Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.77K photos
141 videos
2 files
412 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሮም ጣሊያን በረራ ማድረግ የጀመረበትን 60ኛ ዓመት በማስመልከት በሮም ግራንድ ሆቴል ፕላዛ ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ተካሂዷል። በመርሓ ግብሩ ላይ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የሮም በረራ ስኬት አስተዋፅዖ ላበረከቱ የተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።
በዚህ ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት በጣሊያን የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀምቢሳ፣በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓልሴ፣ በጣሊያን የሚገኙ የሌሎች ሀገራት አምባሳደሮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣የ “Aeroporti di Roma” (ADR) ኤርፖርት ኃላፊዎች፣በጣሊያን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት፣ በሮም እና ሚላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አጋሮች እና ልዩ ልዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #60ስኬታማዓመታት #ሮም