙ ጊዜ #አስለቅሷት ፤ ጻዲቅ የሚሆን ዮሴፍ ስለ ደግነቱ ብዛት ፍየል ጠባቂ እረኛ ተብሎ ተሰደበ !

ለሰው ልጆች ሁሉ እሩሩህ የምትሆን ለፍጥረት ሁሉ የምታዝን ቤዛዊት አለም ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን #ጌታችን_መዳኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ይዛ #ከዮሴፍ እና #ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደች ፤መከራ፥ጭንቀት፥ ግፍ ፥ ከማንም በላይ #ታገሰች !

እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማር ያም ሆይ ስደትሽ ስደታችን ነው ፥መከራሽ ፥መከራችን ነው፥ሀዘንሽ ፥ሀዘናችን ነው በፍፁም አይገባም ላንቺ ፤ #ስደት_ይብቃሽ_ነይ_ወደ_አባቶችሽ_ሀገር_ተመለሽ! የእናታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ ፍቅራ በልባችን ይደርብን ባማላጅነቷን ትርዳን!
መልካም ፆም ይሁንልን ለበረከት ያድርግልን በቸርነቱም ይጠብቀን !
© Adugna brhanu መስከረም 26/11