Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊው የሰራተኞች ቀን ክብረ በዓል አካል የሆነው የመድረክ ውይይት በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ተከናውኗል። በመድረኩም የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ የዓመቱ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ሰራተኞች እንዲሁም የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ሳምንቱን ሙሉ እየተከበረ የሚገኘው ዓመታዊው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሰራተኞች ቀን ዓለም-አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ በተሠራው የአየር መንገዱ የእግር ኳስ ሜዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢትዮጵያ አየር ኃይል ከፍተኛ አመራሮች፤ እንዲሁም በሁለቱ ተቋማት የወንድ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል በተደረጉ ማራኪ የእግር ኳስ ጨዋታዎች፣ በሰራተኞች መካከል በተደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ደምቆ ቀጥሏል። ክብረ በዓሉ በነገው ዕለት በሚደረግ እና 18 ሺ የአየር መንገዱ ሠራተኞች በተጋበዙበት ታላቅ በዓል የሚፈጸም ይሆናል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ