Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.55K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በህንድ አራተኛ መዳረሻ ከተማችን ወደሆነችው ቸናይ በረራ ማድረግ የጀመርንበትን ሁለተኛ ዓመት በደመቀ ሁኔታ አክብረናል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህንድን ዋና ከተማ ኒው ዴልሂን ጨምሮ፣ ሙምባይ እና ባንግሎር ከተሞችን ከአፍሪካ እና ከመላው ዓለም ጋር ያገናኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ቸናይ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፖላንድ ዋርሶ የመጀመሪያ በረራ በግሩም የእራት ድግስ በዋርሶ ደምቆ አምሽቷል። በምሽቱ ለበረራው መሳካት የራሳቸውን አሻራ ላኖሩ አካላት ዕውቅና እና ምስጋና ተበርክቷል።
አሁን ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ጋር ደማቋን ዋርሶን ለመጎብኘት ሁሉም ተመቻችቶልዎታል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በምንታወቅበት ምርጥ እና አስደሳች ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ልናገለግልዎ እና ወደ መዳረሻዎ በልዩ እንክብካቤ ከፍ ብለን ልንበር ዝግጁ ነን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በደማቅ ፈገግታ ተቀብለን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአውሮፓ የውብ ተፈጥሮና መልከዓ ምድር፣ ማራኪ ታሪካዊ ቦታዎች እና ቅርሶች ባለቤት ወደ ሆነችው የፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው በሳምንት አራት ቀናት በመብረር አፍሪካን ከፖላንድ ብሎም ከተቀረው ዓለም ያገናኛል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፖላንድ #አፍሪካ #ዋርሶው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከተሞች ወደሆኑት ኒያሚ ፣ ባማኮ እና ዳካር በረራ በመጀመር አፍሪካን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት የበረራ አድማሱን ማስፋፋት በቀጠለበት ወቅት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
ከእኛ ጋር ወደሚፈልጉት መዳረሻ ለመብረር ይዘጋጁ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
መግለጫ

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች “የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግብራቸውን በታማኝነት ለሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ክብራቸውን የሚመጥን ልዩ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ መዘጋጀቱን ገለጸ” የሚል ዘገባ እንደተሰራጨ አስተውለናል።

ይሁንና የሁነቱ ትክክለኛ አውድ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢዝነስ ዪኒቶች አንዱ በሆነውና በአየር መንገዱ ባለቤትነት ከሚተዳደረው የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል መካከል የተደረገ ስምምነት ብቻ ሲሆን ይህም ታማኝ ግብር ከፋዮች የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ለደንበኞቹ በሚያቀርባቸው አገልግሎቶች ለታማኝ ግብር ከፋይነታቸው የሚመጥን ልዩ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የጋራ መግባባት ከመደረሱ ውጪ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ ጋር የተደረገ ሌላ ሰምምነት አለመኖሩን እንገልፃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
ወደሚፈልጉት መዳረሻ ልናደርስዎ ሁሌም ዝግጁ ነን! መልካም ቀን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ክቡር ሙሳ ፋኪ ማህማትን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀብለን በክብር አስተናግደናል። ክቡር ሊቀ መንበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቅጥር ግቢ እና የስራ ክፍሎች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከአየር መንገዳችን ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ከፍተኛ የአመራር አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታና ስኬት ጋር ቅርብ ቁርኝት ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በምስረታው ወቅት የህብረቱ መስራች የነበሩ ታላላቅ የአፍሪካ መሪዎችን ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች በማጓጓዝ የተጫወተውን ቁልፍ ሚና ዛሬም አፍሪካውያንን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር ይበልጥ በማስተሳሰር አይተኬ ሚናውን በትጋት እንደሚወጣ ይገልፃል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ