[የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ]
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ጳጒሜን የተባለችው 13ኛዋ ወር በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል፡፡ የ5 ቀናትን የጳጉሜንን አመጣጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጠንቅቀው ቀምረው በባሕረ ሐሳብ ብራናቸው ላይ ጽፈውልናል፡፡
ይኸውም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ያሉት 12ቱ ወራት ያላቸው ዕለታት በአጠቃላይ 360 ናቸው፡፡ በቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ትንተና 1 ቀን የሚባለው 12 ሰዓት ከ52 ካልዒት ከ31 ሳልሲት ነው፡፡
1 ካልዒት ማለት 24 ሰከንድ ሲኾን 52 ካልዒት ማለት 1248 ሰከንድ ነው፤ 31 ሣልሲት ማለት 12.4 ሰከንድ (ቅጽበት) ይኾናል፡፡ በመኾኑም በአንድ ቀን ውስጥ 1 ደቂቃ ከ0.4 ሰከንድ ትርፍ መኖሩን ያስረዳል፡፡
በመኾኑም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ባሉት 360 ቀናት ያሉትን 52 ካልዒት ወይም 1248 ሰከንድ እንዲኽ እናባዛቸዋለን፤ 52 ካልዒት X 360 ዕለታት= 18720 ካልዒት ወይም (449, 280 ሰከንድ) ይኾናል፤ ወደ ደቂቃ ስንለውጠው 7488 ደቂቃ ወይም 5 ዕለት ይኾናልና የጳጒሜን አመጣጥ ይቺ ናት፡፡
☞☞ [የጳጉሜን 5 ምስጢር]
አራቱ የዓመት ወቅቶች ማለትም መፀው፣ ሐጋይ፣ ጸደይና ክረምት 91, 91 ቀናት የሚኾኑት ከጳጒሜን 1 አንድ ዕለት እየተሰጣቸው ሲኾን በአጠቃላይ 364 ዕለታት ወይም 52 ሳምንት ኾኖ አንዲት ዕለት ትተርፋለች፤ ይቺም ጳጒሜን 5 ስትኾን በኢትዮጵያ ቀደምት የዘመን ቀመር ሊቃውንት “ዕለተ ምርያ፣ አዕዋዲት” ትባላለች፡፡
ዕለተ ምርያ ማለት ዕለተ መድኀኒት ማለት ነው፤ ምክንያቱም ጳጒሜን 5 የመድኀኒታችን ክርስቶስ ልደትን የምናውቅባት ስለኾነች ነው፤ ይኸውም ጳጒሜን 5 በዋለችበት ዕለት የክርስቶስ ልደት ዕለት በተመሳሳይ መልኩ ይውላል፡፡
ለምሳሌ የዚኽ ዘመን ጳጉሜን 5 ዕለት ሰኞ ናት፤ በተመሳሳይ መልኩ የ2011 የጌታችን የልደት በዓል ታኅሣሥ 29 ሰኞ ይውላል፡፡ በዚህ ምክንያት ዕለተ ምርያ የሚል ሥያሜ ሊሰጣት ችሏል፡፡
በተጨማሪም ጳጒሜን 5 የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የዐዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደኾነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመኾኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ መዋሉ በእጅጉ ይደንቃል፡፡
☞☞ [ጳጉሜን 6 እና አመጣጧ]
የ6ተኛዋ ጳጒሜን አመጣጥን ስናይ፡- በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ስሌት 1 ዓመት የምንለው 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው፡፡ ይህን የየዓመቱን 6 ሰዓት ስንቈጥር የኹለት ዓመት 12 ሰዓት፤ የሦስት ዓመት 18 ሰዓት፤ የአራተኛው ዓመት 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ሲሆን ይኸውም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መጀመሪያ ሲኾን ይኸውም በቀደምት የአቡሻክር ሊቃውንት “መጠነ ራብዒት፣ ሠግረ ዮሐንስ” ትባላለች። ዘመነ ዮሐንስ ተራምዶ የሚያልፍባት ለማለት ነው፡፡
እኛ ጳጒሜን 6 ስናደርግ ምዕራባውያኑ ግን የጳጒሜን ወራትን በማጥፋታቸው ኹሌ ለእነርሱ 28 የኾነችው የካቲትን በአራት ዓመት አንዴ 29 ያደርጋሉ፤ Leap Year ብለው ይጠሯታል፡፡
☞☞ [ጳጒሜን 7 እና አመጣጧ]
የኢትዮጵያን ቀደምት ሊቃውንትን በእጅጉ እንድናደንቅ ከሚያደርገን አንዱ የጳጒሜን 7ትን ስሌት ጠንቅቀው አስልተው በብራና የአቡሻክር መጽሐፍ ላይ ጽፈውልን ስሌቱን አስልተው ማለፋቸው ሲኾን፤ የስሌቱም መጠሪያ “ዕሪና መዓልት ዕሪና ሌሊት” በመባል ይታወቃል፡፡
ይኸውም 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ የኾነው የፀሓይ ዐውደ ዓመት የ6 ካልዒት ወይም የ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ጥርቅም ወይም ከላይ ያየናት የአንዷ ዕለት 0.4 ሰከንድ ጥርቅም ነው፡፡
ስናሰላውም የ5 ዓመቱ 30 ካልዒት፤ የ10ሩ ዓመት 60 ካልዒት (1 ኬክሮስ ወይም 24 ደቂቃ) ይሆናል፡፡ የ100 ዓመት (10 ኬክሮስ) ወይም 240 ደቂቃ (4 ሰዓት) ይኾናል፡፡ የ200 ዓመት 20፤ የ300 ዓመት 30፤ የ400 ዓመት 40 ኬክሮስ፤ የ500 ዓመት 50 ኬክሮስ፤ የ600 ዓመት 60 ኬክሮስ ሲሆን 60 ኬክሮስ ማለት 1440 ደቂቃ ወይም 24 ሰዓት ወይም 7 ተኛዪቱ ጳጉሜን ናት፡፡
ሆኖም ግን የአቡሻሕርና የባሕረ ሐሳብ መምህራን ጳጕሜን 7 የተገኘችው ከጥቃቅን መስፈርት ወገን ከሆነችው ከካልዒት በመሆኑ ሒሳቧ ብቻ ታስባ ድቁቅ ደቃይቅ ተብላ ብቻ እንድትተው በማዘዝ ዕለቷ ግን በኅሊና ብቻ እንድትታሰብ እንጂ ተቆጥራ እንዳትከበር አዘዋል፡፡ በመሆኑም በማሰብ ብቻ እንጂ በዕለትነት ተቆጥራ አትውልም፡፡
በአቡሻሕሩ ስሌት መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ 12 ዕሪና መዓልት 12 ዕሪና ሌሊት (ጳጉሜን 7) ተመላልሶ በ1700 ዓ.ም. ወይም በ7800 ዓመተ ዓለም ኾኖ 13ኛው ከተጀመረ 311 ሆኖ በዘመነ ሉቃስ ይኸው ሊፈጸም በ2011 ዓ.ም ካሰላነው 289 ዓመት ይቀራል ወይም በ2300 ዓ.ም. ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡
ይህ በሚሆን ጊዜ ዐቀድ የሚባል ኮከብ አለ፤ ሰሌዳው በፀሓይ ልክ፤ ባሕርዩ ጽሉም ነው፤ ርሱ በ600 ዓመት መጥቶ ፀሓይን ይጋርዳታል፤ ያን ጊዜ ሌሊቱና መዓልቱ ጨለማ ኹኖ ይውላል ያድራል፤ ይኸውም የመከራ ፊት አውራሪ አጫሪ ነው፤ ይኸውም በዐጤ ኢያሱ ወይም ፀሓይ ሰገድ በተባለ በዐጤ ዮስጦስ ጊዜ ተደርጓል ብለው መዝገብውልናል፡፡ ይህን ስናይ የቀደምት ኢትዮጵያውያንን ዕውቀት ሁሌም እንድናደንቅ ያደርገናል፤ መልካም የጳጉሜን 13ኛ ወራት ይሁንልን፡፡
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ጽሑፉን ሲወስዱ ምንጩን መጥቀስ ታላቅነት ነው)

ይኩን ለነ ዘመነ ፍሰሐ ወሰላም።፳፻፲፩ ዓ/ም ሃገርና ሰላም ልኾነሉ፣ ናይ ሰላም ዘመን፣ዘመነ ራህዋ ክኾነልና ይምነ።
++ከልደት በፊት ተጀምሮ
ከሞት በኋላ ያልቆመ ስብከት ++(
አይሁድ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ መልእክተኞችን ደጋግመው እየላኩ ስለ ማንነቱ ይጠይቁት ነበር፡፡ አጥብቀው የሚጠይቁት የእግዚአብሔር መልእክተኛ መሆኑን አረጋግጠው አምነው ሊቀበሉት ባይሆንም እንኳን ቅዱስ ዮሐንስ ግን ‹‹ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ›› ሲል መለሰላቸው፡፡
በእርግጥም ዮሐንስ በነቢዩ ‹‹የአዋጅ ነጋሪ ቃል ፡- የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሃ አስተካክሉ፡፡ ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይበል ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል ጠማማውም ይቃናል ስርጓጉጡም ሜዳ ይሆናል የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል ሥጋ ለባሽም ሁሉ በአንድነት ያየዋል›› ተበሎ ተነግሮለት ነበር፡፡ (ኢሳ. 40፡3)
የምድረ በዳ ጩኸት
ጩኸት በቀጥታ ሲተረጎም የድምፅን ከፍ ማለት ያመለክታል፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ነበር፡፡ ምድረ በዳ ልምላሜ የሌለበት ፣ ዛፍ የማይገኝበት ሥፍራ ነው፡፡ የዮሐንስ በዚህ ሥፍራ መጮኽ የሕይወት ዛፍ መንገድ በገነት መካከል በተዘጋበት ጊዜ ፣ የሕይወት ውኃ የሆነ የጌታችንን መምጣት ፍጥረት ሁሉ እንደ ምድረ በዳ ደርቆ በሚጠብቅበት ጊዜ ዮሐንስ ለማስተማር መነሣቱን ያሳያል፡፡ በምድረ በዳ መጮኹም እንደ ምድረ በዳ የደረቀ ልብ ባላቸው ፣ በሚሰሙት ቃል በማይረሰርሱ ፣ በማይለመልሙ አይሁድ መካከል ዮሐንስ አስተማሪ ሆኖ መነሣቱን ያሳያል፡፡‹ተራራው ዝቅ ይበል ፣ ሸለቆው ከፍ ይበል› እያለ እንደ ተራራ በትዕቢት ያበጠ ልብ ያላቸውን ፣ እንደ ሸለቆ የተዋረደ ሰብእና ያላቸውን ሁሉ እያስተማረ መጣ፡፡ ዮሐንስ በምድረ በዳ መካከል መጮኹ በልበ ደንዳኖች መካከል ቃሉን መስበክ እንደሚገባ ድንቅ ማሳያ ነው፡፡
ዮሐንስ ድምፅ - ጌታ ቃል
ቅዱስ ዮሐንስ ራሱን ከነቢዩ ቃል ተውሶ ‹የሚጮኽ ሰው ድምፅ› ነኝ ብሎ ጠርቷል፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ እንደተረጎመው ይህ የዮሐንስ አነጋገር ጥልቅ መልእክት ያለው ነው፡፡
ሊቃውንት ‹በምድረ በዳ የሚጮኸ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ› ብሎ የተናገረውን የመጥምቁ ዮሐንስን ንግግር ሲተረጉሙ ዮሐንስ ራሱን ድምፅ ያለበትን ምሥጢርም ያነሣሉ፡፡ አንድ ሕፃን ገና እንደተወለደ ቃል ማውጣት አይችልም ድምፅ ማሰማት ግን ይችላል፡፡ ቃል መናገር እስከሚችል ድረስ በድምፁ ብቻ ከወላጆቹ ጋር ሲግባባ ይቆያል፡፡ ቃል መናገር ሲጀምር ግን የድምፁ አስፈላጊነት ይቀርና ቃል ሥፍራውን ይይዛል፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ራሱን ድምፅ ብሎ የጠራውም ከቃል መምጣት በፊት ሲያስተምር የነበረ ስለሆነ ነው ፤ ቃል የተባለ እግዚአብሔር ወልድ ሲመጣ ግን ድምፅ የተባለ መጥምቁ ዮሐንስ ‹‹እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባኛል›› ብሎ ለጌታው ለቃል መንገድ ለለቀ፡፡ (ዮሐ. ፩፥፳፫፣፫፥፴)
በድምፅ ቃል እንደሚገለጥ በመጥምቁ ዮሐንስም ስብከት ጌታችን ተገልጧል፡፡ ድምፅ ያለ ቃል ትርጉም እንደሌለው የዮሐንስም ተልእኮ ያለ ጌታችን መምጣት ትርጉም የለውም፡፡ ቃል ያለ ድምፅ ሊኖር ይችላል ፤ ለምሳሌ ድምፅ አውጥቶ ለመናገር የማይችል ሰው በልቡ ቃል ያለማቋረጥ ይመላለሳል እንዲሁም በጽሑፍ ወይም በምልክት ተጠቅሞ ቃልን ለሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡ ስለዚህ የድምፅ አለመኖር ቃልን ከመኖር አያግደውም፡፡ ፈቃዱ ሆኖ መንገድ እንዲጠርግለት ወደደ እንጂ ቃል የተባለ ጌታችንም ድምፅ የተባለ ዮሐንስን ሳያስቀድም ወደ እኛ ከመምጣት የሚያግደው ምንም ነገር አልነበረም፡፡
የመጥምቁ ዮሐንስ ድምፅነት በምድረ በዳ ብቻ አልነበረም፡፡ ተጸንሶ ሳለ የድንግል ማርያም ስትመጣ ሰምቶ በመዝለሉ እናቱን ‹በታላቅ ድምፅ ጮኻ› እንድትመሰክር አንድ ምክንያት የሆነው ዮሐንስ በተወለደበት ዕለትም ዲዳ ሆኖ ለቆየው ለአባቱ ለዘካርያስ ድምፅ ሆኖለት ነበር፡፡ ‹‹የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ ወነድ ልጅም ወለደች፡፡ ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው፡፡ በስምንተኛው ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ፡፡ እናቱ ግን መልሳ አይሆንም ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች፡፡ እነርሱም ፡- ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሉአት፡፡ አባቱንም ማን ሊባል እንደሚወድ ጠቀሱት፡፡ ብራናም ለምኖ፡- ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ፡፡ [ገና ከመወለዱ ገድሉ በብራና መጻፍ የጀመረለት ጻድቅ ማለት ዮሐንስ ነው መቼም] ሁሉም አደነቁ ፤ ያን ጊዜም አፉ ተከፈተ ምላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ሉቃ. 1፡57-64) አባቱ ስሙን ሲጽፍ ብቻ አንደበቱን የፈታለት ድምፅ የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ ስሙን ጠርተን የምንዘክረውን አንደበታችንን ለጸሎትና ምስጋና ይክፈትልን፡፡
ዮሐንስ ሚዜ ፤ ጌታ ሙሽራ
በአንድ ወቅት ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስ እንደተለመደው ጥያቄ ቀረበለት፡፡ የጥያቄው መነሻ በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል የተነሣ ክርክር ነበር፡፡ የጌታችን ደቀ መዛሙርት ሲያጠምቁና ብዙ ሰው ሲከተላቸው ተመልክተው የተቆጡት የዮሐንስ ተማሪዎች ከአይሁድ ጋር በማንጻት (በንስሓ ጥምቀት) ዙሪያ ተከራከሩ፡፡ አይሁድ ከዮሐንስ ተማሪዎች ጋር የተሟገቱት ጌታችን በደቀ መዛሙርቱ በኩል እያጠመቀ መሆኑን ወድደው ሳይሆን በጌታ ሐዋርያትና በዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ጠብ እንዲፈጠር ለማድረግ ነበር፡፡
በመጨረሻም የመጥምቁ ተማሪዎች ነገሩን ለማጣራት ወደ መምህራቸው ወደ ዮሐንስ መጡ፡፡ የክሳቸው ጭብጥም ‹‹መምህር ሆይ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርክለት እነሆ እርሱ ያጠምቃል ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ›› የሚል የቁጣ ንግግር ነበር፡፡ በእነርሱ አስተሳሰብ በዮሐንስ እጅ በትሕትና ሲጠመቅ ያዩትን ጌታ ከአጥማቂው ዮሐንስ አሳንሰው እንደ አንድ ደቀ መዝሙር ቆጥረውት ነበር፡፡ ከዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አንዳንዶቹ የራሱን የዮሐንስን ምስክርነት ጭምር ሳይቀበሉ ጌታችን ካረገም በኋላ የዮሐንስ ጥምቀት ብቻ እንደተጠመቁ የቆዩ ሰዎች ነበሩ፡፡ (ሐዋ.19፡2)
ቅዱስ ዮሐንስም ለተማሪዎቹ ጥያቄ እንዲህ ሲል መለሰ ፡- ‹‹እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ነገር ግን ከእርሱ በፊት ተልኬያለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩኛላችሁ፡፡ ሙሽራዪቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው ፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምፅ እጅግ ደስ ይለዋል፡፡ እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ›› አላቸው፡፡ ተከታዮቹ እርሱን ከፍ ከፍ እያደረጉት ቢመጡም ፣ ‹ከአንተ ሌላ መምህር አናውቅም› ሊሉት ቢሞክሩም ባሕታዊ ዮሐንስ ግን በተከታዮቹ አለንልህ ባይነት ሳይታለል የአምላኩን ክብር አስቀድሞ ‹‹እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል›› አለ፡፡ በዚህ ሥፍራ ደግሞ መጥምቁ ራሱን ሚዜ አምላኩን ደግሞ ሙሽራ ብሎ ጠራ፡፡
እውነት ነው ፤ ጌታችን ሙሽራ ይባላል፡፡ ‹‹እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል እንደ አርበኛ በመንገዱ ለመሮጥ ደስ ይለዋል፡፡ አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው›› ይላል፡፡ (መዝ. 18፡5) ጌታችን ራሱም ‹‹ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን?›› ‹‹መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ ዐሥር ቆነጃጂትን ትመስላለች›› በማለት ሙሽራ እንደሆነ ነግሮናል፡፡ (ማቴ. 8፡15 ፣ 25፡1)

በአይሁድ ልማድ ሚዜ ሙሽራዪቱን ተንከባክቦ ፣ ለሰባቱ የሰርግ ቀናት ማንም እንዳይተናኮላት ጠብቆ ከሙሽራው ጋር የማገናኘት አለበት፡፡ በሚዜ የተመሰሉ የጌታችን ደቀ መዛሙርትም በሙሽራዪቱ የተመሰሉ ምእመናንን ከዲያቢሎስ መተናኮል በሰባት ቀን በተመሰለው በፍጹም ትምህርታቸው ጠብቀው ከሙሽራው ክርስቶስ ጋር የማገናኘት ሓላፊነት አለባቸው፡፡ ይህንን የሚያስረዳን የቅዱስ ጳውሎስ ንግግር ነው ፡- ‹‹እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና ፤ ነገር ግን ሰይጣን በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ›› (2ቆሮ. 11፡2)
በሥርዓቱ መሠረት ሚዜው ሙሽራይቱን ለሙሽራው ሳያስረክብ ቢቀር አደራ የበላ ይሆናል፡፡ ሥራውን ፈጽሞ ለሙሽራው ሙሽራዪቱን ሲያስረክብ ግን ደስ ያሰኛል፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ አደራውን ጠባቂ ነበርና ምእመናን ወደ ጌታችን ሲሔዱ ፣ ሙሽራዪቱ ከሙሽራው ጋር ሲገናኙ በማየቱ ተደስቶ ‹‹ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው ፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምፅ ደስ ይለዋል ፤ እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ›› ሲል ተናገረ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ የተማሪዎቹ ቁጥራቸው በመቀነሱ ፣ ተከታዮቹም ከእርሱ በመራቃቸው የተደሰተ የመጀመሪያው ሰባኪ ሆነ፡፡ የትኛው ሰባኪ ነው ሕዝቡ ጥሎት ሲሔድ ‹ደስታዬ ተፈጸመ› የሚለው? የዮሐንስ ትሕትና እንዴት ያለ ነው? ‹‹እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባኛል›› ብሎም ነፍሳትን ለጌታው አስረከበ፡፡ እውነቱን ነው! ፀሐይ ከወጣ ወዲያ የጨረቃ ብርሃን ለምን ያስፈልጋል? ሙሽራው ከሙሽራዪቱ ጋር ከተገናኙ ወዲያ ሚዜው ምን ይሠራል? ‹‹ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊለን›› የወደድነው መብራታችን ዮሐንስ እውነተኛው ብርሃን ሲመጣ ሥፍራውን ለቀቀ፡፡
መንገድ ጠራጊነት እንዲህ ነው፡፡ መንገድን የሚጠርግ ሰው መንገዱን ጠርጎ ለመንገደኛው ይተዋል እንጂ ሊጠርግ በተሠጠው ጎዳና ላይ ለራሱ ቤት ካልሠራሁ አይልም፡፡ በመንገድ መጥረግ ሥራው ላይ ያፈራቸው ወዳጆቹ አትለየን ቢሉት እንኳን መንገድ ጠርጎ መልቀቁ የግድ ነው፡፡ የዮሐንስን ጌታ የምናገለግል አገልጋዮች ሁላችንም ምእመናንን ከፈጣሪ አገናኝቶ ዞር ማለት እንጂ ራስን እያሳዩ መንገድ በመጥረግ ፈንታ መንገድ መዝጋት እንደሌለብን ከዮሐንስ እንማራለን፡፡ ጌታ አህያውና ውርጫይቱን ፈታችሁ አምጡልኝ አለ እንጂ እናንተ ጋልቧቸው አላለም፡፡ የአገልጋይ ሥራው ፈትቶ ለጌታ ማስረከብ ብቻ ነው፡፡
ዮሐንስ ትሑትና ክቡር
መጥምቁ ዮሐንስ ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር አፉ በትሕትና ተሳስሮበት ነበር፡፡ ወንጌላዊያኑ የዮሐንስን ጥልቅ ትሕትና መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው በአንድ ሥፍራ የተናገረውን ንግግር በተለያየ መንገድ በመጻፍ የዮሐንስን ታላቅ ትሕትና ተከፋፍለው ተሸክመውታል፡፡
‹‹ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል›› ማር. 1፡7
‹‹ነገር ግን የጫማውን ጠፍር መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል›› ሉቃ. 3፡16
‹‹ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይበረታል›› ማቴ. 3፡11
አንድን ጫማ ለመሸከም መጀመሪያ መፍታት ያስፈልጋል ፤ ለመፍታት ደግሞ ማጎንበስ ያስፈልጋል፡፡ የዮሐንስ ልብ ምንኛ በትሕትና ተጨነቀ ‹‹ጫማውን መሸከም አይገባኝም… ኸረ የምን መሸከም? መፍታትም ቢሆን አይገባኝም ፤ ኸረ የምን መፍታት ለመፍታት ራሱ ማጎንበስ እንኳን አይገባኝም›› እያለ ሲያመነታ በወንጌላቱ መነፅር ይታያል፡፡
ይህንን የዮሐንስን ትሕትና ‹ለትሑታን ጸጋን የሚሠጥ ጌታ› በከንቱ አላስቀረበትም ፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ጫማውን ልፈታ አይገባኝም ላለው ለዮሐንስ ጌታ እጆቹን ከራሱ በላይ ከፍ አድርጎ ያጠምቀው ዘንድ ፈቀደለት፡፡
ሳይወለድ ጀምሮ ሞቶ ያላረፈ ሰባኪ
ዮሐንስ የሰባኪነት አገልግሎቱን የጀመረው ገና በእናቱ ማኅፀን እያለ ነበር፡፡ ለመወለድ ገና ሦስት ወራት የቀሩት ቢሆንም እንኳን የድንግል ማርያምን የሰላምታ ድምፅ በሰማ ጊዜ ዮሐንስ እስኪወጣ መታገሥ አቃተው፡፡ የእርስዋን ድምፅ የሰማ ሰው በደስታ እንደሚዘልል በተግባር ለማሳየት ዮሐንስ ተወልዶ ፊደል መማርና የመጽሐፍ ጥቅስ ማወቅ አላስፈለገውም፡፡ ለጌታ እናትና ለጸነሰችው ፈጣሪዋ ዮሐንስ የእናቱን ማኅፀን ቅኔ ማሕሌት አድርጎ አሸበሸበ፡፡ ‹መወለድ ቋንቋ ነው› የሚለው ለዮሐንስ የበለጠ ይስማማል ፤ ተወልዶ ጌታን ከእናቱ ጋር ማክበር ከማይችል ሰው ያልተወለደው ዮሐንስ ይሻላል፡፡
የዮሐንስ ስብከት ከመወለዱ በፊት ተጀምሮ በሞቱም አልተገደበም፡፡ ገድሉ በሰይፍ የተቆረጠች አንገቱ በተአምራት ዞራ ማስተማርዋን ይገልጻል፡፡ ይህ ተአምር ከአእምሮው በላይ ለሆነበት ሰው ደግሞ የዮሐንስን ከሞት በኋላ ሰባኪነት ከሔሮድስ እንረዳለን፡፡ ዮሐንስን በግፍ ያስገደለው ሔሮድስ ዮሐንስ ከሞተም በኋላ የመጥምቁ ትምህርት እንቅልፍ ያሳጣው ነበር፡፡ ‹ዮሐንስ ከሞት ተነሥቷል› እያለ የጌታን ዝና ሰምቶ ይረበሽ ነበር፡፡ ይህ የሆነው በግፍ ያስገደለው የሰባኪው የዮሐንስ ትምህርት በዚህ ጨካኝ ንጉሥ ሕሊና እየተመላለሰ ያስጨንቀው ስለነበር ነው፡፡ ሰባኪ ቆሞ ጮኾ እየሰበከ ባለበት ቅጽበት እንኳን የሰዎችን ልብ ማሸነፍ ባልቻለበት ዘመን ዮሐንስ ሞቶም ስብከቱ ከሕሊና አለመጥፋቱ ምንኛ ይደንቃል? በረከቱ ከእኛ ጋር ትሁን!
መስከረም 2004 ዓ ም ተጻፈ
(አበረታች መድኃኒት ከሚለው የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ አዲስ መጽሐፍ የተወሰደ)

❤️ሁሉም ነገር ለበጎ ነው❤️
///////////////////////////////
አንድ ንጉስ ከአሽከሩ ጋር ለአደን ወደ ጫካ ያመራል። ዙርያውን ወጥመድ በማጥመድ ላይ ሳሉ አንደኛው ወጥመድ የንጉሱን እጅ ላይ አርፎ እጁን ያሳጠዋል። ንጉሱም በመጮህ ላይ ሳለ አሽከሩ የደማውን እጁን በጨርቅ እየጠቀለለ "ንጉስ ሆይ አይዞህ ለበጎ ነው ይለዋል" ንጉሱም እጅግ ይበሳጭና የእኔ እጅ መቆረጥን ለበጎ ነው ትላለህ ብሎ ያሳስረዋል።
ከብዙ ቀን ቆይታ በኋላ ንጉሱ ለብቻው ወደ አደን ሲሄድ ሰው ገድለው ለአማልክቶቻቸው መስዋዕት የሚያቀርቡ ሽፍቶች ይይዙታል። ሊሰውትም ሲሉ ንጉሱ እጁ የተቆረጠ ነውና በባህላቸውም መሠረት አካለ ጎዶሎ ሰው ለመስዋዕት አይቀርብምና ይተውታል።
ንጉሱም ወዳሰረው አሽከር ሄዶ "ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ያልከው እውነት ነበር ብሎ ታሪኩን ያጫውተዋል። ባደረገውም ተጸጽቶ "ይቅርታ አድርግልኝ አንተን ማሰሬ ልክ አደለም" ይለዋል
አሽከሩም "ንጉስ ሆይ አንተም እኔን ማሰርህ ለበጎ ነው ባታስረኝ ኖሮ ካንተ ጋር አብሬ እሄድ ነበር። አንተን ሲለቁህ እኔን ደግሞ ሙሉ አካል ነው ብለው ይሰዉኝ ነበር" አለው።
⭕️◻️⭕️◻️⭕️◻️⭕️◻️⭕️◻️⭕️◻️⭕️◻️
" እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28)
ብናገኝ፣ ብናጣ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ከማማረራችን በፊት የእግዚአብሔርን በጎ ምላሽ እንጠብቅ። እግዚአብሔር ቢዘገይም የሚቀድመው የለም ከችግራችን በላይ እግዚአብሔር ይበልጣል።
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር

ሚስቶች ሆይ፥ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ተገዙ።
ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው።
ልጆች ሆይ፥ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።
አባቶች ሆይ፥ ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጩአቸው።
ባሪያዎች ሆይ፥ በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፥ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፥ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።
ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥
ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና። የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና።
የሚበድልም የበደለውን በብድራት ይቀበላል፥ ለሰው ፊትም አድልዎ የለም።"
ቆላስ. 3÷18-25

“አንድ ምንም እውቀቱና ልምዱ የሌለው ሰው ዝም ብሎ መሬት ስለ ቆፈረ ብቻ ወርቅ አያገኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምንም ረብሕና ጥቅም የሌለውን ድካም ያተርፋል እንጂ፡፡ ባስ ካለም የቆፈረው ጉድጓድ ተደርምሶበት ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚነበብና እንዴት መረዳት እንዳለበት ያለወቀ ሰውም ይህን ሰው ይመስላል፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መልካም ዕለተ ሰንበት ⛪️⛪️⛪️
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መልካም ዕለተ ሰንበት ⛪️⛪️⛪️
ኩሉ ነገር ዝኸውን ንፅቡቅ ምኽንያት እዩ::
ኩሉ ሰብ ከንብቦ ዝግባእ..
.
. [ለካ ንኣደስ ኩሉ እዩ ዘፍቅራ]
.
.
..ንኣዴና ንፎቱ ላይክ፣ሼር ንግበር ሪኢቶና ንሃብ....
.
.
.
ቀደም እዩ ሓደ መንእሰይ ንስራሕ ናብካልእ ከባቢ ይከይድሞ
ሚነዋለ ሰሪሑ ዘጠራቆሞ 400 ቅርሺ ሓንቲ ቅርሺ ንባዕሉ
ከይኣትረፈ ንኣዴኡ ንኣውደኣመት መውዓሊ ዝከውን ኣብ ፖስታ
ኣሺጉ ምስቲ ቅርሺ እውን ናይ ሰላምታ ደብዳቤ ገይሩ ክልእኮ
ናብ ፖስታ ቤት እናከደ እናሃለወ ሌባ ነታ ፓስታ ይሰርቆ።
.
ደሓር ብጣዕሚ ይሓዝን ርእሱ ደፊኡ ድማ ፊቅፊቅ ኢሉ
ይበኪ።ምክንያቱ ካልእ ቅርሺ ከይሰደላ ምንም የቡሉን።
.
.ብድሕሪኡ ኣውደኣመት ምስሓለፈ ካብ ኣዲኡ ደብዳቤ
ይመፀሉ። እቲ ደብዳቤ፦
.
...ወደዋይ መዓረይ ፀጋጥዕናካ ከመይ ኣለካለይ ኣነ ኣዴካ
ከብድካ ገዲፍካ ብዝሰደድካለይ 600 ቅርሺ ዝደለኩዎ ገዚአ
ደስ ኢሉኒ ዊዒለ ኣለኩ። ዓይኒ ንዓይኒ ክሳዕ ዘራአየና ኩሎም
መላእክቲ ምሳካ ይኩኑ ...ይብል።
.
.ደሓር ብጣዕሚ ይገርሞ እዙይ ከመይ ክከውን ኪኢሉ
ይብል።እዙይ ናይ ኣደይ ደብዳቤ ኣይኮነን ይብልሞ ግን ድማ ናይ
ኣዲኡ ጉርዲ ፎቶ እንየዎ።
.
ደሓር እናተገረመ እናሃለወ ቅንይ ኢሉ እንደገና ካልእ ደብዳቤ
ይመፀሉ።ናይቲ ደብዳቤ ትሕዝቶ ከምዙይ ይብል፦
.
...ንካልእ ተዝከውን ምሕረት ኣይምገበርኩን ነይረ ንኣደ ዝጭክን
ልቢ ግና የብለይን።ናብቲ ናትካ 400 ቅርሺ 200 ናይ ባእለይ
ወሲከ ንኣዴካ ሊኢከላ ኣለኩ።በጃካ ንስካ ግን ጠንኪርካ ሰሪሕ ካ
ንኣዴካ ኣሀጉሳ ኢካ...
.
..ናትካ ሌባ ..ይብል።
.
.
ነዊሕ ዕ ድመን ጥዕናን ንኣዴታትና!!
.
...............ኣሜን.................

"ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡
እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርጉዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡
ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??”
ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡
ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል...የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ፡፡”
⭕️🛑⭕️🛑⭕️🛑⭕️🛑⭕️🛑⭕️🛑
ሰዎች ለጥያቄዎቻቸዉና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ለሁሉም ጊዜ ና ቦታ አለው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨♦♥♦፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨♦♥♦፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሁለት ሰዎች ወደ ገዳም ይሄዱና ስለአንድ ጉዳይ አብረው ይጸልያሉ። አንደኛው ጸሎቱ
ተመለሰለት፣ አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ጸሎቱ ያልተመለሰለት ሰው፡- “ጌታ
ሆይ ሁለታችንም እኩል ጸለይን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ የከለከልከኝ ለምንድን ነው?”
አለው።
ፈጣሪም፡- “ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ትጠፋለህ” አለው።
እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን
በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሣቱም ሁለቱም ለፍቅር ነውና
ስለሆነልን ስለሚሆንልንና ስላልሆነልን ነገር ሁሉ ተመስገን ማለትን አንርሳ፡፡
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ተመለሰለት፣ አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ጸሎቱ ያልተመለሰለት ሰው፡- “ጌታ
ሆይ ሁለታችንም እኩል ጸለይን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ የከለከልከኝ ለምንድን ነው?”
አለው።
ፈጣሪም፡- “ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ትጠፋለህ” አለው።
እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን
በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሣቱም ሁለቱም ለፍቅር ነውና
ስለሆነልን ስለሚሆንልንና ስላልሆነልን ነገር ሁሉ ተመስገን ማለትን አንርሳ፡፡
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue
ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
#ሎመዓንቲ_ታሪኽ_ክንሰርሕ_ኢና
Share. Share. Share
ኹላትና ብሓደ! ናይ ኣዋርሕ ትልምና፣ ናይ ሰሙናት ኣኼባታትና፣ ኣብ ፌስቡክ ከም ዕቡድ ሰብ ዝነባሕናሉ፣ በቢዕለቱ ንጎይታ መስቀል ዝፀሓፍናሉን ፕሮፋይልና ዝቐየርናሉን ነገር ብተግባር ንፍፅመሉ እዩ። ናይ መቐለ አባላት ቤት ትምህርቲ ሰንበትን ንእምነትና ተገደስቲ መናእሰይን ታሪኽ ክንሰርሕ ኢና። #ማንም_ሰብ ቅድሚ 10:30 ናብ ጮምዓ #ከይድይብ! ምስ መዘምራንን ካህናትን ካብ 7:00 ካበየ ቤ.ክ ብምውፃእ እናዘመርና 10:30 ጮምዓ ክንኣቱ ኢና። ብዝማሬ ምድረ ሰማይ ድብልቕልቕ ክነብሎ፣ መስቀል ጎይታና ኣብ ዓይኒ ኩሉ ሰብ ልዕል ክነብሎ ኢና። "መስቀል ብመዝሙር እምበር ብደርፊ ኣይኽበርን" ዝብል ዓበይቲ ባነራር ሒዝና ናብ ርእሲ ጮምዓ ንወፅእ ኢና!
ኣብ ልዕሊ ጮምዓ ንዝፀንሐና አጋንንቲዊ ደርፍን ጓይላን ድማ በቲ ዝማሬና እናሰላዕና ብዕልልታ እናቖረፅና ንጮምዓ ክንወርሶ ኢና። ጮምዓ ቦታ ክሳብ ዝፀብብ ብዘማርያንን መናእሰይን ዓብለቕለቕ ክብል እዩ። #ሓደራ! ክትደርፍን ክትስዕስዕን እንተመፂኻ እቲ ዝመፅእ ሰልፊ መዘምራን ሓያል እዩሞ ፀግዕኻ ሓዝ። ኣይሰማዕኹን ከይትብል! ንዝሞተልካ ጎይታ ክትዝምር እንተመፂእኻ ግና ናብቲ ናይ ዝማሬ ማዕበል ተወሰኽ! ድሕሪ 10:30 ናይ መላእክቲ ዝማሬ እምበር ናይ አጋንንቲ ደርፊ፣ ናይ ያሬድ ሽብሸባ እምበር ናይ ሰይጣን ዕብዳን ኣይህሉን። ጉባኤና ተሳቲፍና መስወልንል ኣኽቢርና ኣብርሂናን ሓሙስ ድማ እቲ ታሪኽ ብዕዙዝ መልክዑ ኣፍ ብዘኽፍት መንገዲ #ክንደግሞ_ኢና!
Share ብምግባር ኣዋጅ ንኣውጅ! ንዘይሰምዑ ነስምዕ!
©Binyam ZeChristos መስከረም 16 - 2011

ወርኃ ጽጌ -
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕግና ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡
በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡
የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡

ሥርዓተ ማኅሌት ዘዘመነ ጽጌ "መስከረም ፳፯"
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
ዚቅ
እግዚኦ በሰማይ ሣሕልከ፤ ወበደመናትኒ አንተ አርአይከ ኃይለከ፤ ወበምድርኒ ዘሠናየ ጽጌ ወጥዑመ ፍሬ አንተ አርአይከ፤ ወበቀራንዮ አንተ አርአይከ ትህትናከ በዲበ ዕፀ መስቀል።
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ሐፁር የዓውዳ ወጽጌረዳ፤ ብእሲ ተወልደ በውስቴታ ንጉሠ ፳ኤል፤ አልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ ንጉሠ ፳ኤል፤ ህየ ማኅደሩ ለልዑል ንጉሠ ፳ኤል፤ መድኃኔዓለም እግዚአብሔር ኃደረ ላዕሌሃ፤ ኪያሃ ዘሠምረ ሀገረ።
ማኅሌተ ጽጌ
ጽጌ አስተርአየ ሠሪፆ እምአፅሙ፤ ለዘአምኀኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፤ ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ መዐዛ ጣዕሙ፤ ለተአምርኪ አኀሊ እሙ፤ ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ።
ወረብ
መዓዛ ጣዕሙ ለተአምርኪ ሶበ ሐወዘኒ/፪/
ወበእንተዝ ማርያም አኀሊ ለተአምርኪ/፪/
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ናሁ አስተርአየ ጽጌ፤ መርዓቱኒ ትቤ ወልድ እኁየ ይምዕዝ ከርቤ፤ ናሁ አስተርአየ ጽጌ፤ ዕንባቆም ነቢይ ስነ ምግባሩ ለወልድ አንከርኩ ይቤ፤ ናሁ አስተርአየ ጽጌ፤ ንጉሠ ሰላም ክርስቶስ ዓቢይ ልዕልናከ፤ ወመንክር ስብሐቲከ፤ ለዕረፍት ሰንበተ ሠራዕከ።
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።
ወረብ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ ሠናይትየ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ/፪/
ዚቅ
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ በአምሳለ ወርቅ፤ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ ብርሃንኪ፤ ውእቱ ሰላምኪ።
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።
ወረብ
"ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ"/፪/ እምዕንቌ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ/፪/
ዚቅ
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል ጽሑፍ በትእምርት መስቀል።
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
አክሊል ዘእምጳዝዮን ተደለወ፤ ጌራ ባሕርይ ወቀጸላ ወርቅ ጽሩይ በቤተልሄም ተወልደ እምድንግል፤ ብሥራትክሙ መሃይምናን፤ እምአፈ ዮሐንስ ሥርግው ተቀስም አፈው፤ ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማዕከለ አኃው።
ሰቆቃወ ድንግል
በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ህፀተ ግፃዌ ዘአልቦ፤ ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤ ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንበቦ፤ ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ሶበ በኲለሄ ረከቦ፤ ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ።
ወረብ
"ከማሃ ኃዘን"/፪/ ወተሰዶ ኃዘን/፪/
ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ ዓይነ ልብ/፪/
ዚቅ እወ አማን እምውሉደ ሰብእ አልቦ ምንዳቤ ወግፍዕ ዘከማኪ በውስተ ኲሉ ዘረከቦ።
መዝሙር
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
ትዌድሶ መርዓት፤ እንዘ ትብል ነዓ ወልድ እኁየ ንፃእ ኃቅለ፤ ትዌድሶ መርዓት፤ ንርአይ ለእመ ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፤ ትዌድሶ መርዓት፤ አሠርገወ ሰማየ በከዋክብት ወምድርኒ በስነ ጽጌያት፤ ትዌድሶ መርዓት፤ እስመ ውእቱ ወልድ ዋሕድ እግዚአ ለሰንበት፤ ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ፤ ወልድ እኁየ ቃልከ አዳም።
የኪዳን ሰላም

🌻 መልካም የምስጋና ሌሊት 🌻