Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.57K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ወዳጅነት በተሞላው ልባዊ መስተንግዶአችን ልንቀበልዎ ዝግጁ ነን። ከእኛ ጋር በምቾት ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፍረው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ፈገግታን በተላበሰ መስተንግዶ ወዳሻዎት ቦታ ይጓዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመግታት በተደረገው ዓለም አቀፍ ርብርብ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ በቶሮንቶ ካናዳ በተካሄደ የመጀመሪያው ድህረ ኮቪድ ኮንፈረንስ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት።
ሽልማቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በአፍሪካ እና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የሚገኙ አገራት ወረርሽኙን ለመከላከል ጥቅም ላይ ያዋሉዋቸውን የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶች በቀልጣፋ አገልግሎቱ በማጓጓዝ የበርካቶችን ህይወት ለመታደግ በተደረገው ጥረት ለነበረው የጎላ ሚና የተሰጠ ነው።
ኮንፈረንሱ የተዘጋጀው በDevelopment International Initiatives (LDII) ፣በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት(ኢጋድ) እና የተለያዩ ወረርሽኞችን በጋራ መከላከል ላይ አተኩረው በሚሰሩ የስራ አጋሮች ትብብር ነው።
ለበለጠ መረጃ: https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-receives-global-recognition-and-appreciation-award-for-outstanding-role-in-covid-19-response
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጉዘው ሊያዩት የሚሹት መዳረሻ የት ነው?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን አቤል መንግስቱ ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበርሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ