የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹንና አገልግሎቱን በማስፋት የባሌ ሮቤ ዋቆ ጉቱ ኤርፖርት ተርሚናልን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሀደ ሲንቄዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል።
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ የቱሪስት መዳረሻ በሆነው የባሌ ዞን ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው ይህ የዋቆ ጉቱ ኤርፖርት ተርሚናል የቱሪስት ፍሰቱን ለማሳለጥ ከሚኖረው ሀገራዊ ፋይዳ በተጨማሪ ለደንደበኞች ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።
የኢትጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ባሌ ሮቤ ዋቆ ጉቱ ኤርፖርት 14 ሳምንታዊ በረራዎችን ያደርጋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ በይፋ የተመረቀው የዋቆ ጉቱ ኤርፖርት ተርሚናል ጎብኚዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም የአካባቢው ተወላጆች ከመላው ዓለም ወደ ባሌ ዞን ሲመጡ ምቾት ያለው አገልግሎት በመስጠት ቁልፍ መተላለፊያ (Gateway) ሆኖ ያገለግላል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ2017 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል። መልካም በዓል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአስደናቂ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የምትታወቀውን ታሪካዊቷን የላሊበላ ከተማን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይጎብኙ። ይህንን የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ በስፍራው ተገኝተው በመጎብኘት የማይረሳ የጉዞ ትዉስታ ያኑሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ላሊበላ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ላሊበላ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አጠቃላይ የደንበኞች አገልግሎት እንደምን ያለ ነው? በዛሬው የኢትዮጵያ ዝግጅታችን የኢትዮጵያ አየር መንገድን የደንበኞች አገልግሎት የስራ ክፍል እንቅስቃሴ በተመለከተ ቆይታ አድርገናል፤ይከታተሉን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ @FanaBroadcastingCorporate
#የኢትዮጵያአየርመንገድ @FanaBroadcastingCorporate
ክቡራን ደንበኞቻችን
የደንበኞች ጥሪ መቀበያ ማዕከል ቁጥራችን 6787 በሙሉ አቅሙ የሀገር ውስጥ ጥሪዎችን እየተቀበለ እንዳልሆነ ተረድተናል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የቴክኒክ ባለሙያዎቻችን እየሰሩ ይገኛሉ።
በ6787 መገልገል ያልቻላችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን በድረ ገፃችን www.ethiopianairlines.com በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app እንዲሁም በሌሎች የዲጂታል አማራጮቻችን በመጠቀም አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጨማሪ እርዳታ የምትሹ ደንበኞቻችን በአቅራቢያችሁ ወደሚገኙ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችን አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን። ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል