Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.75K photos
141 videos
2 files
411 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ እና አጠቃላይ በካርጎ አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን የአፍሪካ ምርጥ የፋርማ እቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Air Cargo Pharma Service of the Year, Africa) እና የአፍሪካ ምርጥ የዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Cargo Airline of the Year, Africa) በመባል ሁለት ሽልማቶች ከ “Aviation Achievement Awards” (AAA) የተበረከተለት መሆኑን ሲገልጽ በደስታ ነው።
እነዚህ ሽልማቶች አየር መንገዳችን ለልህቀት፣ ፈጠራ እና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለደንበኞች ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክቱ ሲሆን አየር መንገዳችን ዓለም አቀፍ የዕቃ ጭነት በረራ አድማሱን እያሰፋ መሄዱን ተከትሎ በዓለም ደረጃ ያለውን ተፎካካሪነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ያስችለዋል።
አሸናፊዎች እንድንሆን ላበቁን የምንጊዜም አጋሮቻችን እና ታታሪ ሰራተኞቻችን ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን። የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መዳረሻዎቹንና አገልግሎቶቹን በማስፋፋት የመሪነት ሚናውን ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎ
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሞዴል ምን ይመስልዎታል?
Anonymous Poll
25%
ሀ-ቦይንግ 787
30%
ለ-ኤርባስ A350
39%
ሐ-ቦይንግ 777
5%
መ-ቦይንግ 767
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርቱጋልዋ ፖርቶ ከተማ ከሀምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት አራት ቀን የበረራ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን ለውድ ደንበኞቹ በደስታ ያበስራል። ይህ አዲስ በራራ ወደ አውሮፓ ለሚጓዙ መንገደኞቻችን የተቀላጠፈ አገልግሎት እና ምቹ የበረራ አማራጭ ከመሆኑ ባሻገር አየር መንገዳችን በአውሮፓ ሀገራት ያለውን የበረራ አድማስም ያሳድጋል።
ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-to-commence-new-flight-service-to-porto-in-portugal
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፖርቶ
አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት የመሪነት ድርሻውን በብቃት እየተወጣ የሚገኝ የስታር አሊያንስ አባል አየር መንገድ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የፅናት፣ የአንድነት እና የኩራት ምልክት፤ ዓድዋ!
እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ዓድዋ
በስኬት የደመቀ የስራ ሳምንት ይሁንልዎ!!!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በላቀ አገልግሎት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት እና የቱሪዝም ሚኒስቴር የአዲስ አበባ የቱሪዝም ዕድገትን ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገና በከተማዋ የቆይታ ግዜ ለሚኖራቸው መንገደኞች በተዘጋጀ ስቶፕ ኦቨር ፓኬጅ ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

የዚህ የመግባቢያ ሰነድ ዋና ዓላማ አገራችን ለስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም ያላትን ሰፊ ዕድል መነሻ በማድረግ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት በተቀናጀ ጥረት ስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም እንዲስፋፋ፣ እንዲጎለብት እና ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ የሚያስችል የትብብር ማዕቀፍ ለመዘርጋት ነው።

ስምምነቱን ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ ክብርት ሰላማዊት ዳዊት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተፈራርመዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስደሳች በረራ እና ማራኪ እይታ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በየትኛው ወቅት መብረር ያስደስትዎታል? #የኢትዮጵያአየርመንገድ
Anonymous Poll
22%
ሀ. በክረምት
19%
ለ. በበጋ
43%
ሐ. በምሽት
17%
መ. በቀን
ከሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሃይደራባድን በህንድ አምስተኛ መዳረሻች ልናደርግ ተዘጋጅተናል። ትኬትዎን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app በመቁረጥ ወደ ሃይድራባድ ጉዞዎን ከእኛ ጋር ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እንግሊዝ ማንችስተር ከተማ የሚያደርገውን አምስት ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ ከሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዕለታዊ በረራ እንደሚጀምር ሲያበስር በደስታ ነው።
ትኬትዎን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app በመቁረጥ ጉዞዎን ከ እኛ ጋር ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ማንችስተር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚያበራቸው የአውሮፕላን አይነቶች (ሞዴሎች) መካከል በየትኛው ላይ ሴት አብራሪዎች ያለው ይመስልዎታል? #የኢትዮጵያአየርመንገድ
Anonymous Poll
20%
ቦይንግ 737
10%
ቦይንግ 767
22%
ቦይንግ 777
20%
ቦይንግ 787
23%
ኤርባስ A350
12%
Q-400
50%
በሁሉም የአውሮፕላን አይነቶች (ሞዴሎች)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም ዓቀፉን የሴቶች ቀን ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ሀላፊ አቶ ለማ ያዴቻ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በሴቶች ብቻ በሚመራ በረራ ዘንድሮም ለዘጠነኛ ግዜ የሚያከብር ሲሆን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ወደ አቴንስ፣ ሳኦፖሎ፣ ኒው ዴልሂ፣ ዊንድሆክ፣ ዱባይ እና ባህር ዳር በሴቶች ብ ቻ በሚከወን በረራ ቀኑን በድምቀት ያከብራል።
መልካም የሴቶች ቀን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ