የኢትዮጵያአየር መንገድ ከሚድያዎች ጋር ባለው የላቀ ሞያዊ ግንኙነት እና የላቀ ሞያዊ ጨዋነት አርትስ ቲቪ ለአየር መንገዱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ዋና ሃላፊ ወ/ሮ ሃና አጥናፉ የዕውቅና ሽልማት አበርክቷል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #አርትስቲቪ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሳምንቱን ሙሉ በሚዘልቅ ሰፊ መርሀ-ግብር እየተከበረ የሚገኘው የሠራተኞች ቀን በትላንትናው ዕለት በተደረገ ከመንግስት ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት በተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የመሰረተ ልማት ጉብኝት ቀጥሏል። ሃላፊዎቹ የአየር መንገዱን ዋና ዋና የስራ ክፍሎች ጎብኝተዋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #የሰራተኞችቀን2017
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የ2025 የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ሽልማትን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አበርክቷል። ይህ ሽልማት አየር መንገዱ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለፅዱ ኢትዮጵያ ላበረከተው አስተዋፅኦ የተበረከተ ሲሆን አየር መንገዱ በዘርፉ እየተጫወተ ላለው ሚና ዕውቅና የሰጠ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ