የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
የበለስ ቅጠል ሰፊና ደስ የምታሰኝ ናት፤ ወደ ጥፋት የምትወስደው የኃጢአት መንገድም ሰፊ በር ናት፡፡ የበለስ ፍሬ ሲበሏትና ሲያላምጧት ጣፋጭ ናት፤ ኃጢአትም ሲሠሯት ደስ ታሰኛለች፡፡ ከሠሯት በኋላ ግን (እንደ በለሲቱ) መከራን ታመጣለች፡፡ በሚሠሯት ጊዜ ጣፋጭ ከሠሯት በኋላ ግን መራር ናትና እርሷን ከመሥራት ሽሽ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ውርጃ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ

ምድሪቱ (የሴቲቱ ማኅፀን) ዘር ከዘራንባት በኃላ ፍሬ እንዳታፈራ የምናደርገው ስለ ምንድን ነው? ውርጃን የምናካሒደው ስለ ምንድን ነው? እናንተ ዘማውያን ሆይ! ዝሙት መፈጸማችሁ ሳይበቃ ሰውን መግደል ትጨምሩበታላችሁን? እንግዲህ ስካር እንደ ምን ሴተኛ አዳሪን እንደሚያደርግ፣ ሴተኛ አዳሪነትም ዘማዊ፣ ዝሙትም እንደ ምን ነፍሰ ገዳይ እንደሚያደርግ ታስተውላላችሁን? ይህን ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም ምክንያቱም ይህን ሕፃን ከተወለደ በኃላ ከቤት አስወጥተን አይደለም ያባረርነው፤ እንዳይወለድ ከለከልነው እንጂ ወዮ! ስለምን የእግዚአብሔርን ስጦታ ታቃልላላችሁ? ስለምን ሕጉን ትተላለፋላችሁ? ስለምን ርጉም የሆነን ተግባርን እንደ በረከት ትቆጥሩታላችሁ? ስለምን እግዚአብሔር ሰውን ለመፍጠር ያዘጋጀውን መንገድ መግደያ ታደርጉታላችሁ? ስለምን ልጅን አቅፋ እንድትስም የተፈጠረችውን ሴት ነፍሰ ገዳይ እንድትሆን ታደርጓታላችሁ? እህቴ ሆይ! ፍቅረ ንዋይ ዐይንሽን አሳውሮት፣ ዳግመኛም በፍትወት ከሚመስሉሽ ጋር ዝሙትን ለመሥራት ስትዪ ፍምን በራስሽ ላይ አታከማቺ ወንድሜ ሆይ! ምንም እንኳን ይህን አሰቃቂ ግድያ የምትፈጽመው እርሷ ብትሆንም አንተም ከእርሷ ጋር ተባባሪ ነህ።
++++++++++++++++ Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
++++++++++++++++
ብጹዕ_አቡነ_ሰላማ_ከሣቴብርሃን
ስሞም ፍሬምናጦስ እዩ! ፅርዓዊ/ግሪካዊ ኮይኖም ኣቡኦም ሜሮጵዮስ (መረጵዮን) ፍሉጥ ነጋዳይ ኮይኑ ኣብ ከባቢ ፫፻፴ ዓ.ም. ብሥራሕ ንግዲ ናብ ከባቢና ምስ ክልተ ደቁ (ፍሬምናጦስን ኤዴስዮስን) ብመርከብ ኣቢሉ ኣብ ዝተንቀሳቐሰሉ ኣብ ወደብ ኣዱሊስ በጺሑ። ነገር ግን ከተርቲ ሸፋቱ ሓደጋ አብፅሑሉሞ ሞተ። ነቶም 2 ደቁ ግና ሓለፍቲ መንገዲ ኣርኪቦም ኣናገፍዎም። ናብ 1ይ # አልዓሜዳ (ታዜር) ንጉሠ አክሱም ድማ ወሰድዎም። ንጉስ ኣብ ቤተ መንግሥቱ ኸዓ ኣዕቖቢዎም እኳ እንተነበረ ብዙሕ ከይጸንሐ ኢዛናን ሲዛናን ዝበሃሉ ክልተ ንኣሽቱ ደቁ ገዲፉ ሞተ። እዚኦም ደቁ ኸዓ ኣብ እንበረም ዝበሃል ሊቀ ካህናት ኦሪት ንባብን መጻሕፍትን ይመሃሩ ዝነበሩ እዮም። ኣዴኦም # አሕየዋ (ሶፍያ) ድማ ደቃ ክሳብ ዝዓብዩ፣ ንኤድስዮስ ናይ ኣዛዝነትን ሓላፊ ምስላፍን (መጋቤ ቤተ ቀጢን) ሥራሕ ክወሃቦ ከሎ ንፍሬምናጦስ ኸኣ ሓላፊ ቤተ መጻሕፍትን መምህር ደቃን (ዓቃቤ ሕግ ወጸሐፌ አኵሱም) ገበረቶ። ፍሬመናጦስ ግና ብርሃን ወንጌል ዝተረደኦ ስለዝነበረ፣ ነቶም ካህናተ ኦሪት በብቝሩብ ብርሃነ ወንጌል የብርሃሎም ነበረ። ዋላኳ ብትምህርቱ ኵሎም ኦርሕጉሳት ተነበሩ፤ ጥምቀት፣ ቍርባንን ክህነትን ስለዘይነበቶም ግና ሓጐሶም ምሉእነት ኣይነበሮን።
...
ድሕሪ ዝተወሰነ ዓመታት ግና ኢዛና ዘውዲ ኣቡኡ ምስ ደፈአ፤ ኤዴስዮስ ናብ ሃገሩ ጢሮስ ተመልሰ። ፍሬምናጦስ ምስ ንጉሥን ኣብኡ ምስ ዝነበሩ ካህናተ ኦሪትን ብዝገበሮ ምርድዳእ ናይ ክርስትና ጥምቀትን ቁርባንን ከምኡ 'ውን ክህነት ዝህብ ጳጳስ ካብ ግብፂ ንክለኣኸ ናብ እስክንድርያ ተላእኸ። ኣብ ግብፂ ድማ እቶ ዓብዪ ሊቅን ቅዱስ አቡነ አትናቴዎስ እዩ ነይሩ። አርዮስ ዝተወገዘሉ ጉባኤ ኑቅያ ምስ ሓለፈ፣ "ካባኺ ንላዕሊ ቋንቊኦምን ባህሎምን ዝፈለጥ ስለዘየለ ንስኻ ጳጳስ ክትኾኖም ይግባእ" ኢሉ ንፍሬመናጦስ 5 ዓመት አምሂሩን ስልጣነ ክህነት ሂቡን " # ሊቀጳጳስ_ዘአክሱም " ኢሉ ሸይሙ ለኣኾ! ሕዝቢ ኢትዮጵያ (ኣኽሱም) ድማ ብዓብይ ደስታን ሓጎስን ምስ ተቀበልዎ "አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን" ኢሎም ስም አውፅእሉ! ብርሃን ዝኾነ ወንጌል ዘብርህ ሰላማዊ አቦ ንምባል እዩ! ድሕሪ ቁሩብ ጊዜ ድማ ንኢዛናን ሳይዛናን ብምምሃርን ንክጥመቁ ብምግባርን አብርሃ ወ አጽብሐ ኢሉ ስም ሃቦም! ብድሕሪኡ ካብ ትግራይ ሓሊፎም ሙሉእ ኢትዮጵያ ክሳብ ማእኸልን ክሳብ ደቢብ ኢትዮጵያን ክስሥብ ሸዋ ብምኻድ አምሂሮምን ሰቢኾምን እዮም! (ኣብ ሸዋ ኣብ ጥቃ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ዘሎ ዜጋመል ቤ.ክ ንሶም ከምዝሰርሕዎ ይንገር።)
...
አቡነ ሰላማ ኣብ መላእ ኢትዮጵያ ትምህርተ ሃይማኖት ብምስትምሃር፣ ስብከተ ወንጌል ብምስፍሕፋሕ፣ ካህናትን ዲያቆናት ብምሻም፣ አብያተ ክርስቲያናት ብምህናፅ፣ ምንኲስና ብምስፍሕፋሕ፣ መጻሕፍቲ ናብ ግዕዝ ብምትርጓም፣ ኣበ ነፍስን ኣበ ልገን ብምጅማር፣ ክልብ ኩሉ ንላዕሊ ድማ ንወንጌል ዝጓየ " # ማሕበረ_ጽዮን " ዝበሃል ማሕበር ብምምስራትን ቋንቋ ግዕዝ ንክዓቢ ብምግባርን ዓብዪ ግደ ዝነበሮም ቅዱስ ኣቦ እዮም! 26 ሓምለ ዕረፍቶም ኣብ ኦርቶዶክስ ቤ.ክ እንትኽበር፣ ኣብ ሮማውያን 27 ጥቅምቲ፣ ብግሪኻውያን ድማ 30 ሕዳር በዓሎም የኽብሩሎምን ይዝክርዎምን እዮም። ኣብ ተንቤም ብስሞም ኣብ ዝፅዋዕ ገዳሞም፣ ኣብ መቀለ ደብረ ሰላም ሚካኤል ብድሙቅ መልክዑ ይኽበር አሎ! በረኸቶም ይሓልወና!
"ሳምራዊቷ ሴት ውሃ አጠጭኝ ሲላትም የተጠማው
ውሃን ሳይሆን የእርሷን ነፍስ ነበር እርሷ ግን የተጠማው ምን እንደሆነሳታውቅ ፣ስለዘር ልዩነት
ለመከራከር ተነሳች። መቼም የእግዚአብሔር ን ስጧታና ውሃ አጠጡኝ የሚላቸው ማን እንደሆነ የማያውቁ ሁሉ ዘርኞች ናቸው። ከመድሐኔዓለም
ክርስቶስ ፊት ቆመውም እንኳን ዘር መቁጠራቸውን
አያቆሙም። እግዚአብሔር ግን የሚፈልገው የሰዎችን ነፍሳቸውን እንጂ ወደላይ ቢቆጠር ሄዶሄዶ
አንዱ አዳም ላይ የሚያርፈውን የዘር ሀረጋቸውን አይደለም። "
--- ሕማማት ----
"ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ "
የ"አባታችን ሆይ" ጸሎት አድምታ ትርጓሜ

ሐዋሪያት ወደ ጌታችን ቀርበው የምንጸልየውን ጸሎት አስተምረን አሉት። ጌታችንም "እናንተስ ስትጸልዩ የሰማይ አባታችን በሉኝ" በማለት ማንም ቢሆን ሲቆምና ሲቀመጥ ሲተኛና ሲነሣ ዘወትር ሊጸልየው የሚችለውን አጭር ጸሎት አስተማረ። ማቴዎስ 6÷9-14
ይኽም ጸሎት እንደ አባቶቻችን አስተምህሮ አድምታ ትርጓሜው አጠር ባለ መልኩ እንደሚከተለው ቀርቧል።

አባታችን ሆይ :-
ጌታችን ከግብርናተ ዲያብሎስ /ከዲያብሎስ ባርነት/ ነፃ እንዳወጣን: አጥተነው የነበረውን ልጅነት እንዳገኘን ሲያጠይቅ አቡነ /አባታችን/ በሉኝ አለ። ጌታ ሎሌውን መምህር ደቀመዝሙሩን ምን ቢወደው ያበላዋል ያጠጣዋል የልቡናውን ምስጢር ያጫውተዋል እንጂ ርስቱን አያወርሰውም። ርስቱን የሚያወርሰው ለልጁ ነው። እርሱ ግን ጌታችን እና አምላካችን ሲሆን የማታልፍ ርስት መንግሥተ ሰማያትን የሚያወርሰን ስለሆነ 'አቡነ' በሉኝ አለ። አባት ለወለደው ልጁ እዲራራ የሚራራልን ስለሆነ አቡነ በሉኝ አለ።

በሰማያት የምትኖር :-
እንዲህ ማለቱ ራሱን ከምድራዊ አባት ሲለይ ነው። ምድራዊ አባት ሲወልድ በግዙፍ ሲያሳድግ በግዙፍ ነው። ኋላም ሓላፊ ርስቱን ያወርሳል። እርሱ ግን ሲወልደን በረቂቅ ሲያሳድገን በረቂቅ ነው። ኋላም የማታልፍ ርስቱን መንግሥተ ሰማይን ያወርሰናል። በተጨማሪም ጌታ በሁሉ ምሉዕ ሲሆን ስለ ልዕልናው በሰማይ የምትኖር ይባላል። 1ኛጴጥ.1÷8-10 ራዕይ 21÷2-6።

ስምህ ይቀደስ:-
ይኽም "ስሜ መሐሪና ይቅር ባይ ነው።" ያልኸው ይጽናልን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ስምህን አመስግነው ቅድስናህን ተሳትፈው እንዲኖሩ እኛም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለን አመሰገንህ ቅድስናህን ተሳትፈን እንድንኖር አድርገን በሉ ሲለን ነው። ኢሳያስ 6÷3 ራዕይ 4÷8።

መንግሥትህ ትምጣ:-
መንግሥተ ሰማይ ትምጣልን ልጅነትን ትሰጠን በሉ ሲል ነው። እንዲህም ማለቱ መንግሥተ ሰማይ ከወዲያ ወዲህ የምትመጣ ከወዲህም ወዲያ የምትሄድ ሆና ሳይሆን ትገለጽልን በሉ ማለቱ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፈሪሳውያን ቀርበው " የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች? " ብለው በጠየቁ ጊዜ "የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም ከዚህ አለች ከዚያ የለችም አትባልም የእግዚአብሔር መንግሥት እንሆ በመካከላችሁ ናት" ብሏቸዋል። ሉቃስ 10÷20-21።

ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁ በምድር ትሁን :-
መላእክት ከሰማይ ሲያመሰግኑህ ፈቃድህ እንደ ሆነ እኛም በምድር ያለን ደቂቅ አዳም እናመስግንህ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን። ኋላ ሞተን ተነሥተን እናመስግንህ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን በሉ ሲል ነው። እንዲሁም አቤቱ ፈቃደ መዓትህን ትተህ ፈቃደ ምሕረትህን አድርግልን ብላችሁ ብትለምኑኝ አደርግላችኃለሁ ሲልም ነው።

የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ :-
በዚህ ዓለም ሳለን ለዕለት የሚሆነንን ምግብ ስጠን በሉ ሲል ነው። በሰማይ ያሉ መላእክት ስብሐተ እግዚአብሔር ተመግበው / በሰማይ አመስግነውህ ያው ምስጋናቸው ምግብ ሆኗቸው/ እንዲኖሩ እኛም በምድር እህል ምግባችንን አትንሣን ብላችሁ ብትለምኑኝ አልነሣችሁም ሲል ነው።

በደላችንን ይቅር በለን የበደሉንን ይቅር እንደምንል:-
ማረን ይቅር በለን ኀጢአታችንን አስተስርይልን በደላችንን ደምስስልን መተላለፋችንን ሁሉ ይቅር በለን ይቅርታን እናገኝ ዘንድ እኛም የበደሉንን ሁሉ ይቅር እንላለን ሲል ነው። ለዚህም ነው ጌታ "ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማይ አባታችሁ ደግሞ ይቅር ይላችኋል ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም" ብሏል። ማቴዎስ 6÷13-15። እንዲሁም "አበሳ" የዓመት ነው: " ጌጋዬ " / በደል / የዕለት ነው። አበሳ የዓመት ያለውም ነፍስ መግደል ቋንጃ መቁረጥ ቤት መስበርና ይኸንን የመሳሰለው ሁሉ ነው። ይኸን ያደረገም ጠላቱን ሲርበው ቢያበላ ሲጠማው ቢያጠጣው ሲታረዝ ቢያለብሰው በደለኛ ሲክሰው ዋስ ጠበቃ ቢሆነው ንስሐ ቢገባ ስለክፉ ሥራው ቢያዝን ቢጸጸት ቢያለቅስ ይድናል እንጂ ያለዚያስ አይድንም። ፊያታዊ ዘየማን ሲድን ፊያታዊ ዘጸጋም አለመዳኑ ንስሐ ባለመግባቱ ነው። ጌጋየ ዕለት ያለው ደግሞ ሰው ሆኖ በተለያየ ምክንያት መጣላት መጋጨት አይቀርምና ቂም በቀል ሳይዙ ዕለቱን ስለ እግዚአብሔር ይቅር መባባል ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያው "በቁጣችሁ ፀሐይ አይግባ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት" ያለው። ኤፌሶን 4÷27

አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን :-
ከክፉ አድነን ወደ ኀጢአት ወደ ክህደት ወደ መከራ ወደ ገሃነም አታግባን ከዚህ ሁሉ አድነን እንጂ በሉኝ ሲል ነው።

መንግሥትህ ያንተ ናትና:-
መንግሥተ ሰማያት ያንተ ገንዘብ ናትና በሉኝ ሲል ነው።

ኃይል ምስጋናም ለዘላለሙ:-
ከሃሊነት ጌትነት ለዘላለሙ ገንዘብህ ናትና አሜን በእውነት በሉኝ ሲል ነው። የእግዚአብሔር ኃይል የባሕርይ በመሆኑም ነው ጻድቁ ኢዮብ "ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደሆንህ አሳብህም ይከለከል ዘንድ እንደማይችል አወቅሁ" በማለት የገለጸው ኢዮብ 42÷2

#ማጠቃለያ፡-
በዚህ የጸሎት ክፍል ውስጥ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ 81(ሰማንያ አሀዱ) መጽሐፍት የተገኙ አምስት ቁም ነገሮችን አስተምሯል እነሱም :-
1. ሃይማኖት
2. ተስፋ
3. ፍቅር
4. ትሕትና
5. ጸሎት ናቸው።

#በዘሪሁን_እሸቱ
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
"ፍልሰታ መጣች"
"ሕጻኑም ወጣቱም ወንዱም ሴቱም ዕድሜው የገፋውም ሁሉም በፍቅር የሚጾሟት፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድዔትና በረከት የሚታፈስባት፣ ፍቅረ እግዚአብሔር በሰው ልቡና የሚሰለጥንባት ፈሪሃ እግዚአብሔር የሚያይልባት፣ የንሰሐና የምህረት ጾም ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡ በዓለም ያሉ ወደ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ያሉ ወደ ገዳማት የሚገሰግሱባት ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡"

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
በጾም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን በሌላ ጊዜ ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡፡
እነርሱም፡-
✞ ክፉ ከመናገር መከልከልን
✞ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
✞ እንደልምድ አደርጋችሁ ከያዛቸሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቁጽረታ (ጽንሰታ) ለማርያም
ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ
የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት
በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ
ናትና እንዲህ ይላሉ::

"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ::....ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው:
የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው::"
(መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)

ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ
የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል:: የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው
ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር::
ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ
ነበር:: ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ
እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና
ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ
አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ
ነውና ተስፋ አልቆረጡም::
የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን
አደረገላቸው:: አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች::

"እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ
የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ
ስትደርስ አየ:: እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ
እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ
እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::
በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ
ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም
የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ
ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ
ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::

"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ.. ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም)
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ነሐሴ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓለ ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ገብርኤል መበሥር
4.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
5.አፄ ናዖድ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
6.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (ወልደ ያዕቆብ-ልደቱ)
7.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት
🌈 ወርኀዊ በዓላት🌈
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ
ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . .
.
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::"
(መዝ. ፹፮፥፩-፮)
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ደብረ ታቦር

ደብረ ታቦር ከዘጠኙ የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ በምዕመናን ዘንድ ቡሄ ተብሎም ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ብርሃን፤ የደመቀ የጎላ ማለት ነው፡፡ ይህም ስያሜ በደብረ ታቦር የጌታችንን ብርሀነ መለኮት መገለጥ ጋር የተያያዘ ስያሜ ነው፡፡ የችቦ ማብራት ቱፊትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
ደብረ ታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ ተራራው ከገሊላ ባህር በስተ ምስራቃዊ ደቡብ በኩል ይገኛል፤ መሳ 4 ÷6-14 ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል፤ ጌታችን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ደቀ መዛሙርቱን በጠየቃቸው ጊዜ አንዳንዶች መጥምቁ ዮሀንስ ሌሎች ኤልያስ ነው፤ ሌሎችም ኤርምያስ ነው ወይም ከነብያት አንዱ ነው ይላሉ ብለውት ነበር፤ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ሲላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ’’ ብሎ መልሶለታል ይህ በሆነ በስደስተኛው ቀን ከሐዋርያት መካከል ሦሥቱን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወጣ በኋላ ብርሀነ መለኮቱን ገለጠላቸው ከዚያም ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን ጠርቶ ያመጣቸው ሙሴ ክብርሀን አሳየኝ ብሎት ነበር (ዘጸ. 33÷17-23) ጌታችን ግን በሕይወተ ሥጋ እያለ እኔን ሊያይ የሚቻለው ማንም የለም ቢለውም ከመቃብር አስነስቶ ልመናውን ፈጽሞለታል ፡፡
ስለ እርሱም ማንነት ግራ ለተጋቡ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት እንደተናገረው የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንጂ ከነብያት አንዱ አለመሆኑንና ለዘለአለምም ሰዎች በዚህ እንዳይሰናከሉ በተግባር አስተምሯቸዋል፡፡ ከዚያም ደመና ጋረዳቸውና አብ ከሰማይ "የምወደው ልጄ ይህ ነው አርሱን ስሙት" ሲል መሰከረ፡፡ ማቴ 17÷ 2 ሉቃ 9÷29፡፡
እግዚአብሔር ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
ከ1888-1983 የተወለዱባትና ያረፉባት ወርና ዕለት ነሐሴ 12 ለ 13 አጥብያ
ብጹእ አቡነ ዮሐንስ ቀዳማዊ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዘኩለን አድያማተ ትግራይ ከ ነሐሴ 12 ለ13 አጥብያ የተወለዱባትና ያረፉባት ዕለት ናት፡፡ በተወለዱባት ወርና ዕለት የማረፍ ዕድል የሚጋጥማቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብጹእ አቡነ ዮሐንስ የተወለዱት በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት ልዩ ስሙ ኩርባርያ ተብሎ በሚታወቀው ስፍራ በ1887 ዓ/ም ሲሆን የተጠመቁት ደግሞ በ1888 መስከረም 17 ነው የመጀመርያ ስማቸው የተጠሩት በስመ ክርስትናቸው ገ/መስቀል ነው፡፡
ብጹእ አቡነ ዮሐንስ ከተማሪነት ግዜያቸው ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያን ቀናኢ ቅንና አገልጋይ ነበሩ በትምህርት ተቀባይ ኣእምሮአቸው የተደነቁት መምህራኖቻቸው በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ ተማሪ ገ/መስቀል ከአጠገባቸው አይለዩዋቸውም ነበር፡፡ በትምህርታቸውና በአመስጥሮ መጻሕፍቶቻቸው ሊቀ ሊቃውንት ገ/መስቀል ተብለው እስከ ቤተ መንግስት የታወቁ ነበሩ፡፡
እውነት ለመናገር ወደሃላ የማይሉ ንጉስ የማይፈሩ ስለነበሩ አጼ ሃ/ሰላሴም ሳይቀሩ ይፈሩዋቸው ያከብሩዋቸው ነበር፡፡ጳጳስ ከመሆናቸው በፊትና ከሆኑ በሃላ ለኢትዮጵያ አገራችን ያደረጉት ስራ ብዙ ነው፡፡* ለምሳሌ ያህል
* ኢትዮጵያ በራስዋ ጳጳሳት እንድትመራ ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ክርክርና ትግል እስከመጨረሻ በማስኬድ ያደረጉት ጥረት እንካን ኢትዮጵያስያን ግብጻውያንም የሚረሱት ታሪክ አይደለም ፡፡ ለዚህም ግብጻውያን ገ/ መስቀል ነቀል እያሉ ይጠሩዋቸዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ነቀለን አወጣን ማለታቸው ነው፡፡
*ሌላ ኢትዮጵያ አገራችን ዳር ድንበርዋ እንዳይደፈር አርበኞች ለአገራቸውና ለቤተ ክርስቲያናቸው እንዲዋጉ ሰማእትነት እንዲቀበሉ በማነሳሳት አገራችን ከጣልያን ቅኝ ግዛት ከመውደቅ አድነዋታል፡፡በዚህም የተነሳ ጣልያናውያን አቡነ ዮሐንስ ያሉበት የጠቆመ ወይም ይዞዋቸው የመጣ ብዙ ገንዘብ እንደሚሸላም በወቅቱ አውጀው እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡
ኢትዮጵያ አገራችን ሳትከፋፈል በአንድነት እንድትኖር በአገኙት አጋጣሚ ሳይናገሩ አያልፉም ነበር ፡፡በጣዕመ ስብከታቸውም ብዙ ሰው ይደነቅ ነበር ፡፡አንዳንዴም የብጽእነታችው ትምህርት እንዳያመልጣቸው በማለት ቤታቸው ሽጠው አቡነ ያሉበት ቤተ ክርስቲያን ቤት በመግዛት ይማሩ እንደነበር ህይወት ታሪካቸው ይናገራል፡፡
*ለወጣት የነበራቸው ፍቅር ልዩ ነበር ወጣቶች የነገይቱ የቤተ ክርስቲያን ተረካቦዎች ናቸው በማለት ኮሌጅ ከፍተው መማህራን ከያሉበት ሰብስበው ያስተምሩ ነበር ፡፡
የብጹአ አቡነ ዮሐንስ ስራ እንዲህ በቀላሉ ባጭር ፅሑፍ የሚቃጭ ስላይደለ የተወለዱበትና ያረፉበት ዕለት ለማስታወስ ያህል ነው ስለዚህ አባታችን በአካል እንካን ባናገኛቸውም በሰሩት ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቻቸውን እና በመንፈስ ልጆቻቸው ግን አሁንም እያገለገሉን እያስተማሩን ይገኛሉ፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለን የእግዚአብሔር ቃል የተናገሩዋችሀን መምህራኖቻችሀን አስታውሱ በሃይማኖትና በምግባር ምሰሉዋቸው እንዳለን የብጹእ አባታን ስራ ምግባር በመከተል ለትውልድ የሚተርፍ ስራ ለመስራት እንነሳ * የጻድቅ መታሰብያ ለበረከት ነው * በረከታቸው ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይኑር
ዲያቆን ፊልሞና ይኩኖአምላክ
++ ድንግል ማርያም ተነሥታለች! +++

ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በልጅዋ ፈቃድ ከሞት መነሣት ኦርቶዶክውያን አባቶች ሲያስተምሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሱት ማስረጃ በመዝ. 131፡8 ላይ ያለውን ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን ቃል ነው፡፡ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ትንሣኤ ጋር አያይዞ መጥቀስ አሁን የተጀመረ ነገር ሳይሆን ብዙ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነገር ነው፡፡ ሠላሳ ሦስተኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ከእርሱ ቀድመው የተነሡ አበው ያስተላለፉለትን የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ ታሪክ የዛሬ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በፊት በጻፈው ድርሳን ላይ ፣ በነገረ ማርያም ሊቃውንት ዘንድ Doctor of Dormition በመባል የሚታወቀው ሊቁ ዮሐንስ ዘደማስቆ ፣ ሐዋርያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በድርሳኖቻቸው ላይ ስለ ድንግል ማርያም ትንሣኤ ባነሡና በዓለ ዕርገትዋን ባከበሩ ቁጥር የሚያነቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን የዳዊት መዝሙር ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ቃል ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? ‹ማርያም ተነሣች› የሚል ነገር አለውን? የሚለውን ጥያቄ በዚህች አጭር ጽሑፍ እንመለከታለን፡፡ ወደዚህ ጉዳይ ከመግባታችን በፊት ግን አንድ ቁምነገርን እናስቀድም፡፡

በሐዲስ ኪዳን ለምናምን ፣ በወንጌል ለምንመራ ክርስቲያኖች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ምን ያደርጉልናል? የሙሴ ሕግጋት ፣ የነቢያት መጻሕፍት ፣ የዳዊት መዝሙራት ለክርስቲያኖች ምን ይጠቅሙናል? ብለን ከመጠየቅ እንጀምር፡፡ የዚህ ጥያቄ መልሱ ጌታችን ‹‹በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ሊፈጸም ይገባል›› እንዳለው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ በምሥጢር የሚናገሩት ስለ ክርስቶስ ስለሆነ ነው፡፡ (ሉቃ. 24፡44) ‹ከሙሴና ከነቢያት ጀምሮ ስለ እርሱ የተጻፈውን ተረጎመላቸው› ተብሎ የተነገረላቸው የኤማሁስ መንገደኞች ‹በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትን ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?› ብለው እንደተናገሩ ብሉይ ኪዳን በእርግጥ ስለ ክርስቶስ እንደሚናገር በሚገባ ትርጉሙን ከተረዳን ልባችን በጥልቅ ተመሥጦ ይቃጠላል፡፡ ይህንን የአባቶችን ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ መነፅር በዓይናችን ካጠለቅን ብሉይ ኪዳንን እያነበብን በሐዲስ ኪዳን ባሕር ውስጥ መዋኘት እንችላለን፡፡ በኅብረ አምሳል (Typology) አስቀድሞ የተነገረበትን ምክንያት (Primary application) እና ፍጻሜውን (Ultimate fulfillment) ስንረዳ በታሪክና ትንቢት ሁሉ ውስጥ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን እያገኘነው ስንደነቅ እንኖራለን፡፡

በገነት መካከል ተኝቶ ከጎኑ የሁላችንን እናት ሔዋንን ያስገኘውን አዳም ታሪክ ስናነብ በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ በመስቀል ላይ አንቀላፍቶ ከጎኑ በፈሰሰው የጥምቀት ውኃ የሁላችን እናት ቤተ ክርስቲያንን ያስገኘውን ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ ወይን ጠጥቶ ሰክሮ ዕርቃኑን የወደቀውንና ካም ሲዘብትበት ፣ ሴምና ያፌት ዕርቃኑን የሸፈኑለትን የኖኅን ታሪክ ስናነብ የሞትን ጽዋ ጠጥቶ በሰው ልጅ ፍቅር ሰክሮ ዕርቃኑን የተሰቀለውንና አይሁድ ሲዘብቱበት ፀሐይና ጨረቃ ዕርቃኑን የሸፈኑለትን ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ አብርሃም የሚወደውን ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋ መፍቀዱንና በግ የመሠዋቱን ታሪክ ስናነብ አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን የወደደውን እግዚአብሔር አብንና እስከ ሞት ድረስ የታዘዘ ልጁን ንጹሑን በግ ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ ዳዊት ጎልያድን ድል አድርጎ እስራኤልን ነጻ ሲያወጣ ስናይ ክርስቶስ ዲያቢሎስን ድል አድርጎ የሰው ልጅን ነጻ ሲያወጣ ይታየናል፡፡ እስራኤል በበረሃ ተጉዘው በበትር ከተመታው ከዓለት ውኃ ፈልቆላቸው ሲጠጡ ስናይ በዕለተ ዓርብ ጎኑን በጦር ተወግቶ በደሙ ጥማችንን ያረካልን መድኃኔ ዓለም ይታየንና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ‹ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ› እንላለን፡፡

ወደ መገናኛው ድንኳን ገብተን ደብተራ ኦሪትን ብንጎበኝ እንኳን ክርስትናችን አይለቀንም፡፡ በመሠዊያ ላይ የሚሠዋውን በግ ስናይ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕሊናችን ይመጣብናል፡፡ ወደ ድንኳኑ ዘልቀን በመቅረዙ ላይ መብራት ሲበራ ስናይ እውነተኛው ብርሃን ክርስቶስ ፣ ዕጣን ስናይ የኃጢአት ሽታችንን ያራቀልን ክርስቶስ ፣ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ስናይ በመለኮቱ መለወጥ የሌለበትን ክርስቶስ ፣ መናውን ስናይ የሕይወት እንጀራ ክርስቶስ እየታየን እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ‹‹ልባችን እየተቃጠለ ለካስ ኦሪትና ነቢያት ሁሉ የሚናገሩት ስለ ክርስቶስ ነበረ?›› እንላለን፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ከሆንን ደግሞ ጌታን ባገኘንበት ሥፍራ ሁሉ እመቤታችንን ፍለጋ ማማተራችን አይቀርም፡፡ አዳምን የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ስናየው አዳምን ያለ አባት ያስገኘችዋ መሬት ያለ ወንድ ዘር የወለደችውን ድንግል ሆና ትታየናለች፡፡ አብርሃም የሠዋውን ከዱር ቀንዱ እንደታሰረ የወጣ በግ ስናይ የድንግልናዋ ማኅተም ሳይፈታ የወለደችው የበጉ እናት ትታየናለች፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ገብተንም አናርፍም ፣ እርሱ መብራት ሆኖ ሲታየን እርስዋ መቅረዝ ትሆንልናለች፡፡ እርሱ ዕጣን ሲሆን እርስዋ ማዕጠንት ትሆናለች ፣ እርሱ ታቦት ሲሆን እርስዋ ታቦቱ ያለበት ቅድስተ ቅዱሳን ትሆናለች ፣ እርሱ ጽላት ሲሆን እርስዋ የጽላቱ ማደሪያ ታቦት ትሆናለች ፣ እርሱ በጽላት ላይ የተጻፈው ቃል ሲሆን እርስዋ ጽላት ትሆናለች ፣ እርሱ የተሰወረ መና ሲሆን እርስዋ የመናው መሶበ ወርቅ ትሆናለች፡፡ ለሰብአ ሰገል ‹ሕጻኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት› እንደተባለላቸው እኛም በሔድንበት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ የጌታችንን ምሳሌ ባነበብንበት ሥፍራ ሁሉ እናቱንም እናያታለን፡፡

እውነቱን ለመናገር ለመመርመር ትዕግሥት ላለው ሰው ስለ ክርስቶስ በሚናገሩት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እንኳን ድንግል ማርያምን ቀርቶ ከሐዲው ይሁዳንም ማግኘት ይቻላል፡፡ ዮሴፍ የክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን ዮሴፍ በሃያ ብር እንዲሸጥ ሃሳብ ያቀረበው ወንድሙ ይሁዳ የአስቆሮቱ ይሁዳ ምሳሌ አይደለምን? ፍልስጤማውያንን ድል ያደረገው ናዝራዊው ሶምሶን የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን ሶምሶንን እየሳመች አሳልፋ የሠጠችው ደሊላ ስሞ የሸጠው የይሁዳ ምሳሌ አይደለችምን? አባቱን ለመግደል ሲያሴር ኖሮ መጨረሻ በዛፍ ላይ ተሰቅሎ የሞተው አቤሴሎምስ ጌታውን አሳልፎ ሠጥቶ ተሰቅሎ የሞተው የይሁዳ ምሳሌ አይደለምን? ‹የታመንሁበት የሰላሜ ሰው እንጀራዬን የበላ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ› ተብሎ የተነገረው ስለ ይሁዳ አይደለምን? ብሉይ ኪዳን እንኳን አምላክን ስለወለደችው ቅድስት ድንግል ቀርቶ አምላኩን ስለሸጠው ይሁዳም ትንቢት ተናግሯል፡፡

አሁን ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ! ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት› ብሎ ዳዊት ስለ ቤተ መቅደስ መሠራትና ታቦቱም ወደ ቤተ መቅደሱ ስለመግባቱ የዘመረው መዝሙር ፣ ልጁ ሰሎሞንም መቅደሱ ተሠርቶ ሲያልቅ ደግሞ የዘመረው ይህ መዝሙር ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? (2ዜና 6፡41) ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ከጥንት ጀምሮ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ጋር የሚጠቅሱት ዳዊት ስለ መቅደሱ መሠራትና ስለ ታቦቱ መግባት የተናገረ መሆኑ ጠፍቷቸው ነው? ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት› የሚለውን የዳዊት መዝሙር ከድንግል
ማርያም ጋር አገናኝተን እንድናስብ ያነሣሣን ምንድር ነው? ወደሚለው እንምጣ፡፡

ዳዊት ስለ ታቦቱ የተናገረውን እኛ ስለ ድንግል ማርያም ሆኖ እንዲሰማን ያደረገው ራሱ ዳዊት ነው፡፡ ዳዊትን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እርሱ ስትመጣ ‹‹የእግዚአብሔር ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?›› ሲል አልሰማነውምን? (2ሳሙ. 6፡9) ይህን ንግግርስ ኤልሳቤጥ ‹‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?›› ብላ ለድንግል ማርያም አልደገመችውምን? (ሉቃ. 1፡43) ዳዊት የፈራው ታቦት ወደ እርሱ ሲቀርብ ከዙፋኑ ተነሥቶ በታቦቱ ፊት እየዘመረ ሚስቱ ሜልኮል እስክትንቀው አልዘለለምን? (2ሳሙ. 6፡16) በኤልሳቤጥ ማኅፀን የነበረው ዮሐንስስ የድንግልን ‹‹የሰላምታዋን ድምፅ በሰማ ጊዜ› እናቱ እስክታደንቀው ‹ፅንሱ በደስታ ዘለለ›› አልተባለምን? (ሉቃ. 1፡44) ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የድንግል ማርያምና የልጅዋ ክብር ላልገባቸው ሰዎች ‹‹እንደ ዮሐንስ በማኅፀን ውስጥ መዝለል ቢያቅታችሁ ምነው ነፍስ ካወቃችሁ በኋላ እንኳን ለእግዚአብሔር ማደሪያ እንደ ዳዊት በምስጋና ብትዘሉ?›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ እኛ ምን እናድርግ የእግዚአብሔር ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች እንደተባለ ‹‹ማርያምም በዘካርያስ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች›› ተብሎ ተጽፎ አነበብን፡፡ (2ሳሙ. 6፡11 ፤ ሉቃ. 1፡56) ታዲያ የድንግል ማርያም ታሪክ ከእግዚአብሔር ማደሪያ ከታቦቱ ታሪክ ጋር አንድ ሆኖ ስናገኘው ዳዊት ስለ ታቦት የተናገረውን ስለ ድንግል ማርያም እንደምን አንጠቅስ? የነገረ ማርያምን ታሪክ እንጥቀስ ካልንማ ታቦቱ በወርቅ እንደተለበጠ በንጽሕና ያጌጠችውን ፣ ታቦቱ በመቅደስ እንደኖረ በመቅደስ ያደገችውን ፣ ታቦቱን በትሩ አብባ የተገኘች አሮን እንደ ጠበቃት በትሩ ያበበች ዮሴፍ የጠበቃትን፣ ታቦቱን የነካ ዖዛ እንደተቀሠፈ (2ሳሙ. 6፡7) የድንግልን ሥጋ ነክቶ የተቀሠፈውን ታውፋንያ ታሪክ እንጠቅስ ነበር፡፡

‹የመቅደስህ ታቦት› ማለት መቅደስ የተባለው የሰውነትህ ማደሪያ እናት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ሰውነቱን ‹ይህን መቅደስ አፍርሱት› አላለምን? ‹በጉ መቅደስዋ ነው› ተብሎ አልተጻፈምን? ስለዚህ ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› ማለት ጳውሎስ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት እንትጋ እንዳለው ‹‹ጌታ ሆይ ‹ዕረፍትህ› ወደተባለ ወደ ሰማያት አንተ ብቻ ተነሥተህ አትቅር የመቅደስ ሰውነትህ ማደሪያ እናትህንም ይዘህ ተነሥ›› ማለት ነው፡፡

የእመቤታችን ትንሣኤ ብዙዎችን ማከራከሩ እንዴት ያሳዝናል? ክርስቶስ ‹ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ› ብሏል፡፡ እውነት ትንሣኤን ለወለደች እናት መነሣትዋ ትልቅ ነገር ነው? የሕይወት እናት ሕያው ሆነች ቢባል ያስቆጣልን? ሞትን የሞተው በልጅዋ አይደለምን? የሕይወትን እናት ሞት ይዞ አስቀራት ማለት ደስታ የሚሠጠው ለሞት አበጋዞች ነው፡፡ ‹‹አምላክ ያደረባት የምትናገር ታቦት ፈርሳ ቀርታለች ማለት ፣ ታቦተ ጽዮን ድንግል በሞት ፍልስጤም ተማርካ ቀርታለች›› ማለት የሚያስደስተው በማኅፀንዋ ፍሬ የተፈረካከሰው ዲያቢሎስ ነው፡፡ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን የሚደንቀን መሞትዋ እንጂ መነሣትዋ አይደለም፡፡

ቅዱስ ያሬድ ‹‹የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል›› እንዳለው ሕይወትን ያስገኘች ድንግል ፣ አምላክን የታቀፉ ክንዶች ፣ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆኑ ጉልበቶች በሞት መሸነፋቸው ያስደንቀናል፡፡ መነሣትዋ ግን የምንጠብቀው ነው፡፡ አልዓዛርን ‹አልዓዛር አልዓዛር› ብሎ ያስነሣ ጌታ ፣ በዕለተ ዓርብ በሞቱ ብዙ ሙታንን ያስነሣ ጌታ እናቱን አስነሣ ሲባል የሚቆጡ እንዴት ያሉ ናቸው?

ሁለቱ ምስክሮች የተባሉ ሄኖክና ኤልያስ ወደ ምድር መጥተው አስተምረው ከተገደሉ ‹‹ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ… በሰማይም ፡- ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ ወጡ›› ይላል፡፡ (ራእ. 11፡4-12) ሄኖክና ኤልያስን ከምጽአቱ በፊት ዳግም ላይሞቱ ከሞት አስነሥቷቸው በጠላቶቻቸው ፊት ወደ ሰማይ የሚያሳርጋቸው አምላክ እናቱን በወዳጆችዋ ፊት አስነሥቶ አሳርጓታል ሲባል በቁጣ መቃወም ምን ይባላል?

እንደልጅዋ በራስዋ ዐረገች (Ascension) በማለትና ልጅዋ ወደ ራሱ ነጥቆ ወሰዳት (Assumption) በማለት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ከቻልን የእመቤታችን ማረግ ምኑ ያከራክራል? ዝናምን ከከለከለው ኤልያስ ንጹሑን ዝናም ያስገኘችው ድንግል አትበልጥምን ፣ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረገው ሄኖክስ ይልቅ ለእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችው እመ አምላክ አትበልጥምን?

እኛ ግን ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹‹በሞትዋ ምድር መራራ ኀዘን ስታዝን በሰማይ ደስታ ሆነ እንዳለ›› እመቤታችን ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገርም ሆነ ፣ በልጅዋ ሥልጣን ተነሥታ ስታርግ በሰማይ የሚኖረውን ደስታ በእምነት እናስተውላለን፡፡ ያ ደሃ አልዓዛር እንኳን ሲሞት መላእክት ነፍሱን ወደ አብርሃም አጅበው ወስደውት ነበር ፣ ኤልያስም ሲያርግ መላእክት በእሳት ሰረገላና በእሳት ፈረሶች ነጥቀውት ነበር፡፡ የአምላክን እናት ዕርገት ስናስብ ከዚህ በላይ ዝማሬ ይታየናል ፤ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ እንደጻፈው ቅዱስ ያሬድም ‹በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ› እንዳለው አባትዋ ዳዊት ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› እያለ እየዘመረ ወላዲተ አምላክ ወደዚያኛው ዓለም ተሸጋግራለች፡፡ ኤልያስ ወደ ሰማይ ሲነጠቅ መጎናጸፊያውን ለበረከት እንዲሆነው ለደቀ መዝሙሩ ኤልሳዕ እንደሠጠው እመቤታችንም በልጅዋ ሥልጣን ወደ ሰማይ ስታርግ መግነዝዋን (መታጠቂያዋን) ለቶማስ በመሥጠትዋ ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት አሁንም ድረስ ተከፋፍለው በታላቅ ፍቅር በረከትዋን ይቀበሉበታል፡፡

እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ስለ እመቤታችን መነሣት ስናስብ የምንጠይቀው ‹ተነሣች ወይስ አልተነሣችም ፤ ወደ ሰማይ ዐረገች ወይንስ ዐላረገችም› ሳይሆን ‹በሰማይ የተደረገላት አቀባበል ምን ይመስል ይሆን?› ብለን ነው፡፡ ደሃው አልዓዛር በሞተ ጊዜ መላእክት ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት ከተባለ የአምላክን እናት ምን ያህል አጅበዋት ይሆን? ወደ ሰማይ ማረግ ለእርስዋ ቁምነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰማይን በእጆቹ የሚይዘውን አምላክ በእጆችዋ የያዘች ሁለተኛ ሰማይ ናት፡፡ እርስዋ ወደ ሰማይ በማረግዋም ዕድለኛዋ እርስዋ ሳትሆን ሰማዩ ነው፡፡ ሰማይ ዙፋኑ ነው ፣ ምድርም የእግሩ መረገጫ ናት ድንግል ማርያም ግን እናቱ ናት፡፡ ከእናትና ከዙፋን እናት ትበልጣለች፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ሰማይ አልወለደውም ፣ አላሳደገውም ፣ አላጠባውም ድንግል ግን ይህንን ሁሉ አድርጋለች፡፡ ስለዚህ ወደ ሰማይ ማረግዋ ክብሩ ለሰማዩ እንጂ ለእርስዋ አይደለም፡፡

እመቤታችን ወደ ሰማይ ስታርግ በእርግጥ አቀባበሉ እንዴት ይሆን? እኛ የሰው ልጆች እናታችንን ማክበርም መጦርም የምንችለው በምድር እስካለችና እኛም እስካለን ድረስ ነው፡፡ ‹እናትና አባትህን አክብር› ያለን ፈጣሪ ግን እናቱን ማክበር የሚችለው በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ጭምር ነው፡፡ እናቱ ወደ እርሱ ስትመጣ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንዴት ተቀብሏት ይሆን?

ንጉሥ ሰሎሞን እናቱ ቤርሳቤህ ወደ ቤተ መንግሥቱ በመጣች ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ‹‹ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ ሳማትም ፤ በዙፋኑም ተቀመጠ ፤ ለ
እናቱም ወንበር አስመጣላት በቀኙም ተቀመጠች፡፡ እርስዋም ፡- አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ አታሳፍረኝ አለች፡፡ ንጉሡም ፡- እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ለምኚ አላት›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (1ነገሥ. 2፡19-20) ከዳዊት ሆድ ፍሬ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ንጉሥ ሰሎሞን ይልቅ በዳዊትን ዙፋን ለዘለዓለሙ ይነግሣል የተባለለት ክርስቶስ ይበልጣል፡፡ ስለ ክርስቶስ ‹‹ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ማቴ. 12፡42) ክርስቶስ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከሆነ የክርስቶስ እናትም ከሰሎሞን እናት ትበልጣለች፡፡ ሰሎሞን ለእናቱ ከሠጣት ክብርም በላይ ክርስቶስ ለእናቱ የሚሠጣት ክብር ይበልጣል፡፡ የሰሎሞን ቤተ መንግሥት በምድር ነው ፤ የክርስቶስ ቤተ መንግሥት ግን በሰማይ ነው፡፡ መድኃኔ ዓለም ወደ ሰማያዊው መንግሥቱ እናቱን በጠራት ጊዜ እንደምን ተቀብሏት ይሆን? እንደ ሰሎሞን እናት ወንበር አስመጣላት እንዳንል በሰማይ መቆም መቀመጥ የለም፡፡ ነገር ግን ‹‹የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች›› ተብሎ ድንግሊቱ ስለተሠጣት ክብር ተጽፎአል፡፡ ወርቅ መልበስዋ አነሳት የሚል ካለ ደግሞ ‹‹አሕዛብን በብረት በር የሚገዛቸውን ወንድ ልጅ የወለደችው›› ድንግል ‹‹ፀሐይን ተጎናጽፋ ፤ ጨረቃም ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ፣ ዐሥራ ሁለትም ከዋክብት አክሊል የሆኑላት አንዲት ሴት ነበረች›› ተብሎ ተጽፎላታል፡፡ (መዝ. 44፡9 ፣ ራእ. 12፡1)

ለእኛ ለኦርቶዶክሳዊያን ድንግል ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገር የነበራትን የክብር አቀባበል በሕሊናችን ከማሰብ በቀር ምን የሚያውከን ነገር የለም፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ድንግልን ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? እዚህ ‹ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ› ብሎ ሰላምታ ያቀረበላት ይህ መልአክ ጸጋን የተሞላችው ወደ እርሱ ስትመጣ ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? ቅድስት ኤልሳቤጥስ አሁንም ‹ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?› ብላት ይሆን? መጥምቁስ ዳግም በሰማይ በደስታ ዘልሎ ይሆን? ነቢያቱ ድንግልን እንዴት ተቀበሏት? ኢሳይያስ ‹ትፀንሳለች› ያላትን ድንግል ሲያያት ምን ይል ይሆን? ሕዝቅኤልስ ‹የተዘጋችዋ ደጅ› ወደ እርሱ ስትመጣ ምን አለ? ጌዴዎን ጸምሩን ፣ ኤልሳዕ ማሰሮውን ፣ አሮን በትሩን ፣ ኖኅ መርከቡን ባየ ጊዜ ምን ብሎ ይሆን? ሙሴስ ያልተቃጠለችው ዛፍ ወደ እርሱ ስትመጣ ዳግም እንደ ሲና ተራራው ጊዜ ጫማውን አውልቆ ይሆን? አዳም የልጅ ልጁን ሲያይ ሔዋንስ ዳግሚት ሔዋንን ስታይ ምን ብላ ይሆን? ሁሉንም በሰማይ ለመረዳት ያብቃን!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#ዕረፍተ_ቅዱሳን

† እንኳን ለብፁህ አባታችን ለአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ።

ቅዱሳን ከዚህ ዓለም በሥጋ ሲለዩ አረፉ ይባላል። ሞታቸው ዕረፍታቸው ነውና። ስለ ቅዱሳን ዕረፍት ከማየታችን በፊት ሞትን በ3 ከፍሎ ማየት ተገቢ ነው።

የሥጋ ሞት: ይህ ሞት ሥጋ ከነፍስ ሲለይ ሥጋ ሞተ ያሰኘዋል። ያዕ 2:26 "ከነፍስ የተለየች ሥጋ የሞተች እንደሆነች እንዲሁ ደግሞ ከስራ የተለየ ዕምነትም የሞተ ነው።" እንዲል።

የቁም ሞት: ይህ ሞት በቁም ሳሉ እየሄዱ እየቆሙ እየተቀመጡ እየተኙ እየበሉ እየጠጡ ሥጋ ከነፍስ ሳትለይ ነገር ግን በኃጢአት ተዘፍቆ ከእግዚአብሔር መለየት ከምግባር መጉደል ከሃይማኖት በአፋ መሆን የቁም ሞት ይባላል። 1ጢሞ 5:6 "ቅምጥሊቱ ግን በህይወት ሳለች የሞተች ናት።" ብሎ ሐዋርያው በመልዕክቱ አስፍሮታል።

የነፍስ ሞት: ይህ ሞት በቁም ሳሉ በሰሩት ኃጢአት እንደቆሸሹ በንስሃ ሳሙና ሳይታጠቡ የሥጋ ሞት መቶባቸው በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ሲኦል በነፍስ ላይ ሲፈረድባት የነፍስ ሞት ይባላል።

† የቅዱሳን ሞታቸው ግን ለእነርሱ ዕረፍታቸው ስለሆነ ቅዱሳን ሞቱ አይባልም። ይህም እንደ ምንድን ነው ቢሉ?

1 የሥጋ ሞት ቅዱሳን በዚህ ዓለም ሳሉ ካደረጉት ተጋድሎ ህማምና መከራ ወደ ዘላለማዊ ደስታ ዕረፍት መንግስተ ሰማይ ወደፈጠሪያቸው የሚሄዱበት መንገድ ስለሆነ ነው። ፊሊ 1:23 "ልሄድ ከክርስቶስ ጋር እኖር ዘንድ እናፍቃለው።" እንዳለ ሐዋርያውቅዱስ ዻውሎስ።

2 የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ስለሆነ ነው። መዝ 115(116):15 "የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።" እንዲል።

3 ቅዱሳን በስጋ ሞት ተወስደው ወደ አምላካቸው ከሄዱ በኋላ ዕውቀታቸው ምሉዕ ስለሆነ የቅዱሳኑ ሞት ዕረፍት ይባላል። የቅዱሳን ክብርና ዕውቀት፣ ዕውቀት ሰጭ ከሆነ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ ሁሉን ያውቃሉ፡፡ ለምሳሌ ኤልሳዕ ነቢይ በዚህ ዓለም በነበረ ጊዜ ደቀ መዝሙሩ ግያዝ በምሥጢር /በስውር/ ከሶሪያዊው ንዕማን ስጦታ መቀበሉን ማንም ሳይነግረው እንዴት እንዳወቀ በሁለተኛው መጽሐፈ ነገሥት. 5፡25-27 መመልከት ይቻላል፡፡ ሌላም ከሶርያ ንጉሥ ባለሟሎች አንዱ ለንጉሡ ስለ ኤልሳዕ እንዲህ ሲል ነገር ሠራ "ጌታ ሆይ እንዲህ አይደለም ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእሥራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉስ ይነግረዋል።" በማለት ኤልሳዕ በቦታም አንድ አካባቢ ሳይሆኑ በጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያውቅ እንደ ነበረ ተጽፎአል። 2ኛነገ. 6፡12 በረሀብ ጊዜም የእስራኤል ንጉሥ ሊያስገድለው መልእክተኛ መላኩን ኤልሳዕ አወቀ። 2ኛነገ.6፡12 በዚህም ዓይነት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የሐናንያንና የሰጲራን ምሥጢራዊ ተንኮል የነገረው ሳይኖር አውቆ በሞት ቀጣቸው። የሐዋ. 5፡3-9 ታዲያ ቅዱሳን ካረፉ በኋላ ይህ ዕውቀታቸው አይለያቸውም ይልቁኑ በምድር የነበራቸው ከፊል ዕውቀት ምሉዕ ይሆናሉ። በነፍሳቸው ሕያዋን እንጂ ሟቾች አይደሉምና ነው፡፡ ለዚህም ነው ጌታ ከሰዱቃውያን ጋር ስለሙታን ይነጋገር በነበረበት ጊዜ እግዚአብሔር የአብርሃም የይስሐቅ አምላክ ነው ሲባል እነዚህ የቀድሞ አባቶች በነፍስ ሕያዋን ስለሆኑ ነው እንጂ እርሱ የሙታን አምላክ ስለሆነ አይደለም ያለው ለዚህ ነው። ማቴ 22:31-32
እስኪ ቅዱሳን እውቀታቸው በአጸደ ነፍስ ምሉዕ እንደሆነ የሚያመለክት የተወሰኑ ማስረጃዎችን እንመልከት።
ኤር 15 :1–4 "እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙ እንኳ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይመለስምና ከፊቴ አስወግዳቸው ይሂዱ።" ይህ አባባል የሚያመለክተው ከኤርምያስ ዘመን በፊት ከሞቱ ብዙ ዓመታት ያሳለፉት ሙሴና ሳሙኤል እስራኤል ዘሥጋ የበደሉትን ያውቁ ስለነበር እግዚአብሔርን ይማጸኑና ይማልዱ እንደነበር ነው የሚያሳየው፡፡
ሉቃ 16:19–30 በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ አብርሃም በገነት ሆኖ በምድር ባለፀጋው ነዌ በድሀው አላዛር ላይ ያደረገበትን አውቆ አላዛርንም በእቅፉ እንዳኖረው ይናገራል። ስለዚህ የቅዱሳን ዕውቀት በአፀደ ነፍስ ምሉዕ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል።
4 ሞት ለቅዱሳን እንደ እንቅልፍ በመሆኑ ቅዱሳን አረፉ እንጂ ሞቱ አይባልም። ሰው በዚህ ዓለም ሳለ ከሥጋ ድካም በእንቅልፍ እንደሚያርፍ እንዲሁ ቅዱሳንም በዚህ ዓለም ሳሉ ካደረጉት ተጋድሎና መከራ በስጋ ሞት ያርፋሉና ነው። ሐዋ 7:59–60 ላይ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን በድንጋይ ሲወግሩት "ጌታ ሆይ ይህንን ኃጥያት አትቁጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ ይህንንም ብሎ አንቀላፋ።" እንዲል።

5 ቅዱሳን በዕረፍታቸው ክብራቸው ይገለጣል።ልዑል እግዚአብሔርም ቃልኪዳን ይገባላቸዋል። መዝ 88:2 "ከመረጥኳቸው ጋር ቃልኪዳኔን አደረግኹ።" እንዳለ በዕለተ ዕረፍታቸው ቃልኪዳንን ከፈጣሪያቸው ይቀበላሉ።
ከቅዱሳን ረድኤት በረከት ይክፈለን። የጻድቁ አባት የአቡነ ተክለሃይማኖት ምልጃ አይለየን። የእመቤታችን ፍቅሯ በልባችን ጣዕሟም በአንደበታችን ይኑር። ይቆየን።

#ከወንድማችን አቤኔዘር (ወልደ ተክለሃይማኖት)
"ለበጎ ነው"

"አንድ ንጉስ ከአጃቢው ጋር በመሆን ለአደን ይወጣል። ለአደን ሲወጡ ንጉሱ ወጥመድ እያጠመደ እያለ ወጥመዱ አምልጦት እጁን ቆረጠው። በዚህም አጃቢው በማዘን "አይዞህ ንጉስ ሆይ ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!" ይለዋል። በዚህም ንጉሱ በንዴት እየጦፈ "የኔ እጅ መቆረጥ ነው ለበጎ?" ይለውና እስር ቤት አሳሰረው።

ከብዙ ጊዜ በኋላ ንጉሱ ብቻውን ሀገሩን ሲዞር ሰው አርደው ለጣዖት መሰዋት የሚያደርጉ ጨካኝ ሰዎች ያዙትና አርደው መሰዋት ሊያደርጉት ሲሉ ቆራጣ እጁን አዩት። በእነሱ ህግ መሰዋት የሚያደርጉት ሰዉ ሙሉ ጤነኛ መሆን ስላለበት ለቀቁት።

ንጉሱ አጃቢው 'ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!' ያለው ትዝ አለውና እስር ቤት ሄዶ ስላሰርኩህ ይቅርታ አርግልኝ! ብሎ ታሪኩን አጫወተው። አጃቢውም "ማሰርህ ለበጎ ነበር! እኔም መታሰሬ ጠቅሞኛል።" አለው። ንጉሱ "እንዴት?" አለው አጃቢውም "ባልታሰር ኖሮ ከአንተ ጋር እሄድና አንተ ቆራጣ መሆንህን ሲያውቁ ይለቁህና አኔን ይገሉኝ ነበር" አለው።

ስለዚህ ሁላችንም ስለተደረገልንም ሆነ ስላልተደረገልን እንዲሁም ስለሆነውም ሆነ ስላልሆነው ነገር ሁሉ "ለበጎ ነው" ማለት ይልመድብን፡፡
#ድንግል_ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ። ይደንቃል።

#ደንግል_ሆይ መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን ይዘጋዋል። አይችልምና።

#ልዑሉን_የወለድሽ_ልዕልት_ሆይ የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ። ለዚህ ቃል የለም ዝምታና አንክሮ እንጂ።

#ድንግል_ሆይ የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ። #ትንሣኤሽን #የሚያምን ሁሉ #አሜን ይበል።

#ምልጃሽ #ኢትዮጵያን #ይታደግ። ለአለም ምህረት ይሁን ።

#Memhr_Abunu_Mamo
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ፤ ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽሸ
#Ðôlçhë_Fäfî

ልጄ ጸጉርህ ወጣት ሳለህ ጥቁር፣ ጐልማሳ ስትሆን ገብስማ፣ ስትሸመግል ነጭ ይሆንልሃል። በወጣትነት ማስተዋል ያጥርሀልና ፀጉርሕ ጥቁር፣ በጎልማሳነትህ ጉልበትና ጥበብ ተዋህደውሃልና ገብስማ በሽምግልናህ እውቀትህ በዝቷልና ነጭ ይሆንልሃል።

ጉልበት ያለው ወጣት ማስተዋል ያጥረዋል። ማስተዋል ያለው ሽማግሌ ጉልበቱ ይከዳዋል። ጉልበትና ጥበብ የተዋሃዱት ጎልማሳ ስትሆን ግን ብዙ መስራት ይጠበቅብሃል።

ሀኪም ታማሚ ታካሚውን አስቀምጦ ወይም አስተኝቶ እንጂ በቁሙ እንደማያክመው ሁሉ እግዚአብሔርም አሳምሞ ወይም ጥሎ ያስተምርሃል። ደግሞም ያክምሃል። ሲያስተኛሕና ሲጥልህ "ጌታ ሆይ የምታስተምረኝ ምንድን ነው?" በለው እንጂ አትዘን አትማረር። ለሰው በቁሙ መማርና መለወጥ ብዙ ጊዜ ጭንቅ ነውና እግዚአብሔር ጥሎ ያስተምርሃል። ያነሣሃል።

ልጄ ሽምግልናን እንድታያት ወጣትነትህ ሽምግልናን ታክብራት። የናቅኸውን ነገር እግዚአብሔር አይሰጥህምና ሽማግሌ እንድትሆን ሽምግልናን አክብራት።

ልጄ አምስት አይነት ዘውዶች አሉ። አምስተኛው ግን ከሁሉም ይበልጣል።
✟ የመጀመሪያው የንግስና ዘውድ፣
✟ ሁለተኛው የትምህርት ዘውድ፣
✟ ሦስተኛው የተክሊል ዘውድ፣
✟ አራተኛው የክህነት ዘውድ ሲሆኑ
✟ አምስተኛው ግን የሽበት ዘውድ ናቸው።
አራቱም ዘውዶች ሲመሽ ይወልቃሉ። የማይወልቀው የተፈጥሮ ዘውድ ሽበት ግን ከሁሉም ይበልጣል መብለጡም በኑሮ ማስተዋልን መውለዱ ነው።

ልጄ የክብር ኑሮ አድካሚ ነውና አትመኘው ሀብትም ርካታ የለሽ ያደርጋልና ፍቅርን ምረጥ። አፈር ሥጋዬን ካላከበሩልኝ ብለህ ጠብ አታብዛ የምትረግጣት መሬት አንድ ቀን ትረግጥሃለችና አረማመድህ በዝግታ ይሁን። ገንዘብ ካለኝ ወዳጅ ይኖረኛል ብለሕ አታስብ። ገንዘብ ከድህነት እንጂ ከሞት አያስጥልም። ፍቅር በፍቅር እንጂ በገንዘብ አይገዛምና በገንዘብሕ ሀሰተኛ ወዳጅና እውነተኛ ጠላት እንደምታተርፍ እወቅ። ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ የተባለው ለአውሮፕላን እንጂ ለፅድቅ አይደለምና ገንዘብሕን ተማምነህ የድንግልን አማላጅነት የክርስቶስን ቤዛነት አትርሳ።

ልጄ እኔ ብቻ በችግር እኖራለሁ ብለህ ሌላው ባለመቸገሩ አትቅና። ሁሉም ለማኝ ሲሆን ደግ (ጥሩ) አይደለምና። ዛሬ ዓለም የተጨነቀው ሁሉም ሀገር በመቸገሩ ነው። ሁሉም ሲቸገር ደግ አይደለምና ይሕን አትመኝ።

ሲነጋ ወደ ዓለም ሲመሽ ወደ እግዚአብሔር አትገስግስ። መከራህን ለጌታ ደስታህን ለዓለም አታድርግ። እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ።ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽ። ሕፃን ልጅ ሲቆሽሽም የሚሸሸው ወደ እናቱ ነውና አንተም (ኃጢያትህ ሲበዛ) ወደ እናት ቤተክርስቲያንህ ሽሽና ንስሀ ግባ። ንስሃ ደግሞ ያጣኸውን ለማግኘት የብልጠት መንገድ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ስጦታ በትዕቢት ስለመያዝህ የምትፀፀትበት ሊሆን ይገባዋል።

ልጄ የወጣህበት ሰረገላ በመሬት ላይ ቆሟል! መሬት ደግሞ በእግዚአብሔር እጅ ላይ ተቀምጣለች። የተሸከመንን የተሸከመ እርሱ እግዚአብሔር ነው። የኮራንባቸው ነገሮች ሁሉ የእርሱ ናቸው። ከእርሱ በቀር የሚችለን ማንም የለም። ብዙ ዘመን ግን ያለ እግዚአብሔር በራሳችን ለመኖር እቅድ አውጥተናል፤ ያለ እግዚአብሔር መኖር ግን አይቻልም። ያለ እርሱ መኖር ፍፃሜው ሞት ነውና።

ልጄ ሆይ ከእግዚአብሔር ተለይተሕ መኖር አይቻልም። እርሱ በነፍስም በሥጋም ገዢሕ ነውና ከእርሱ ጋር ተጣበቅ። መንግስት ችግር ሳይመጣ ወታደሩን በችግር ያሰለጥናል፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን መቆም እንድንችል በትግል ውስጥ ያሰለጥንሃልና አትመረር።

ልጄ አንተ የሠማይ ኮኮብ ነህ። የተደበቅህ ቢመስልህም ሁሉ ያይሃል። የክዋክብት ሕልውናቸው ብርሃናቸው ነው። የአንተም ክርስትና ሕልውናው የተለወጠ ሕይወት መሆኑን አስተውል። አዎ የሰማይ ኮኮብ ነህ አገርህም በሰማይ እንደሆነ እወቅ። ስምህ ክርስቲያን አገርህ በሰማይ ዘርህ ክርስትና እናትህ ድንግል ማርያም ንጉስህ ክርስቶስ ነው።

ልጄ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል። ብዙዎች ስለጠሉህም ይጠላሃል። አንተ ግን የብዙሃን እውነት ነው ሳይሆን እግዚአብሔር እውነት ነው በሚል መመሪያ ተመራ። ለመልካምነትህ ክፉ ምላሽ ለወሮታህ ከሳሽ ቢነሳብህ የመልካም ነገር ደሞዝ ሰጪ እግዚአብሔር መሆኑን አምነህ ሥራህን ሥራ።

ልጄ መልካም ነገርህ ነገ ሊረሳ ይችል ይሆናል መልካም መሆንህንም ሰዎች ላይረዱልህ ይችላሉ እውነተኛ መልካምነት ግን ምስጋናን ሳያደምጡ የሚፈፀም መሆኑን እወቅ።

ልጄ ታማኝ ስትሆን ያለፈብሕ ትመስል ይሆናል፤ ግልፅ ስትሆን በቀላሉ ልትጠቃ ትችላለህ፤ ታማኝና ግልፅ መሆንህን ግን እግዚአብሔር ስለሚወደው ብቻ አጥብቀህ ያዘው።

ልጄ ልጅነት የለሰለሰ መሬት፣ ወጣትነት ያዝመራ ዘመን፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል። በሽምግልናሕም የምታጭደው የወጣትነትሕን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ።

(ይህ እማሆይ ፅጌ አሌልቱ ደብረ ሰዋሰው አደሬ ኪዳነ ምሕረት የሴቶች ገዳም ውስጥ ነው የሚኖሩት እናት ለ#Ðôlçhë_Fäfî የሰጡት ታላቅ ምክር ነው)
Send this to your telegram friends
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
@ethiopianorthodoxbooks
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
To join our channel click the one in blue

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር