Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.7K subscribers
3.84K photos
144 videos
2 files
414 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ሁልጊዜም ለበለጠ አገልግሎት እና ውጤታማነት እንተጋለን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የሚስ ቤልጂየም 2021 አሸናፊ ወ/ት ቅድስት ዴልቶርበኢትዮጵያ አየር መንገድ የተለያዩ የስራ ክፍሎችን እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን ጎብኝታለች። በቆይታዋም በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን እና የባህላዊ ምግብ አዳራሾችን ተዘዋውራ ጎብኝታለች። ከታዋቂው የአለም አትሌቲክስ ጀግና ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴም ጋር ተገናኝተዋል። የአየር መንገዳችንን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕቦች በመጎብኘቷ ክብር ተሰምቶናል።
👍1
ከሂማላያ ተራራ በላይ የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን binyamzemo ናቸው፤ እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፤መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ተገቢ የሆኑ የጥንቃቄ መንገዶችን በመከተል እርስዎን ካሰቡበት ለማድረስ ተዘጋጅተናል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ A350-900 በዱባይ ኤር ሾው 2021 ለእይታ ቀርቧል።
የዱባይ ኤር ሾው ከ1,200 በላይ ኤግዚቢሽን አቅራቢዎች እና ከ148 በላይ ሀገራት ተወካዮች የሚሳተፉበት ትልቅ የአየር ትዕይንት ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#DubaiAirShow
👍1
በአቪየሽን ኢንደስትሪው አዳዲስ ምርቶች እና ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ የሚቀርቡበት የ”ዱባይ ኤር ሾው 2021” ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም በዝግጅቱ ላይ እየተሳተፈ ሲሆን ለእይታ ያቀረበው ኤርባስ A350-900 አውሮፕላንም ጎብኚዎችን እያስተናገደ ይገኛል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#DubaiAirShow
👍1