Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ክቡራን ደንበኞቻችን

ዛሬ በደንበኞቻችን የጥሪ አገልግሎት ማዕከል ቁጥር 6787 ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ማዕከሉ የደንበኞችንን ጥሪ በሙሉ አቅሙ እየተቀበለ አለመሆኑን መግለፃችን ይታወሳል።

ችግሩን ለመቅረፍ የቴክኒክ ባለሙያዎቻችን ባደረጉት ርብርብ በአሁኑ ሰዓት አገልግሎቱን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል። በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ወደ 6787 በመደወል የተለመደውን የደንበኞች አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እያስታወቅን ለተፈጠረው ችግር በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
ጤና ይስጥልን!
ይህ የስታር አሊያንስ አባል የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም ዓቀፍ የመንገደኞች ጥሪ ማዕከል ነው። እርስዎን ለማስተናገድ ሁሌም ዘግጁ ነን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስደሳች በረራ እና ማራኪ እይታ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር! በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበርሩ ያነሷቸውን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን በኩል ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ጋር ወደ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ይጓዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአፍሪካ አቪዬሽን ታሪክ የስኬት እና ቀዳሚነት ምልክት ሆነን ዛሬ ላይ ደርሰናል። ለበለጠ ስኬት እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎትም እየተጋን እንገኛለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከእኛ ጋር የሚኖርዎትን ቆይታ በልዩ መስተንግዷችን ምቹ እና አስደሳች ለማድረግ ሁሌም እንተጋለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ከዚህ አለም በሞት ለተለዩት ለቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለካፒቴን መሐመድ አህመድ ቤተሰቦቻቸው፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የመታሰቢያ መርሓ ግብር ያካሄደ ሲሆን በአየር መንገዱ ቅጥር ግቢም የመታሰቢያ ሀውልት ቆሞላቸዋል።

ካፒቴን መሀመድ አህመድ በአቪዬሽኑ መስክ ግንባር ቀደም ከሚባሉት አመራሮች አንዱ ሲሆኑ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለንተናዊ ዕድገት ያኖሩት የማይተካ አሻራ በመጪው ትውልድም ሁልግዜ ሲታወስ ይኖራል።

ካፒቴን መሀመድ አህመድ ከኢትዮጵያ አልፈው የአፍሪካ አየር መንገዶች ህብረት ን ለአስር አመታት በመምራት በአፍሪካ አየር መንገዶች መካከል የጠበቀ ግንኙነት እንዲፈጠርና ለአህጉሪቱ የአቪዬሽን ኢንደስትሪ ዕድገት በጋራ የመስራት መንፈስ እንዲጎለብት ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። በአለም ዓቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር በአመራር ኮሚቴዎች ውስጥ በነበራቸው ሚና የአፍሪካ አየር መንገዶች በአለም መድረክ አድገውና ጎልብተው በአለም መድረክ ላይ እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል።

ካፒቴን መሀመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በዋና ስራ አስፈፃሚነት በመሩባቸው ዓመታት አየር መንገዱ ዛሬ ለደረሰበት እድገት እና ስኬት ባበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር ቦርድ፣ ማኔጅመንት እና ሰራተኞች ምን ጊዜም ያስታውሷቸዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀደም ባሉት ዓመታት አየር መንገዱን በሥራ አስኪያጅነት እና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመሩ የቀድሞ አመራሮች የዕውቅና እና የሽልማት መርኃ ግብር አካሄደ።

በመርሓ ግብሩ ላይ ኮሎኔል ስምረት መድሀኔ፣ ካፒቴን ዘለቀ ደምሴ ፣ ዶ/ር አህመድ ኬሎ ፣ አቶ ብስራት ንጋቱ ፣ አቶ ግርማ ዋቄ እና አቶ ተወልደ ገብረማርያም አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት እና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት በመሩባቸው አመታት አየር መንገዱ ዛሬ ለደረሰበት ስኬት እና አለም ዓቀፍ ዝና ላበረከቱት የማይተካ የመሪነት አስተዋፅዖ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል ።

ብሔራዊ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰባ ስምንት አመት በላይ በበርካታ ደማቅ ስኬቶች ታጅቦ ዛሬ ለደረሰበት ከፍተኛ ደረጃ በቅቷል። ይህ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ውስጥ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው የአየር መንገዳችን ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ አሁንም በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ