ቻይና ወደሚገኙ መዳረሻዎቻችን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app አሊያም በቴሌግራም ቻት ቦት https://t.me/ethiopian_chatBot ተጠቅመው ትኬትዎን በመግዛት አስደሳች የበረራ ቆይታ እና ልዩ ግዜ ያሳልፉ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት። ሽልማቱ የተበረከተው ኮርፖሬሽኑ 35ኛ ዓመቱን ባከበረበት ደማቅ መርሓ ግብር ላይ ሲሆን አየር መንገዳችን ላባረከተው የላቀ አገልግሎት እና የላቀ የስራ አጋርነት ዕውቅና የተሰጠበት ነው። ይህ ሽልማት ለዛምቢያ ኤርፖርት ዕድገት በመንገደኛ እና በዕቃ ጭነት የአገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያበረከተው አስተዋፅዖ እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ማሳያ ነው። ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። https://rb.gy/5t3iso
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቻይና ጓንዡ በሚያደረገው ሰባት ሳምንታዊ በራራዎች ላይ ሶስት ተጨማሪ በረራዎች በማከል ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን ሳምንታዊ የመንገደኛ በረራ አገልግሎት ወደ አስር ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ሲያበስር በደስታ ነው። ትኬትዎን በድረ ገፃችን www.ethiopianairlines.com በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app አሊያም በቴሌግራም ቻት ቦት https://t.me/ethiopian_chatBot ተጠቅመው በመቁረጥ ጉዞዎን ያቀላጥፉ፤ በልዩ መስተንግዷችን ልዩ ግዜ ያሳልፉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ጓንዡ #ቻይና
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ጓንዡ #ቻይና
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሮም ጣልያን በረራዎች 60ኛ አመት! በእምቅ ባህላዊ እሴት፣ ጥንታዊ ታሪክ እና አስደናቂ የኪነ ሕንፃ ጥበብ የምትታወቀውን የጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ከዓለም ጋር በማገናኘት ለስድስት አስርት ዓመታት የዘለቀ ያልተቋረጠ የአቪዬሽን አገልግሎት ልህቀት! ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://rb.gy/qghf61
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #60ስኬታማዓመታት #ሮም
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #60ስኬታማዓመታት #ሮም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሮም ጣልያን በረራዎች 60 ኛ ዓመት በማስመልከት በሮም ጣሊያን ለሚዲያዎች መግለጫ የተሰጠ ሲሆን በመርሓ ግብሩ ላይ በጣሊያን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀምቢሳ፣ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓልሴ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ የ “Aeroporti di Roma” (ADR) ኤርፖርት ኦፕሬሽን ኃላፊዎች፣ በሮም እና ሚላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #60ስኬታማዓመታት #ሮም
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #60ስኬታማዓመታት #ሮም