Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
91.1K subscribers
3.87K photos
146 videos
2 files
416 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ከቀደምት ፎቶ ማህደራችን!

#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
42😍7👍3
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመራር አባላት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ።
በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቪርስቲ፣ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል፣ የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እና የምስለ በረራ ክፍልን የስራ እንቅስቃሴዎች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና ከአየር መንገዳችን የአመራር አባላት ጋር በአየር መንገዱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር ከሚተዳደሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አንዱ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍298
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ታማኝነት እና ፅኑ የስራ ቦታ ስነምግባር በተግባር! በዛሬው የኢትዮጵያ መርሐግብር በተለያየ ግዜ እና አጋጣሚ በስራ ላይ እያሉ ያገኙትን ዳጎስ ያለ ገንዘብ በፍፁም ታማኝነት ለመንገደኞች እንዲመለስ ያደረጉ ምስጉን የስራ ባልደረቦቻችንን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ይከታተሉን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ @fanabroadcastingcorporate
👍298
የአፍሪካ አቪዬሽን ልህቀት ተምሳሌት! ቀጣይ በረራዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍4913👏3
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የ2025 ዓ.ም (STAT Times International Awards for Excellence in Air Cargo 2025) የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት ልሕቀት ሽልማት መርሀግብር “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” በመባል ዕውቅና ተቀዳጀ። ከዚህ በተጨማሪም “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት ኤርፖርት” እና “ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ ያለ የዓመቱ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” በመባል ተደራራቢ ዕውቅና እና ሽልማት ተችሮታል።
እነዚህ ሽልማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ላለው ዘርፈ ብዙ ዓለም አቀፍ አገልግሎት አስተማማኝነትና ቅልጥፍና ማረጋገጫዎች ሲሆኑ፤ የበረራ አድማሳችንን እና አገልግሎታችንን በማጠናከር አህጉራዊ መሪነታችንን እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነታችንን ለማስቀጠል በዕጅጉ የሚረዱ ናቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎ
👍7216👏16😍5🎉4
ምቹ፣ አስተማማኝ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍379