Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.55K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ ሰልጥነው ብቁ የአቪየሽን ባለሙያ ይሁኑ።
#የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርስቲ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ ሰልጥነው ብቁ የአቪየሽን ባለሙያ ይሁኑ።
#የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርስቲ
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና በአፍሪካ በቀዳሚነቱ የሚጠቀስ የአቪዬሽን ትምህርት እና ስልጠናዎችን ከአፍሪካ እና ከተቀረው ዓለም ለሚቀበላቸው ተማሪዎች በተለያየ ፕሮግራም በማስተማር ለአመታት ዘልቋል።
ዘመናዊና ምቹ የሆኑ የማስተማሪያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ብቁ እና የሰለጠነ የሰው ሀብት ለአፍሪካ ብሎም ለአለም አቪዬሽን ኢንደስትሪ እያበረከተ የዘርፉ የልህቀት ማዕከል ሆኖ ቀጥሏል።
#የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርስቲ
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ 200 የሚደርሱ ጋቦናውያን ተማሪዎችን በደማቅ ስነስርዐት ተቀበለ። ጋቦናውያኑ ተማሪዎች በተለያዩ የአቪዬሽን ዘርፎች በዩኒቨርስቲያችን ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ሲሆን በአቀባበል ስነስርዐቱ ላይ በኢትዮጵያ የጋቦን ሪፐብሊክ አምባሳደር ክብርት ሊሊ ስቴላ ንዶንግ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ሓላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ የአየር መንገዳችን ከፍተኛ የስራ ሓላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርስቲ
በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የትኛውን የስራ መስክ ለመቀላቀል ይፈልጋሉ? ሀሳብዎትን ያጋሩን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርስቲ
ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ በዘለቀው የላቀ የአቪዬሽን ስልጠና ግንባር ቀደም ውጤት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የአብራሪዎች ስልጠና ክፍል እ.ኢ.አ ከተመሰረተበት ከ1964 ዓ.ም ጀምሮ ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ አቪዬሽን ዕድገት የራሱን ጉልህ አስተዋፅዖ እያበረከተ ይገኛል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርስቲ