Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
መሃላ በተግባር!
አቶ ለማ በቀለ አለሙ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴኪዩሪቲ ክፍል ውስጥ የሚሰሩ የሥራ ባልደረባችን ሲሆኑ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ ምገባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት በመወጣት አስመስክረዋል። አቶ ለማ በሥራ ገበታቸው ላይ በነበሩበት ወቅት አንድ መንገደኛ ረስተዉ የሄዱትን የእጅ ቦርሳ ውስጡ ከነበረው 71 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ጋር ምንም ሳያጎድሉ በሙሉ ለሚመለከተው የአየር መንገድ ቢሮ ያስረከቡ ሲሆን፤ አየር መንገዱም አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ንብረቱ ለውድ ደንበኛችን እንዲመለስ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም-አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ የደንበኞች አገልግሎትን የዕድገቱ መርሕ አድርጎ በስኬት ጎዳና ላይ የሚገኝ ብሔራዊ ኩራት ነው። በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጀመንት አባላት እና ሠራተኞች ለዚህ መልካምና አርዓያነት ላለው ተግባር የከበረ ምስጋና ያቀርባሉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ክቡራን መንገደኞቹ አዝናኝ የበረራ ቆይታ ይኖራቸው ዘንድ የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን የሚያቀርበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የሙዚቃ ስራዎች 140 ወደሚጠጉ ዓለም-አቀፍ መዳረሻዎቹ ለሚጓዙ መንገደኞቹ ተደራሽ የሚሆኑበትን አማራጭ ይዞ ብቅ ብሏል። በመሆኑም የሙዚቃ ስራዎቻችሁ አየር መንገዱ በሚያቀርበው የአውሮፕላን ውስጥ የመዝናኛ ቻናሎች ምርጫ ውስጥ እንዲካተትላችሁ የምትፈልጉ የጥበብ ባለሙያዎች በሙሉ ደረጃቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ሙዚቃዎቻችሁን ይዛችሁ በመቅረብ የዕድሉ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።
ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በስልክ ቁጥሮቻችን 0115178079/4079/8197 ይደውሉ። አሊያም በኢሜል አድራሻዎቻችን HiwotGe@ethiopianairlines.com ወይም
HilinaBel@ethiopianairlines.com ይፃፉልን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አላያንስ አባል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው “World Travel Awards” ሽልማት በስድስት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀርቧል። ዘርፎቹም ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ፣ ምርጥ የአፍሪካ ቢዝነስ ክላስ አየር መንገድ፣ ምርጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ክላስ አየር መንገድ፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ብራንድ፣ ምርጥ የአፍሪካ የበረራ ላይ መዝናኛ መፅሔት ሰላምታ እና ምርጥ የአፍሪካ ኮንፈረንስ ሆቴል (የኢትዮጵያ ስካይ ላይት) ዘርፎች ናቸው። እርስዎም ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመጠቀም ድምፅዎን የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት ለሆነው አየር መንገድዎ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በደማቅ ፈገግታ ተቀብለን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው “World Travel Awards” ሽልማት ላይ በምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ብራንድ ዘርፍ ዕጩ ሆኖ ቀርቧል። እርስዎም ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመጠቀም ድምፅዎን የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት ለሆነው አየር መንገድዎ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና በአፍሪካ በቀዳሚነቱ የሚጠቀስ የአቪዬሽን ትምህርት እና ስልጠናዎችን ከአፍሪካ እና ከተቀረው ዓለም ለሚቀበላቸው ተማሪዎች በተለያየ ፕሮግራም በማስተማር ለአመታት ዘልቋል።
ዘመናዊና ምቹ የሆኑ የማስተማሪያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ብቁ እና የሰለጠነ የሰው ሀብት ለአፍሪካ ብሎም ለአለም አቪዬሽን ኢንደስትሪ እያበረከተ የዘርፉ የልህቀት ማዕከል ሆኖ ቀጥሏል።
#የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርስቲ
በ World Travel Awards ሽልማት አምና የተቀዳጀነውን የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ አየር መንገድ ሽልማት ዘንድሮም ለመድገም አንድ ርምጃ ብቻ ቀርቶናል። ከታች በተቀመጠው ሊንክ ለዚህ ዘርፍ የታጨውን አየር መንገድዎን ይምረጡ!
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዲጂታል አማራጮቹ በተጨማሪ በአዳዲስ የሽያጭ ቢሮዎች ይበልጥ ወደ እርስዎ ቀርቧል። በሜክሲኮ ከንግድና ዘርፍ ምክር ቤት ወደ አፍሪካ ህብረት በሚወስደው መንገድ ላይ እንዲሁም ከሲ.ኤም.ሲ ወደ አያት በሚወስደው መንገድ ፀሀይ ሪል ስቴት ፊት ለፊት በሚገኘው አዲስ-አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል በከፈትናቸው አዳዲስ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችን አገልግሎት መስጠት ጀምረናል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን Lidya Bekele ናቸው፤ እናመሰግናለን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቦይንግ እና ቲንክ ያንግ በቅንጅት ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ለተውጣጡ ተማሪዎች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርቶች (STEM) ልዩ ስልጠና በመስጠት ተማሪዎችን አስመርቀዋል። ሰልጣኞቹ ከ28 የተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትቤቶች የተውጣጡ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ ስልጠናውም በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩነቪርሲቲ በኩል ተሰጥቷል። ይህ STEM የተሰኘ ፕሮግራም አሁን ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጠ ሲሆን የትምህርት ተደራሽነት በበቂ ሁኔታ ባልተሟላባቸው አካባቢዎች ላሉ ወጣቶች ልዩ ትኩረት ያደርጋል። በዚህ በ2ኛው ዙር ከተመረቁ ተማሪዎች ውስጥ 50% ሴቶች ናቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በዘንድሮው የ “World Travelers Award” ሽልማት ከታጨንባቸው ስድስት ዘርፎች አንዱ በአፍሪካ ምርጡ የኢኮኖሚ ክላስ አየር መንገድ ዘርፍ ነው። ከታች በተቀመጠው ሊንክ ለዚህ ዘርፍ የታጨውን አየር መንገድዎን ይምረጡ!
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሽልማት ውድድሮችና መድረኮች በአፍሪካ አቪዬሽን ኢንደስትሪ በመሪነት የተቀመጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው የ “World Travel Awards” ሽልማት ከዚህ ቀደም ለአራት ጊዜያት በ”ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ዘርፍ ሽልማትን የተቀዳጀ ሲሆን ዘንድሮም እጩ ሆኖ ቀርቧል። ከታች በተቀመጠው ሊንክ ለዚህ ዘርፍ የታጨውን አየር መንገድዎን ይምረጡ!
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ብሔራዊ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገራችንን አቪዬሽን ዘርፍ ዕድገት ከፍ ለማድረግ አዳዲስ ኤርፖርቶችን በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች በመገንባት ለአገልግሎት እያበቃ ሲሆን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን ጨምሮ ነባር ኤርፖርቶችና የመንገደኛ ማስተናገጃ ተርሚናሎችን በከፍተኛ ወጪ እያስፋፋና እያዘመነ ይገኛል።
የአዳዲስ አቪዬሽን መሰረተ ልማቶች መገንባትና የማስፋፊያና ዝመና ተግባራት መጠናቀቅ የበለጠ ምቹ እና ተደራሽ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት ከማስቻሉም በላይ ንግድና ቱሪዝምን ለማሳደግ የጎላ ሚና ይኖረዋል። ባለፉት ጥቂት አመታት ኤርፖርቶችን ለማስፋፋትና ለማዘመን በኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተተገበሩ ያሉት ስትራቴጂክ መዋዕለ ንዋዮች የደንበኞች አገልግሎትን ምቹ፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ የላቀ እገዛ ያደርጋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ለክላውድ ናይን” (ቢዝነስ ክላስ) መንገደኞቹ ነፃ የበረራ ላይ ገመድ-አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን እየገለፀ ደንበኞች በአገልግሎቱ በመጠቀም አስደሳች የበረራ ቆይታ እንዲያሳልፉ ሲጋብዝ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የባንግላዴሽ ዋና ከተማ ወደሆነችው ዳካ ከተማ ከጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ስድስት ቀናት አዲስ በረራ እንደሚጀምር ሲያበስር በደስታ ነው። ይህ አዲስ የበረራ መስመር የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ እስያ ያለውን ተደራሽነት የሚያሰፋ ሲሆን በባንግላዴሽ እና አፍሪካ መካከል ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር የሚደረገውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። https://rb.gy/uoqkmg
#የኢትዮጵያአየርመንገድ