Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.6K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ወደ በርካታ መዳረሻዎቻችን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ቅርንጫፍ ቢሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦች ያስተዋወቀ ልዩ መርሐግብር በኪንሻሳ አካሄደ። በመርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመኑ የደረሰባቸውን አዳዲስ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ በማስተዋወቅና አህጉሪቱን ከመላው ዓለም ጋር በማገናኘት ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋፅዎ የተገለፀ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏትን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶችና ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሰፊው ተዋውቀውበታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዘመናዊነትንና ዕምቅ ባህላዊ ይዘቶችን አለም አቀፍ ዕውቅና ከተቸራቸው ሙዚየሞች ጋር አጣምራ ወደያዘችው ፍራንክፈርት ከተማ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አስደሳች የበረራ ጉዞ ያድርጉ!
#ፍራንክፈርት #የኢትዮጵያአየርመንገድ
መልካም አለም ዓቀፍ የሕፃናት ቀን ለወደፊቱ አቪዬሽን ቴክኖሎጂ ተረካቢዎች!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አለምዓቀፍየሕፃናትቀን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስደሳች በረራ እና ማራኪ እይታ ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ጋር! በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበርሩ ያነሷቸውን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን በኩል ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዘመናትን በስኬት ከፍታ የተሻገረ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግብጽ፣ካይሮ በተካሄደው 56ተኛው የAFRAA (የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር) አጠቃላይ ስብሰባ በዓለም አቀፍ አገልግሎት የዓመቱ ምርጥ አየርመንገድ (Airline of the Year - Global Operations) በመባል ለስምንተኛ ግዜ ሽልማት መቀዳጀቱን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።
ለተጨማሪ ንባብ: https://shorturl.at/5jKtg
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #AFRAA
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አራት ነጥብ አግኝተው፣ የዩኒቨርስቲ ቆይታቸውንም በወርቅ ሜዳልያ አጠናቅቀው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ካለፉት አርባ አመታት በላይ በተለያዩ የሐላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለው በአሁኑ ወቅት አየር መንገዳችንን በግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚነት እየመሩ የሚገኙት አቶ መስፍን ጣሰው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ያደረጉትን ቆይታ እንድትከታተሉ ጋብዘናችሗል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) https://youtu.be/mwtyuNVAsSQ