Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ኢትዮጵያ በቀዳሚነት አፍሪካውያንን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር እያገናኘ ለዘመናት የዘለቀ ፓን አፍሪካዊ አየር መንገድ መገኛ አገር ናት። በመጪው አዲስ ዓመት ትኬትዎን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ገዝተው በአዲስ መንፈስ በአዲስ ከፍታ ከፓን አፍሪካዊው አየር መንገድዎ ጋር ይብረሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት
ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ፤ ምድረ ቀደምት!
ትኬትዎን ባመችዎት አማራጭ ቆርጠው አገርዎን ይጎብኙ ያስጎብኙ ።
ድረ-ገፅ www.ethiopianairlines.com
ተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት
ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት እና አቪዬሽን ልህቀት ማዕከል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት
ከ2016 ስኬቶቻችን በጥቂቱ። 2016ን ከነዚህ ስኬቶች ጋር በማገባደድ ለ2017 በአዲስ መንፈስ ለበለጠ ከፍታ ተዘጋጅተናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት #ስኬታማዓመት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2017 አደረሳችሁ እያለ መጪው ዘመን የሰላም፣ የስኬት እና የደስታ እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።
መልካም አዲስ ዓመት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያአዲስአመት
ክቡራን መንገደኞቻችን

በናይሮቢ የጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሠራተኞች በስራ ማቆም አድማ ላይ በመሆናቸው ወደ ናይሮቢ የምናደርገው በረራ በታቀደለት መርኃ ግብር እየተከናወነ አይደለም።

በዚህ አጋጣሚ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልን የምንገኝ መሆኑን እየገለጽን በክስተቱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ እንጠይቃለን።

ለበለጠ መረጃ የዓለም አቀፍ የደንበኞች አገልግሎት ማዕከላችንን በ+251 11 617 9900 ወይም በ 6787 በመደወል አልያም ናይሮቢ የሚገኘውን ትኬት ሽያጭ ቢሯችንን እንዲጎበኙ በትህትና እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አልያንስ አባል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ፖርት ሱዳን የመንገደኛ በረራ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን ሲገልፅ በደስታ ነው።

ይህ አዲስ በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት ለማስተሳሰር ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ከመሆኑም በላይ በቀጠናው ያለውን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የንግድና ቱሪዝም ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።

ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://rb.gy/faairf

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስበረራ #ፖርትሱዳን
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስታር ዋይድ አዋርድ 2016 ‘ቀልጣፋ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋም’ በመባል በሕዝብ ድምፅ ተሸላሚ ሆኗል። ሽልማቱን አስመልክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሽልማት ርክክብ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ሽልማት የሚያስደስተን ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ለላቀ ደረጃ በትጋት እንድንሰራ የሚደግፈን ነው ብለዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦትስዋና ጋቦሮኒ በተካሄደው የ2024 የአፍሪካ ቱሪዝም አመራር ፎረም ላይ “የላቀ የቱሪዝም ትራንስፖርት ሽልማት” እንደተበረከተለት ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው። ይህ ሽልማት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመንገደኞች በማቅረብ እንዲሁም ዘላቂነት እና የአየር ንብረት ጥበቃ ላይ ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ ለአፍሪካ ቱሪዝም ኢንደስትሪ የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ድርጅቶች ዕውቅና የሚሰጥበት ነው። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://rb.gy/ifr4sj
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በብሩህ የአዲስ ዘመን ተስፋ በአዲሱ ዓመት በደማቅ መስተንግዶ ልናገለግልዎ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት
ክቡራን ደንበኞቻችን
የደንበኞች ጥሪ መቀበያ ማዕከል ቁጥራችን 6787 በሙሉ አቅሙ ጥሪዎችን እየተቀበለ እንዳልሆነ ተረድተናል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የቴክኒክ ባለሙያዎቻችን እየሰሩ ይገኛሉ። በ6787 መገልገል ያልቻላችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን በድረ ገፃችን www.ethiopianairlines.com በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app አሊያም በቴሌግራም ቻት ቦት https://t.me/ethiopian_chatBot ተጠቅመውአገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጨማሪ እርዳታ የምትሹ ደንበኞቻችን በአቅራቢያችሁ ወደሚገኙ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችን አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን። ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
ክቡራን ደንበኞቻችን

ዛሬ በደንበኞቻችን የጥሪ አገልግሎት ማዕከል ቁጥር 6787 ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ማዕከሉ የደንበኞችንን ጥሪ በሙሉ አቅሙ እየተቀበለ አለመሆኑን መግለፃችን ይታወሳል።

ችግሩን ለመቅረፍ የቴክኒክ ባለሙያዎቻችን ባደረጉት ርብርብ በአሁኑ ሰዓት አገልግሎቱን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል። በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ወደ 6787 በመደወል የተለመደውን የደንበኞች አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እያስታወቅን ለተፈጠረው ችግር በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሰዎ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በርካታ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ከአስደሳች የበረራ ቆይታዎች ጋር!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኅዳር 23 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ የሚያደርገውን አራት ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ በሳምንት ስድስት ቀን በረራ ማድረግ የሚጀምር መሆኑን ሲገልፅ በደስታ ነው። ትኬትዎን በድረ ገፃችን www.ethiopianairlines.com በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app አሊያም በቴሌግራም ቻት ቦት https://t.me/ethiopian_chatBot ተጠቅመው በመቁረጥ ጉዞዎን ያቀላጥፉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አቴንስ #ግሪክ
ቻይና ወደሚገኙ መዳረሻዎቻችን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app አሊያም በቴሌግራም ቻት ቦት https://t.me/ethiopian_chatBot ተጠቅመው ትኬትዎን በመግዛት አስደሳች የበረራ ቆይታ እና ልዩ ግዜ ያሳልፉ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ