Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.6K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ወደ በርካታ መዳረሻዎቻችን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ቅርንጫፍ ቢሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦች ያስተዋወቀ ልዩ መርሐግብር በኪንሻሳ አካሄደ። በመርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመኑ የደረሰባቸውን አዳዲስ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ በማስተዋወቅና አህጉሪቱን ከመላው ዓለም ጋር በማገናኘት ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋፅዎ የተገለፀ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏትን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶችና ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሰፊው ተዋውቀውበታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዘመናዊነትንና ዕምቅ ባህላዊ ይዘቶችን አለም አቀፍ ዕውቅና ከተቸራቸው ሙዚየሞች ጋር አጣምራ ወደያዘችው ፍራንክፈርት ከተማ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አስደሳች የበረራ ጉዞ ያድርጉ!
#ፍራንክፈርት #የኢትዮጵያአየርመንገድ
መልካም አለም ዓቀፍ የሕፃናት ቀን ለወደፊቱ አቪዬሽን ቴክኖሎጂ ተረካቢዎች!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አለምዓቀፍየሕፃናትቀን