Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.55K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሮም ጣልያን በረራዎች 60ኛ አመት! በእምቅ ባህላዊ እሴት፣ ጥንታዊ ታሪክ እና አስደናቂ የኪነ ሕንፃ ጥበብ የምትታወቀውን የጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ከዓለም ጋር በማገናኘት ለስድስት አስርት ዓመታት የዘለቀ ያልተቋረጠ የአቪዬሽን አገልግሎት ልህቀት! ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://rb.gy/qghf61

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #60ስኬታማዓመታት #ሮም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሮም ጣልያን በረራዎች 60 ኛ ዓመት በማስመልከት በሮም ጣሊያን ለሚዲያዎች መግለጫ የተሰጠ ሲሆን በመርሓ ግብሩ ላይ በጣሊያን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀምቢሳ፣ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓልሴ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ የ “Aeroporti di Roma” (ADR) ኤርፖርት ኦፕሬሽን ኃላፊዎች፣ በሮም እና ሚላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #60ስኬታማዓመታት #ሮም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሮም ጣሊያን በረራ ማድረግ የጀመረበትን 60ኛ ዓመት በማስመልከት በሮም ግራንድ ሆቴል ፕላዛ ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ተካሂዷል። በመርሓ ግብሩ ላይ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የሮም በረራ ስኬት አስተዋፅዖ ላበረከቱ የተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።
በዚህ ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት በጣሊያን የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀምቢሳ፣በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓልሴ፣ በጣሊያን የሚገኙ የሌሎች ሀገራት አምባሳደሮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣የ “Aeroporti di Roma” (ADR) ኤርፖርት ኃላፊዎች፣በጣሊያን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት፣ በሮም እና ሚላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አጋሮች እና ልዩ ልዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #60ስኬታማዓመታት #ሮም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ህዝቦችን፣ ባህሎችን እና ኢኮኖሚዎችን በማስተሳሰር ለ60 ዓመታት የዘለቀ ስኬታማ የአየር በረራ አገልግሎት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #60ስኬታማዓመታት #ሮም